ፈረሰኞቹ የሳምንቱን ከፍተኛ ጎል በማስቆጠር አሸነፉ
ጥቅምት 22, 2008

ዛሬ ከሰዓታት በፊት በተጠናቀቀው አንድ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲዳማ ቡናን አምስት ለአንድ አሸንፏል። ፈረሰኞቹ አሸናፊ የሆኑባቸውን ጎሎች ያስቆጠሩት ምንያህል ተሾመ፣ ብሪያን አሙኒ፣ አዳነ ግርማ እና ራምኬል ሎክ ናቸው። ለሲዳማ ቡና ደግሞ የቀደሞው ፈረሰኛ አንዷለም ንጉሴ አቤጋ ነው።
St.George Vs Sidama Buna


ፈረሰኞቹ ላስቆጠሯቸው በርካታ ጎሎች የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ ደካማ መሆን  አስተዋጽዎ አድርጓል። ከአምስቱ ሶስቱ ጎሎች ከርቀት ተመተው የገቡ ምርጥ ጎሎች ናቸው።  የመጀመሪያውን ጎል በ13ኛው ደቂቃ ላይ ምንያህል ተሾመ ከርቀት በረኛው መውጣቱን አይቶ በሰማይ የላካት ኳስ በረኛውን አልፋ  መረቡ ላይ ከማረፍ ሌላ አማራጭ አልነበራትም። ምንያህል ተሾመ ጨዋታ እያነበበ የሚጫወት በሳል ተጫዋች መሆኑን ያሳየበት ምርጥ ጎል ነበር። አዳነ ግርማ በ33ኛው እንዲሁም ራምኬሎ በ37ኛው ደቂቃ ያስቆጠሩዋቸው ጎሎች እንደዚሁ ከርቀት ተመተው የገቡ ምርጥ ጎሎች ነበሩ።  ብሪያን በ16ኛው ደቂቃ ላይ ከጎን የተሻገረለትን ኳስ በግምባር  ገጭቶ ጠባብ አንግል ላይ የሰካት ኳስ በረኛውን እጅ ጥሳ ከመረብ ያረፈች ሌላዋ የፈረሰኞቹን ድል ያደመቀች ምርጥ ጎል ነበረች። 

St.George Vs Sidama Buna

በጨዋታው 31ኛ ደቂቃ ላይ ሲዳማ ቡናዎች በጊዮርጊስ የፍጹም ቅጣት ግብ ክልል    ውስጥ ኳስ በእጅ ተነክቷል የፍጹም ቅጣት ምት ይገባናል ብለው ቢከራከሩም ዳኛው አላመኑበትም። የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ አንድ ደቂቃ ሲቀር ሲዳማ ቡናዎች የናፈቁትን የፍጹም ቅጣት ምት አግኝተው በቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች አንድዋለም ንጉሴ አማካኝነት ለቡድኑ ማስተዛዘኛ የሆነችውን ጎል ማስቆጠር ችለዋል።

ከረፍት መልስ ሲዳማ ቡናዎች አጥቅተው ቢጫወቱም የቅዱስ ጊዮርጊስን መረብ መድፈር አልቻሉም። በተቃራኒው ከረፍት መልስ ብዙም የማጥቃት እንቅስቃሴ ያላሳዩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በባከነ ሰአት  በመልሶ ማጥቃት ጨዋታ አዳነ ግርማ ከግራ በኩል ወደጎል ያሻማትን ኳስ ብርያን አግኝቷት ወደጎል ለመቀየር ሲታገል በመጠለፉ የፍጹም ቅጣት ምት ለቅዱስ ጊዮርጊስ በመሰጠቱ አዳነ ግርማ ለራሱ  ሁለተኛውን ለቡድኑ አምስተኛውን ጎል በማስቆጠር ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ የበላይነት ሊጠናቀቅ ችሏል።


በዛሬው ጨዋታ የሲዳማ ቡናውን የግብ ጠባቂ የወረደ ብቃት የተመለከተ ታላላቆቹ ክለቦች ግብ ጠባቂዎቻቸውን ለምን ከውጭ አገር እንደቀጠሩ ለመገንዘብ አያዳግተውም። 

የኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ ደርዘን ሙሉ ጊዜ በመቀዳጀት ቀዳሚ የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ እግርኳስ ክለብ በዘንድሮው የፕሪሚየር ሊግ ውድድር የመክፈቻ ጨዋታውን በአዳማ ከነማ የሁለት ለባዶ ሽንፈት አስተናግዶ ነበር። ሆኖም ዛሬ በሲዳማ ቡና ላይ የተጎናፀፈው ድል ከነበረበት የመጨረሻ ደረጃ ወደ መሪዎቹ ተጠግቷል። 

