አርባምንጭ ከነማ እና ሆሳዕና ሀድያ ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈረሙ
ጥቅምት 20, 2008

በይርጋ አበበ

ፕሪሚየር ሊጉን ያለ አሠልጣኝ የጀመረውና በሊጉ የመክፈቻ ጨዋታው ሀድያ ሆሳዕናን አንድ ለባዶ ያሸነፈው አርባ ምንጭ ከነማ አሠልጣኝ የቀጠረ ሲሆን ቡድኑን ለማጠናከርም ሁለት ተጫዋቾችን ማሥፈረሙን የኢትዮፉትቦል ዶትኮም ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን ያደረሱን መረጃ አስታወቀ። አርባ ምንጭ ከነማ የቀጠረው አዲስ አሰልጣኝ ጳውሎስ ተስፋዬ ናቸው። አሠልጣኝ ጳውሎስ ከዚህ ቀደም ሱሉልታ ከነማ፣ ለገጣፎ ከነማ እና ጂንካ ከነማን አሠልጥነዋል። ክለቡ ከአሠልጣኝ ጳውሎስ በተጨማሪ ሁለት አጥቂዎችንም አስፈርሟል። የአርባ ምንጭ ከነማ አዲስ ፈራሚዎች የቀድሞው የወልድያ ከነማው አብይ በየነ እና ናይጄሪያዊው ሞሊስ ኦኮቾ ናቸው። 

በሌላ ዜና በዚህ ዓመት ፕሪሚየር ሊጉን የተቀላቀለው ሆሳዕና ሀድያ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል። ሆሳዕና ያስፈረማቸው ሁለት ተጫዋቾች የቀድሞው የአዳማ ከነማ አጥቂ አሸናፊ ይታየው እና የንግድ ባንኩ ሀኪም ኦኬንዳ ናቸው።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
ፏፏቴያችን [843 days ago.]
 blease update z league table and standing uptodate...dhank u

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!