ዋልያዎቹ ወደ ሩዋንዳ የሚወስዳቸውን ትኬት ቆረጡ
ጥቅምት 14, 2008

ከሳምንት በፊት ቡጁንቡራ ላይ በብሩንዲ ብሔራዊ ቡድን የሁለት ለባዶ ሽንፈት አስተናግዶ የነበረው የዮሐንስ ሳህሌ ስብስብ ዛሬ በደጋፊው ፊት በመጫወት የመጀመሪያውን ጨዋታ ውጤት በመቀልበስ በቻን ዋንጫ የሚያሳትፈውን ውጤት አስመዘገበ።  

ከጨዋታው በኋላ ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች መግለጫ የሠጠው አሠልጣኝ ዮሐንስ ሣህሌ ለዚህ ውጤት መገኘት ትልቁን ስራ የሠሩት ተጫዋቾቼ ናቸው ላመሠግናቸው እፈልጋለሁ ብሏል። ከጨዋታው በፊት በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን በስፋት የተዘገበው የስዩም ተስፋዬ እና ራምኬሎ ግጭትም ከጊዜያዊ አለመግባባት የተፈጠረ ነበር ወዲያውኑ ተፈቷል ሲል ተናገግሯል። ዋልያዎቹ ሩዋንዳ ለምታስተናግደው አራተኛው የቻን ዋንጫ ያለፉባቸውን ጎሎች ያስቆጠሯቸው ተከላካዩ ስዩም ተስፋዬ እና አማካዩ ጋቶች ፓኖም ናቸው። የኢትዮጵያ ቡናው ኤልያስ ማሞ ደግሞ የጨዋታው ኮከብ ሆኖ አምሽቷል።
Gatoch Panom Scoring The Winning 3rd Goal From a penalty

የጨዋታውን ዝርዝር ዘገባ እና የአሠልጣኝ ዮሐንስን መግለጫ በነገ ረፋድ ዘገባችን ይዘን የምንመለስ ይሆናል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!