ኤሌክትሪክ እና ደደቢት የውድድር ዓመቱን በድል ጀመሩ
ጥቅምት 17, 2008

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2008 ዓ.ም ውድድር ዛሬ ከቀትር በኋላ በተካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ተጀምሯል። የሊጉን ውድድር የከፈቱት ኮረንቲዎቹ እና መከላከያ ሲሆኑ ናይጀሪያዊው ፒተር ኦኮቾኮ ደግሞ የውደድር ዓመቱን የመክፈቻውን ጎል አስቆጥሯል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ለተመልካች አዝናኝ ካለመሆኑም በላይ ከግብ ሙከራ ይልቅ በርካታ ቢጫ ካርዶች የተመዘዙበት ነበር። ኢንተርናሽናል  አልቢትር ሀይለየሱስ ከመዘዟቸው ሰባት ቢጫ ካርዶች ኮረንቲዎቹ አምስቱን በመውሰድ ገና በውድድር ዓመቱ መባቻ የአምስት ሺህ ብር ቅጣት ይደርስባቸዋል። 

ከመከላከያ እና ኤሌክትሪክ ቀጥሎ የተገናኙት ደደቢት እና ወላይታ ድቻ ሲሆኑ ባለሜዳው ደደቢት አማካዩ ሳምሶን ጥላሁን በቅጣት ምት እና አጥቂው ሳሙኤል ሳኑሚ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ሁለት ጎሎች ሁለት ለአንድ ማሸነፍ ችሏል። የወላይታ ድቻን ብቸኛ ጎል ያስቆጠረው አማካዩ አልቢትር ብርሀኑ ነው። ጎሏ የተቆጠረችውም በፍጹም ቅጣት ምት ነው። 

ፕሪሚየር ሊጉ ነገም ቀጥሎ የሚካሄድ ይሆናል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
henoke [778 days ago.]
 youare very good work keep it up

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!