የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገ ይጀመራል
ጥቅምት 16, 2008

በይርጋ አበበ

የ2008 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ነገ ረቡዕ በአዲስ አባ ስታድየም በሚደረግ ጨዋታ ይጀመራል። ፕሪሚየር ሊጉ ነገ መካሄድ ሲጀምር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከመከላከያ ይገናኛሉ። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት የሚካሄድ ይሆናል። የፕሪሚየር ሊጉ የዓመቱ ሁለተኛ ጨዋታ ነገ ረቡዕ ከአመሻሹ 11:30 በአዲስ አበባ ስታድየም ይካሄዳል። ተጋጣሚዎቹም ደደቢት እና ወላይታ ድቻ ይሆናሉ። 

የፕሪሚየር ሊጉ አምስት ጨዋታዎች ሐሙስ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ይካሄዳሉ። የ80 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋውና ያለፈው ዓመት ሻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አዳማ ተጉዞ አዳማ ከነማን ይገጥማል። ሐዋሳ ከነማ በሜዳው ሲዳማ ቡናን ያስተናግዳል። የአዲስ አበባ ከተማን ዋንጫ ያነሳው ዳሽን ቢራ በሜዳው አጼ ፋሲል ስታድየም የመሠረት ማኒውን ድሬዳዋ ከነማን ያስተናግዳል።

አሠልጣኝ የሌለው አርባምንጭ ከነማ ከሆስዕና ሀድያ ጋር አርባምንጭ ላይ ይጫወታል። የሳምንቱን የመጨረሻ ጨዋታ የሚያስተናግደው ሁሉን ቻዩ አዲስ አበባ ስታድየም ሲሆን ተፋላሚዎቹ ክለቦች ደግሞ በሰርቢያዊው ድራገን ፖፓዲች የሚሰለጥነው ኢትዮጵያ ቡና እና የፀጋዬ ኪዳነማርያሙ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ናቸው። 

የአገራችንን እግር ኳስ ለማሳደግ የበኩሉን እየጣረ የሚገኘው ኢትዮፉትቦል ዶትኮም እሮብ የሚደረገውን የደደቢት ከወላይታ ድቻ  እንዲሁም  ሐሙስ   አመሻሽ ላይ ኢትዮጵያ ቡና ከንግድ ባንክ የሚያካሂዱትን ጨዋታ በቀጥታ ውጤት ስርጭት  LIVESCORE  የሚያስተላልፍ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!