የ18 ዓመት ድልን ለማነቃቂያነት የተጠቀመው አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ
ጥቅምት 15, 2008

በይርጋ አበበ

የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ትናንት አመሻሽ ላይ በካምቦሎጆ የብሩንዲን ብሔራዊ ቡድን ገጥሞ ሶስት ለምንም በማሸነፍ ሩዋንዳ ለምታስተናግደው አራተኛው የቻን ዋንጫ ማለፉን አረጋግጧል። ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላም አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በራስ መተማመን ስሜት ተሞልቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ከጋዜጠኞች ለተነሱለት በርካታ ጥያቄዎች መልስ ሰጥቷል። አሰልጣኙ በሰጠው ፖስት ማች ኮንፍረንስ ላይ የተመረጡ ጥያቄዎችንና መልሶችን ከዚህ በታች አቅርበናቸዋል።

የተጫዋቾችን ሞራል ማነሳሳት

ከሳምንት በፊት በቡጅቡራ የሁለት ለባዶ የሽንፈት ጽዋን ተጎንጭቶ የተመለሰው የዮሐንስ ሳህሌ ስብስብ አዲስ አበባ ላይ ያን ውጤት ቀልብሶ ለቻን ዋንጫ ያልፋል ተብሎ አልተገመተም ነበር ማለት ይቻላል። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ብሩንዲዎች በሜዳቸው ያስቆጠሩት የጎል ብዛት ሲሆን ያንን ውጤት ለመቀልበስ ዋልያዎቹ አንድም ኳስ መረባቸውን ሳትነካባቸው ሶስት ጎሎችን ማስቆጠር ወይም አንድ ጎል እንኳ ቢቆጠርባው አራት ጎሎችን ማስቆጠር ይጠበቅባቸው ስለነበረ ነው። ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአጥቂ ችግር በቀላሉ ይሳካል ተብሎ የሚጠበቅ አይደለም። ለዚህም ነው በርካታ ደጋፊዎች ቡጅንቡራ ላይ በተመዘገበው ውጤት ተስፋ ቆርጠው ካምቦሎጆን ብርድ ያስመቱት። ማለትም በርካታ ደጋፊ ስታዲየም ቢገባም ታዲየሙ ግን አልሞላም ነበር።

አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ግን “ተጫዋቾቼ ውጤቱን መቀልበስ እንደሚችሉ እምነት ነበረኝ” ሲል ተናግሯል። “ለዚህ ደግሞ በተጫዋቾቼ ላይ እኔም ሆንኩ ረዳቶቼ የማነሳሻ ስራ ሰርተናል” ሲል የተናገረ ሲሆን በዋናነት የተጠቀመውም “ፋሲል እና ዓሊ አባል የነበሩበት የ1990 ዓ.ም ማለትም የዛሬ 18 ዓመት ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ግብጽ ላይ አምስት ለባዶ ተሸንፎ ከመጣ በኋላ በመልሱ አምስት ለባዶ ማሸነፉን አንስተን ተነጋግረናል። ተጫዋቾቹም በዚያ ተነቃቅተዋል” ሲል ተናግሯል።

 

 

የመሃመድ ናስር መቀየር

የጎል መስመሩን ለይተው አያውቁም የሚባሉት ኢትዮጵዊያን አጥቂዎች በጎል ድርቅ የሚታሙ ናቸው። ብሔራዊ ቡድኑም በእነዚህ አጥቂዎች የተዋቀረ በመሆኑ ጎሎችን በቀላሉ ያመርታል ተብሎ አይጠበቅም። በትናንቱ ጨዋታም የታየው ይሄው ነው አጥቂዎቹ እያሉ ተከላካዮቹ ሶስት ጎሎችን አስቆጥራው ወጥተዋል። በዚያ ጨዋታ የመጀመሪያ ተሰላፊ የነበረው የመከላከያው አጥቂ መሀመድ ናስር ሲሆን ተጫዋቹ በእረፍት ሰዓት ተቀይ ወጥቷል። ለምን እንደተቀየረ ጥያቄ የቀረበለት ዮሐንስ ሳህሌ ሲመልስ “ቡድኑን ዘግይቶ በመቀላቀሉ ምክንያት ከተጫዋቾቹ ጋር ሊዋሃድ አልቻለም። ሜዳ ላይ በቆየባቸው ደቂቃዎችም እኛ በምንፈልገው መልኩ አልተንቀሳቀሰልንም። ለዚህ ነው የቀየርነው” ብሏል። አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ መሀመድ ናስርን ቀይሮ በማስወጣት በምትኩ ሌላኛውን የመከላከያ አጥቂ ምንይሉ ወንድሙን አስገብቷል። ወጣቱ ምንይሉ ወንድሙ ተቀይሮ ከገባ በኋላም በአንጻራዊነት ከመሀመድ በተሻለ የተጋጣሚ ተከላካዮችን ማስጨነቅ ችሏል።

