ዋልያዎቹ በውዝግብና በስጋት ታጅበው ብሩንዲን ያስተናግዳሉ
ጥቅምት 14, 2008


በይርጋ አበበ

በአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ የሚመራው የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ሩዋንዳ ለምታስተናግደው 4ኛው የቻን ዋንጫ ለማለፍ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ይገኛል። ቡድኑ ከሳምንት በፊት ቡጅንቡራ ላይ በብሩንዲ ብሔራዊ ቡድን ሁለት ለባዶ ተሸንፎ እና አማካይ አጥቂውን ኤፍሬም አሻሞን በቀይ ካርድ ከሜዳ አሰናብቶ የተመለሰ ሲሆን አዲስ አበባ ላይ ደግሞ በልምምድ ሜዳ አምበሉ የደደቢቱ ስዩም ተስፋዬ እና አዲሱ የፈረሰኞቹ አጥቂ ራምኬል ሎክ በፈጠሩት ውዝግብ ወደ ድብድብ በማምራት የቡድኑን አንድነት ሳያናጋው እንዳልቀረ ከብሔራዊ ቡድኑ ካምፕ የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል። የብሩንዲው የመጀመሪያ ጨዋታም ቡድኑን ስጋት ላይ ሳይጥለው እንዳልቀረ ተነግሯል።

የመጀመሪያውን ጨዋታ ተሸንፎ የተመለሰው ቡድን በመልሱ ጨዋታ ተጋጣሚውን በሶስት ጎል ልዩነት ካላሸነፈ ወደ ውድድሩ የማያመራ ቢሆንም አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ግን “የማይቻል ነገር የለም በመልሱ ጨዋታም አሸንፈን ወደ ሩዋንዳ የሚወስደንን አውሮፕላን እንሳፈራለን” ሲል ስፖርት ዞን ለተባለው ድረገጽ ተናግሯል። ቡድኑ ወደ ሩዋንዳ የሚወስደውን አውሮላን እንዲሳፈር መንገዱ ላይ የቆመውን የብሩንዲን ብሔራዊ ቡድን ማሸነፍ የግድ የሚለው ሲሆን ለዚህ ግዳጅ ደግሞ ቡድኑን በአዳዲስ እና ወሳኝነታቸው ከፍተኛ ነው የተባሉ ተጫዋቾችን በማካተት ልምምድ ሲሰራ ቆይቷል። በተለይ በቻን ዋንጫ የማይሳተፈውን ሽመልስ በቀለን የሚተካው ፈጣሪ አማካይ ያልነበረው የዮሃንስ ሳህሌ ስብስብ ለብሩንዲው ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡናውን ኤልያስ ማሞን እና የመከላከያውን ፍሬው ሰለሞንን በመጥራት ክፍተቱን ለመሙላት እንደተዘጋጀ ተናግሯል።

ቡድኑ በዚህ መልክ ልምምዱን አጠናክሮ እየሰራ መሆኑ በተነገረበት ወቅት ግን አምበሉ ስዩም ተስፋዬ እና አቂው ራምኬል ሎክ ልምምድ ሜዳ ላይ መጋጨታቸው አነጋጋሪ እና አሳዛኝ ክስተት ሆኗል። በተጫዋቾቹ ግጭት ዙሪያ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከብሔራዊ ቡድኑ ብራንድ ስፖንሰር ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት አሰልጣኙም ሆነ የቡድኑ አምበል ከጋዜጣዊ መግለጫ ውጭ ምንም አይነት መረጃ ለማንኛውም ጋዜጠኛ መስጠት የማይችሉ በመሆኑ ስለተጫዋቾቹ ግጭትም ሆነ ስለወቅታዊው የቡድኑ ስሜት አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌን ማነጋገር አልቻልንም። ምክንያቱም ፌዴሬሽኑ ቀድሞ ከላይ የተጠቀሰውን መመሪያ አስተላልፏልና።

የዋልያዎቹ እና የብሩንዲ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ዛሬ ከቀኑ አስር ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚካሄድ ሲሆን ጨዋታውንም ኢትዮፉትቦል ዶትኮም እንደተለመደው በቀጥታ ስርጭት የሚያስተላልፍ መሆኑን በደስታ ይገልጻል። አንባቢያን ውጤት በመተንበይ ተሸላሚ እንድትሆኑም እንጋብዛለን።

መልካም ጨዋታ ለሁለቱም ቡድኖች መልካም ውጤት ለዋልያዎቹ!!

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Atinafu [850 days ago.]
 3 le o tashenifalech

Atinafu [850 days ago.]
 3 le o tashenifalech

yilkal [850 days ago.]
 congratulate the player and coach Yohanes. but the next game with Congo it will be very difficult to overcome. Coach Yohanes please think about your stackers . defender and midfielder give chance to pass chan. please think about your decision regarding Sladin, Getaneh and Umed If not I doubt to pass world cup group stage

Mali [850 days ago.]
 Idiot coach Burindin ashenefe ! lol

Yoni [850 days ago.]
 ይሄ ማፈሪያ ኮች በዚህ ብድን ነበር 2 ለ 0 ተሸንፎ የመጣው ?! ኮች ሰውነት ቢሻው ወይም ሌላ ኮች ቢሆን ኖሮ ጨዋታውን እዛው ቡርንዲ ላይ ጨርሰውት ይመጡ ነበር ! ማፈሪያ ነህ ዮሃንስ ! አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ኮች ጠፍቶ ነው አንተ የዋልያዎቹ ኮች የሆንከው ?!!! ቆይ ጠብቅ ሁሉንም ነገር የተደበቀውን የፖለቲካ ት ስ ስ ር ጊዜ ይፈታዋል እስከዛ ድረስ ግን አንተ ባለ ጊዜ ነህ ፈንጭብን !

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!