ፈረሰኞቹ ባለፈው ዓመት ሲዳማ ቡናን በሜዳቸውም ከሜዳቸው ውጭም በተመሳሳይ ሁለት ለባዶ በሆነ ውጤት ነበር ማሸነፍ የቻሉት። 

በሌሎች ጨዋታዎች ድሬዳዋ ከነማ ከሐዋሳ ከነማ አንድ እኩል ሲለያዩ ዳሽን ቢራ ሀድያ ሆሳዕናን፤ ወላይታ ድቻ ደግሞ አርባምንጭ ከነማን በተመሳሳይ አንድ ለባዶ አሸንፈዋል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Yoni Sanjawe [842 days ago.]
 @ ኳስ መቼ ነው ግን የምታምኑት የቡላ ገለባ ደጋፊዎች ? ሁልጊዜ ለሽንፈታችሁ ምክንያት መደርደር {በዳኛ} {በሳሩ} {በፌዴሬሽኑ} {በዝናቡ} {በፀሃዩ} እንዳሳበባችሁ ነው መቼ ነው ውስጣችሁን የምትመለከቱት ???????? መቼ ነው የቤት ስራችሁን የምትሰሩት ???????? መቼ ነው ጊዮርጊስን መፍራት የምታቆሙት ?????????? መቼ ነው ገና ማሊያውን ስታዩ ሽንታችሁን መሽናት የምታቆሙት ?????????? መቼ ነው {ወሬ} {አልቧልታ } {ስድብ} {ድንጋይ ውርወራ} አቁማችሁ እውነተኛ የጊዮርጊስ ተፎካካሪ የምትሆኑት ?????!!!!!!! ዘንድሮ ዋንጫ እንበላለን ብላችሁ አስባችሁ ኖሯል ሃሃሃሃሃሃ ዘንድሮ ከፈረንጁ ጋር ተያይዛችሁ ጃል ሜዳ ነው የምትወርዱት !!!!!! ማፈሪያዎች ናችሁ በ 13 ዓመት አንድ ጊዜ ዋንጫ እየበላችሁ የጊዮርጊስ ተፎካካሪ ነን ስትሉ ! ቅዱስ ጊዮርጊስ ይከብዳቹሃል 12 ጊዜ ሻምፒዮንንንንንንንንንንንንንንንን !!!! ይከብዳቹሃልልልልልልልል ይልቅ ክላሳችሁን ፈልጉ የቡና ገለባ ክላስ ከኒያላ .... ከወንጂ .... ከጉና ጋር ነው ! Respect St.George fc Ethiopian Foot Ball Ambassador !!! VVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVV

Samuel Bezabeh [842 days ago.]
 ቡላ ገለባ ወሬ ከነማ ዘንድሮ ይወርዳል ጊዮርጊስ አንበሳው ለ 13 ኛ ጊዜ ሻምፒዮን ይሆናል !

Sirak [841 days ago.]
 እኛ ሀገር ኢህአድግ ምርጫ ጊዬርጊስ ዋንጫ እንደሚያሸንፉ ቀድሞ ይታወቃል፥

Yoni Sanjawe [841 days ago.]
 ቡና ማለት የሴት እድር የሆነ ወረኛ ሰበበኛ ለሽንፈቱ ሁሉ ውስጡን ሳይሆን ሌሎች ላይ የሚያሳብብ በጊዮርጊስ የበላይነት ተስፋ ቆርጦ ስራ የሚሰራ ሳይሆን ተቃጥሎ እርርርርርርርርር ብሎ ስታዲየሙን በስድብ በድንጋይ ውርወራ ያመሰ ወሮ በላ ቲም ነው:: ቡና ማለት እኮ ትንሽዬ ቡድን ነው ጊዮርጊስ እንኳን ሊጉ ላይ ባይኖር ዋንጫ መብላት አትችሉም :: እስቲ መቼ ነው የጊዮርጊስ ተፎካካሪ ሆናችሁ አንገት ለ አንገት ተናንቃችሁ ጨርሳችሁ የምታውቁት ? ኧረ መቼ ? ሁልጊዜ እንደምናውቃችሁ አመቱ መጨራሻ ላይ 6 ኛ ወይም 7 ኛ ሆናችሁ ስጨርሱ ነው:: እስቲ ዝምምምምምምም በሉ የማይሰራ ሰው ሲያወራ አያምርበትም :: ወሬ እና ስራ በጣም የተላያዩ ነገሮች ናቸው :: ቡና ገለባዎች እግዛብሔር ከሰማይ ወርዶ ቢዳኛችሁም እንኳን ሽንፈታችሁን የማትቀበሉ ደረቆች ናችሁ:: የአለማችን ምርጥ ዳኛ የነበረው ጣሊያናዊው ፒዮሮሊጂ ኮሊና እሱ መጥቶ ጊዮርጊስና ቡና ገለባን 10 ጨዋታዎች ቢዳኝ እርግጠኛ ነኝ 9 ጊዜ እናሸንፋቹሃለን ምክንያቱም እናውቃቹሃለና ፈሳሞች ናችሁ ገና የሳንጃውን ማሊያ ስታዩ ነው ወኔያቹን የምትሸኑት ! እንደ ሰማይ የራቀሽ የፕሪም የር ሊጉ ዋንጫ እንዴት ነሽ ቡንዬ የማንም መፈንጫ ሃሃሃሃሃሃሃ ዘንድሮ ትወርዳላችሁ ሃሃሃሃሃ

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!