በሊጉ ሁለተኛ ሳምንት መርሃ ግብር፦
ጥቅምት 22, 2008

በይርጋ አበበ

-      አዳማ ከነማ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ

-       ኢትዮጵያ ቡና በሽንፈት ሲያጠናቅቅ ንግድ ባንክ በጎል ድርቅ እንደተመታ ቀጥሏል

 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲየም እና በአዳማው አበበ ቢቂላ ስታዲየም ተካሂዶ ቀጥሎ ውሏል። ሊጉ ትናንት አዲስ አበባ ላይ ሲካሄድ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ የተገናኙት ደደቢት እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲሆኑ ውጤቱም ቀደም ሲል በኢትዮፉትቦል ዶትኮም በቀጥታ የጽሁፍ ስርጭት እንደተገለጸው ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል። ውጤቱን ተከትሎ ደደቢት ሊጉን ለሰባት ደቂቃ መምራት ሲችል ከሰባት ደቂቃ በኋላ አደዳማ ላይ ኤሌክትሪክን ሁለት ለባዶ ያሸነፈው አዳማ ከነማ ጨዋታ በመጠናቀቁ የመሪነት ርካቡን አዳማ ከነማ ተረከበ። ንግድ ባነክ ደግሞ 180 ደቂቃ ጎል ያላስቆጠረበትን ውጤት አስመዝግቧል።

አዳማ ላይ የተካሄደው የአዳማ ከነማ እና ኢትዮኤሌክትሪክ ጨዋታ በአዳማ ከነማ ሁለት ለባደ አሸናፊነት ተጠናቋል። አዳማ ከነማ በተከታታይ ሁለት ጨዋታዎችን በሜዳው አካሂዶ ሁለቱንም ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሁለት ለባዶ አሸንፏል። ትናንት ባለፈው ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት ለባዶ ሲያሸንፍ የማሸነፊያዎቹን ጎሎች ወንዶሰን ሚልኪያስ ማስቆጠሩ የሚታወስ ሲሆን ትናንት ኤሌክትሪክን በተመሳሳይ የጎል ልዩነት ሲያሸንፍ ለአዳማ የማሸነፊያዎቹን ሁለት ጎሎች ያስቆጠረው የቀድሞው የኤሌክትሪክ አጥቂ ታፈሰ ተስፋዬ ነው። ውጤቱን ተከትሎ አዳማ ከነማ ሊጉን በስድስት ነጥብ እና በአራት ተጨማሪ ጎል ሲመራ አጥቂዎቹ ታፈሰ ተስፋዬ እና ወንዶሰን ሚልክያስ ደግሞ በሁለት ጎሎች የሊጉን ከፍተኛ ጎል አግቢነት እየመሩ ይገኛሉ።

ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲየም ከአመሻሹ 11 ፡30 የተካሄደው የመከላከያ እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ በመከላከያ አንድ ለባዶ አሸናፊነት ተጠናቋል። መከላከያ ያሸነፈባትን ብቸኛ ጎል ያስቆጠረው የቀድሞው የቡና አጥቂ ሳሙኤል ታዬ ወይም ልምሻ ነው። ሳሙኤል ጎሏን ያስቆጠረው የቡናዎቹ ተካላካዮች የጎል መስመራቸውን ነቅተው መጠበቅ ባለመቻላቸው በተፈጠረ ስህተት ነው። ከጎሏ ቀደም ብሎም ቢሆን የቡናዎቹ ተከላካዮች የተጣለባቸውን አደራ በንቃት መጠበቅ ተስኗቸው የታዩ ሲሆን ድክመታቸውን የጋረደላቸው ግብ ጠባቂው ኮኢሶ ሀሪስተን ነው። ቤኒናዊው ግብ ጠባቂ በትናንቱ ጨዋታ መከላከያ በሰፊ የጎል ልዩነት ማሸነፍ የሚችልበትን እድል እንዳይጠቀም ያደረገ ሆኖ በማምሸት ለክለቡ ለቡና ውለታን ሰርቶ አምሽቷል።