የአስቻለው ግርማ ተደጋጋሚ ስህተት መስራት እና የኤልያስ ማሞ ብቃት

አስቻለው ግርማ በጨዋታው በተደጋጋሚ ጊዜ ኳሶችን ሲያበላሽ ታይቷል። በርካታ ተመልካቾችም ተጫዋቹን አሰልጣኙ ቀይሮ ያስወጣዋል ብለው ቢጠብቁም ሙሉውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ እንዲጫወት አድርጎታል። በጨዋታው መጠናቀቂያ አካባቢም የተገኘችዋን ፍጹም ቅጣት ምት ያስገኘው እሱ ነው። ለመሆኑ አሰልጣኙ ተጫዋቹን ያልቀየርከው ለምንድን ነው? በእለቱ ምርጥ ሆኖ ያመሸውን ኤልያስ ማሞንስ እንዴት ትገልጸዋለህ? የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ነበር።

ዮሃንስ ሲመልስም አስቻለው ግርማ በእለቱ በርካታ ኳሶችን በተጋጣሚ ተከላካዮች ቢቀማም የነገርነውን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ አድርጓል ያለ ሲሆን “እኛ ለአስቻለውም ሆነ ለጋቶች የነገርናቸው ያገኛችኋቸውን ኳሶች በሙሉ ወደ ፊት እንጂ ወደኋላ አትመልሱ አጥቅታችሁ ተጫወቱ ነበር ያልናቸው። ልጆቹም የነገርናቸውን ተግባራዊ አድርገዋል” ብሏል። የቡናው አማካይ ተከላካይ ኤልያስ ማሞን ብቃት በተመለከተ ለቀረበለት ጥያቄም ልምድ እያገኘ በመምጣቱ ተሻሽሎ ቀርቧል ብሎ መልሷል።

ከመቀመጫህ ለምን አልተነሳህም?

አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በትናንቱ ጨዋታ አንድም ጊዜ ከመቀመጫው ተነስቶ ተጫዋቾቹን ሲያስተባብርና መመሪያ ሲሰጥ አልታየም ነበር። ለምን እንደዛ እንዳደረገ ለቀረበት ጥያቄ የሰጠው መልስ ይህን ነው “ሜዳ ላይ ተጫዋቾቼ ማድረግ ያለባቸውን የነገርኳቸው ከጨዋታ በፊት ነው። በጨዋታውም የነገርኳቸውን ተግባራዊ አድርገዋል ስለዚህ የእኔ ከወንበር መነሳት አስፈላጊ ስላልነበረ አልተነሳሁም” ብሏል።

የቀጣይ ጉዞ ዝግጅት እና ተጋጣሚ

ብሔራዊ ቡድኑ ለቻን ዋንጫ ቢያልፍም በቀጣይ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ከኮንጎ ብራዛቢል ብሔራዊ ቡድን እና ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያዎች እንዲሁም ለሴካፋ የሚያደርጋቸው በርካታ ጨዋታዎች ከፊቱ ይጠብቀዋል። አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ለዚህ ምን አይነት ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ሲጠየቅ “እኛ የምንዘጋጀው እንደተጋጣሚያችን አጨዋወት ነው” ያለ ሲሆን በቻን ውድድርም ሆነ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ እና የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያዎች ቡድኑን በሚገባ እንደሚያዘጋጅ ገልጿል። ለዚህ ደግሞ ፕሪሚየር ሊጉ በቅርቡ የሚጀመር በመሆኑ ተጫዋቾችን በበቂ ሁኔታ ለመምረጥ እድሎችን እንደሚፈጥርለት ተናግሯል። በቀጣይም ሌሎች ተጫዋቾች ብሔራዊ ቡድኑን እንደሚቀላቀሉ የገለጸ ሲሆን ለዚህም በርካታ ስራ ከፊቱ እንደሚጠብቀው ነው የገለጸው።

የአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ፖስት ማች ኮንፍረንስ በርካታ ጥያቄዎች የቀረቡበትና መልስ የተሰጡበት ቢሆንም ኢትዮፉትቦል ዶትኮም ግን ከዚህ በላይ የዘረዘራቸውን ከአንባቢያን እና ለስፖርት አፍቃሪያን ይመጥናሉ ብሎ መርጦ አቅርቧቸዋል። በቀጣይ የብሔራዊ ቡድን ዝግጅትና ተከታታይ መረጃዎችን እየተከታተልን የምናቀርብ ይሆናል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
felexsami [849 days ago.]
 ምንም ጥያቄ አያስፈልገውም እኮ 90 ደቂቃ ሙሉ ከወንበሩ ላይ ተጣብቆ የዋለው የደጋፊውን ቁጣ.... ጩኸት..... ስድብ....መቋቋም ስለማይችል ነው ።።።።።።። ደጋፊውም ፀጥ ብሎ ቡድኑን የደገፈው እሱን ስላላየ ነው ። ይሄኔ ቆሞ ቢሆን ኖሮ ከህዝብ ውግዘት ስድብ ቁጣ ጩኸቶች ያሰክሩትና ደንብሮ ቡድኑንም ያስደነብረውና አይሆኑ ቅያሬዎች ሲያደርግ እናየው ነበር ሃሃሃሃሃሃ

