የፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት የመሪነት ርካቡን ለአዳማ ከነማ አስጨብጧል
ጥቅምት 18, 2008

በይርጋ አበበ

የዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ትናንትና እና ዛሬ በተካሄዱ ሰባት ጨዋታዎች ተጀምሯል። ትናንትና በአዲስ አበባ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደው ኤሌክትሪክንና ደደቢትን በድል ሲያስጀምር ዛሬ በተካሄዱ አምስት ጨዋታዎች ደግሞ አዳማ ከነማ በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ የሁለት ለባዶ ድል በማጎናጸፍ የሊጉን መሪነት አስጨብጦታል። የስምጥ ሸለቆው ክለብ በፈረሰኞቹ ላይ የበላይነቱን እንዲያጎናጽፍ ያደረጉትን ሁለት ጎሎች ያስቆጠረው ሚልኪያስ ወንድወሰን ነው። 
CBE Coach

ጎንደር ላይ የተካሔደውን የዳሽን ቢራ እና ድሬዳዋ ከነማ ጨዋታ ይተሻ ግዛው በ92ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል በዳሽን ቢራ አሸናፊነት ተጠናቋል። አርባምንጭ ከነማ በበኩሉ ሆሳዕና ሀድያን አንድ ለባዶ ሲያሸንፍ ጎሏን ያስቆጠረው ደግሞ አጥቂው ተሾመ ታደሰ ነው። በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ ፈጣኗን ጎል ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ቡናው ያቡን ዊሊያም ክለቡ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ የአንድ ለባዶ ድል እንዲቀዳጅ አስችሎታል። 

በሳምንቱ ከተካሄዱ ሰባት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት የተጠናቀቀው አንድ ጨዋታ ሲሆን እሱም ሐዋሳ ከነማ እና ሲዳማ ቡና ያካሄዱት ጨዋታ ነው። ጨዋታው የተጠናቀቀው አንድ እኩል ሲሆን ለባለሜዳው ሐዋሳ ከነማ በረከት ይሳቅ ሲያስቆጥር ለእንግዳው ቡድን አንዷለም ንጉሴ ፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል። 
ጨዋታዎቹን በተመለከተ ዝርዝር ዘገባ በነገው ዝግጅታችን እናቀርባለን።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!