የሁለቱ ክለቦች አሰልጣኞች ከጨዋታው በኋላ ለጋዜጠኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የመከላከያው ገብረመድህን ሀይሌ ቡድኔ ከሽንፈት የመጣ በመሆኑ ቡናን አሸንፈን ወደ አሸናፊነታችን ለመመለስ በመቻሉ ደስተኛ ነኝ ያለ ሲሆን የቡናው ግራጋን ፖፓዲች በበኩላቸው ከጨዋታው ቀደም ብዬ መከላካያዎች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ስለተሸነፉ ዛሬ በእኛ ላይ ሊበረቱ እንደሚችሉ ነግሬያቸው ነበር ሲሉ ተናግረዋል። አያይዘውም ቡድናቸው ጥሩ መጫወት ቢችልም የጎሉን መስመር የሚያውቅ አጥቂ በማጣታቸው እንደተሸነፉ ተናግረው በሴካፋ ውድድር ለቡድናቸው ጠቃሚ የሚሆን ተጫዋች ካገኙም ለማስፈረም ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ቡና በትናነት ጨዋታ የመስዑድ መሀመድ በጉዳት ከጨዋታ ውጭ በመሆኑ የመሃል ሜዳው ተበልጦ ታይቷል። መከላከያ በበኩሉ የአጥቂ መስመሩ በርካታ ኳሶችን ለማባከን የተዘጋጀ አስመስሎታል። በተለይ መሀመድ ናስር በሙሉ ብቃቱ ላይ አለመገኘቱ እና ባዬ ገዛኸኝም ከአዲሱ ክለቡ ጋር መዋሃድ አለመቻሉ መከላከያን በጉዳት ላይ ያለው ሙሉዓለም ጥላሁንን በጊዜ መመለስ እንዲጠብቅ አስገድዶታል።

ፕሪሚየርጉ ዛሬም ቀጥሎ የሚውል ሲሆን ድሬዳዋ ላይ ድሬዳዋ ከነማ ሀዋሳ ከነማን፣ ቦዲቲ ላይ ወላይታ ድቻ ጎረቤቱን አርባምንጭ ከነማን እና ሆሳዕና ላይ ሆሳዕና ሀድያ ዳሽን ቢራን በተመሳሳይ ዘጠኝ ሰዓት ያስተናግዳሉ። የሊጉ ሁለተኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር የሚሆነው ከምሽቱ 11፡30 ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚካሄደው የፈረሰኞቹ እና የሲዳማ ቡና ጨዋታ ነው። የፈረሰኞቹ እና የሲዳማ ቡና ጨዋታ የሳምንቱ የመጨረሻ ጨዋታ ብቻ ሳይሆን ለ40 ቀናት ለሚቋረጠው ፕሪሚየር ሊግ ውድድርም የመጨረሻ ጨዋታ ይሆናል። ኢትዮጵያ የሴካፋን ዋንጫ ማዘጋጀቷን ተከትሎ ፕሪሚየር ሊጉ ለመጭዎቹ 40 ቀናት የማይካሄድ ይሆናል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Dani man [810 days ago.]
 ህልምሽ ሆኖ ቢቀር የሊጉ ዋንጫ እንደምነሽ ቡንዬ የማንም መፈንጫ ሃሃሃሃሃሃሃሃ በጣም ደስ ብሎኛል ትላንትና መከላከያ አስደስቶኛል:: ጎሉ ግን አነሰ በትንሹ 3 ለ 0 ማለቅ ነበረበት ! አይ ቡና ገለባ እውነትም አደገኛ ሃሃሃሃሃሃሃ ግን አደገኛነታችሁ ድንጋይ ውርወራ .... ስድብ .... ባስ መስበር ነው !

jaimibarca [810 days ago.]
 ህልምሽ ሆኖ ቢቀር የሊጉ ዋንጫ እንደምነሽ ቡንዬ የማንም መፈንጫ ሃሃሃሃሃሃሃሃ wooooooooow i like this poem tnx dani man.

Mamush [810 days ago.]
 ዘንድሮ ቡና ስንተኛ ደረጃ ላይ ሆኖ እንደሚጨርስ ማየት ነው የጓጓሁት ጃል ሜዳ የሚወርድ አይመስላችሁም ከፈረንጁ ጋር ?!

Samuel Bezabeh [810 days ago.]
 ቡና ገለባዎች ከጨዋታው በሃላ በሰጡት ፕሬስ ኮንፍረንስ ላይ ለሽንፈታቸው ምክንያት ፈረንጁ አሰልጣኝ ፀሎት ሳያደርግ መውጣቱ መሆኑን ቀጣይ ጨዋታ ላይ ግን ያ እንደማይደገም ተናግረዋል

Mele [810 days ago.]
 ማፈሪያዎች ናችሁ በፔናሊቲ ጊዮርጊስን አሸንፋችሁ ልክ አለም ዋንጫ እንዳሸነፈ ቡድን ከተማውን ረበሻችሁ ለዋንጫ ግን በዳሽን ቢራ ነስር በነስር ሆናችሁ ሃሃሃሃ ብትሸነፉም ፌዴሬሽኑ ዋንጫ ብርቁ መሆናችሁን ተመልክቶ ዋንጫውን ሰጣችሁ

yisak tomas [810 days ago.]
 ወይ ደቡቦች ዘንድሮስ እናንተ ማን ይቻላቹ በተለየ አርባ ምንጭ

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!