Melaku [849 days ago.]
 ይሄ አሰልጣኝ በዚህ ግትርነቱ ከቀጠለ በእነ ቡርንዲ ... ሲሸልስ .... ሯዋንዳ..... ሱማሊያ... ሌሴቶ .....ተቀልዶበታል በእነ አልጄሪያ ኮንጎ ምን እንደሚገጥመው መገመት በጣም ቀላል ነው !

AbduilBunna [849 days ago.]
 ልክ በለሃል መላኩ ጥሩ ታዝበሃል ዮሃንስ በፊፋ የእግር ኳስ ደረጃቸው ዝቅተኛ በሆኑ ሁሉም ሃገሮች ተሸንፏል ማን ቀረ only ጅቡቲ እና ኤርትሪያ ብቻ. ha ha ha

EM [848 days ago.]
 Its sad to see these kind of un disciplined comments and we will ask Ethiofoot ball if you guys have access please filter each email before its posted for public. Some people use it your website for their political purposes. The players or the coach represent our country and sometime lets think twice before we said bad things . At this time honestly they did a great job and all of us we are happy on their performance and results. Go Wallias and keep it up the good work.

EM [848 days ago.]
 Its sad to see these kind of un disciplined comments and we will ask Ethiofoot ball if you guys have access please filter each email before its posted for public. Some people use it your website for their political purposes. The players or the coach represent our country and sometime lets think twice before we said bad things . At this time honestly they did a great job and all of us we are happy on their performance and results. Go Wallias and keep it up the good work.

Gizegeta [848 days ago.]
 @ getachew gamo :- በጣም ትገርማላችሁ ደካማዋን ቡርንዲን አሸነፍን ብላችሁ ዮሃንስ ልክ ነው ብላችሁ የምትንጫጩት በሙሉ its shame. እኔና የብሔራዊ ቡድኑ ደጋፊዎች ከሰውዬው ጋር ምንም ችግር የለብንም ከሚሰራው ስራ እንጂ ይልቅ አሁን እዚህ የምትንጫጩት በሙላ ብሔራዊ ቡድናችንን በደንብ የምታውቁት አይመስለኝም. የባለፈውን የቡርንዲ ድል አይታችሁ ብቻ ነው ኮመንት የሰጣችሁት. እውነት እላቹሃልሁ ቡድናችንን ሰውነት ቢሻው አሊያም ውበቱ አባተ ወይም ሌላ ኮች የያዘው ቢሆን ኖሮ ቡጁምቡራ ላይ ጨዋታውን ጨርሰውት ይመጡ ነበር .... ቢያንስ እንኳን አቻ ወተው ይመለሱ ነበር. @ ኳስ:- ብሔራዊ ቡድኑን መደገፍ የጀመርከው መቼ ነው ??? ቡድኑን የምታውቀው ቢሆን ኖሮ እንደዚህ ብለህ ባልጠየከኝ ነበር ! ኳስ.... አትሳሳት እኔ ያልኩት ይሄ ቡድን አልጄሪያና ኮንጎን ሲገጥም ምን ሊገጥመን እንደሚችል በግልፅ ነው ያስቀመጥኩት እውነታውም ያ ነው. ቡርንዲን አሸነፍን ብለህ ዮሃንስ ልክ ነው ካልክ ከቀጣይ ጨዋታ በሃላ ምን አይነት ኮመንት እንደምትሰጥ ለማየት ጓጉቻለሁ anyway please አትጥፋ ???!!!

Melaku [847 days ago.]
 @ Vava ይሄ አሰልጣኝ በ ቡርንዲ ... ሲሸልስ .... ሯዋንዳ..... ሱማሊያ... ሌሴቶ .....ተቀልዶበታል በእነ አልጄሪያ ኮንጎ ደግሞ ምን እንደሚገጥመው መገመት አያቅት ህም::

AbduilBunna [847 days ago.]
 እዚህ ፔጅ ላይ new መጤ ኳስ ተመልካቾች የሚሰጡት አስተያየት በጣም ያስቃል ይደብራል:: በአንድ ጨዋታና በደካማ ቡድን አሰልጣኝን ማቆለጳጰስ ኳስ አለማወቅ እንጂ ሃገር ወዳድነት አይደለም :: አሁንም ህዝቡ እያለ ያለው መመራጥ የሚገባቸው ልጆች በአሰልጣኙ ግትርነት አምባገነናዊነት ሳይመረጡ ቀርተው ቡድኑ እየተጎዳ ሃገር እየተዋረድ እየተሰደበ ነው:: ዮሃንስ ከብሔራዊ ቡድኑ ክብር ይልቅ ለራሱ ስም የሚሰራ አሜሪካዊ እንጂ ኢትዮጵያዊ ያልሆነ እንዴትና በምን መስፈርት ከማንስ ጋር ተወዳድሮ የብሔራዊ ቡድናችን አሰልጣኝ እንደሆነ ግልፅ ያልሆነ የስፖርት ተመልካቹ ጥያቄ ነው !!!

Yirga andarge [847 days ago.]
 መጀመሪያ Ethio Football ን አመሰግናለው ለሰጣቹህን መረጃ በተረፈ ግን አሰልጣኙ ላይ ብዙ ትችት ባናበዛና በቂ ግዜ ለአሰልጣኙ ቢሰጠው መልካም ነው

Yirga andarge [847 days ago.]
 መጀመሪያ Ethio Football ን አመሰግናለው ለሰጣቹህን መረጃ በተረፈ ግን አሰልጣኙ ላይ ብዙ ትችት ባናበዛና በቂ ግዜ ለአሰልጣኙ ቢሰጠው መልካም ነው

Tesefahun Gebere [847 days ago.]
 አሰልጣኙን በአንድ ጨዋታ ማወደሱን እኔም አልቀበለውም ተጫውቶም ያሸነፈው ደካማዋን ቡርንዲን ነው ጨዋታውን ከተመለከትኩ በሃላ እንዴት ቡጁምቡራ ላይ 2 le 0 በዚህ ደካማ ቡድን ተሸነፈ ብዬ በጣም ነው የገረመኝ ! የደነቀኝ ! ግን ሰውዬው ጋር ችግሮች አሉ እኔ ብቻ ያልኩት ይሁን እና ጡንቻውን ማሳየት ይፈልጋል ይሄ ነገር ደግሞ ጥሩ አይደለም ከተጫዋቾቹም ሆነ ከደጋፊው ያቀያይመዋል::

Naod [846 days ago.]
 ከተጫዋቾች ጋር መስማማት የማይችል ኮች ምኑን ኮች ሆነው ጎበዝ ኮች እንዴት አድርጎ ተጫዋቾችን ትሪት ማድረግ እንዳለበት ያውቃል:: ዮሃንስ ግን ከሲንየሮቹ ብቻ ጋር ሳይሆን ከ ጁኒየሮቹም ጋር ተባልቶ ተፋጭቶ ሊሞት ነው:: በዚሁ ከቀጠለ ከምክትል ኮቾቹም ጋር የሚጋጭ ይመስለኛል:: እኔ ብቻ ያልኩት ይሁን ማለት ለማንም አልበጀም:: አሁንስ Kim Jong-un መሰልከን !

Gezegeta [844 days ago.]
 @ ኳስ ፖፓፓፓፓፓ የኳስ እውቀትሽ የሚገርም ነው ለዛም ነው መሰለኝ ስምሽን ከአስፋው ወደ ኳስ የቀየርሽው :: ቡርንዲ ትልቅ ቡድን ነው ትላለህ እንዴ ቡርንዲን ያስተለቀው የኛ ድክመት ብቻ ነው:: ነገርኩህ እኮ ኮች ሰውነት ቢሻው ወይም ሌላ ኮች ቢሆን ኖሮ ጨዋታውን እዛው ቡርንዲ ላይ ጨርሰውት ይመጡ ነበር ::

Gizegeta [844 days ago.]
 @ ድል ጥሩ ብለሃል ጥሩ ታዝበሃል የስፖርት ተመልካቹም እያለ ያለው ይሄንኑ ነው የአሰልጣኙም ትልቁ ችግር መጠራት የሚገባቸውን ልጆች ጥሩ አቋም ላይ እያሉም ቢሆን የሰውነት ቡድን ውስጥ ስለነበሩ ብቻ የራሱን ክሬዲት ከፍ ለማድረግ የራሱን ቡድን ሰራ ለመባል እነዚህን ልጆች ዘሏቸዋል ይሄም ነገር ነው ህዝቡን ያሳመመውና ያናደደውም ይሄ ነገር ነው ዮሃንስ ግትርነቱን ትቶ ልምድ ያላቸውን ተጫዋቾች ከአዲሶቹ ጋር በመቀላቀል የሲኒየሮቹን ልምድ መጠቀም ይኖርበታል አለበለዚያ ግን በሲሸልስ እንደዚህ የሆነ ቡድን በአልጄሪያ ና በኮንጎ ምን ሊገጥመው እንደሚችል መገመት በጣም ቀላል ነው

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!