አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረበ
ጥቅምት 23, 2008


በይርጋ አበበ

የዋልያዎቹ አሠልጣኝ ኢንስትራክተር ዮሐንስ ለ23 ተጫዋቾች አገራዊ ጥሪ አቀረበ። ከኢትዮጵያ እግር ኳስ  ፌዴሬሽን የህዝብ ግንነት ክፍል በደረሰን መረጃ ለማወቅ እንደቻልነው አሠልጣኝ ዮሐንስ በአዲሱ ስብስቡ አዳዲስ ተጫዋቾችንም ጥሪ አቅርቧል። ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ነገ ጥቅምት 24 ቀን ካፒታል ሆቴል በመገኘት ሪፖርት ማድረግ አለባቸው ተብሏል። 

በአሰልጣኝ ዮሐንስ የብሔራዊ ቡድን ጥሪ ከቀረበላቸው ተጫዋቾች መካከል የመከላከያዎቹ ይድነቃቸው ኪዳኔ፣ አዲሱ ተስፋዬ እና በሀይሉ ግርማ ይገኙበታል። 
የዳሽን ቢራው ተከላካይ ያሬድ ባየህ፣ የድሬዳዋ ከነማው ይሁን አለባቸው እና የአዳማ ከነማው ታከለ አለማየሁ የዮሐንስ ሳህሌን ስብስብ ተቀላቅለዋል።

በአንጻሩ የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ ለዓለም ብርሀኑ፣ የንግድ ባንኩ ኤፍሬም አሻሞ፣ የመከላከያው ፍሬው ሰለሞን እና የሐዋሳ ከነማው ሙጂብ ቃሲም ከስብስቡ ተቀንሰዋል። 

ሙሉ የቡድኑ ዝርዝር 

ግብ ጠባቂዎች፦ አቤል ማሞ፣ ታሪክ ጌትነት እና ይድነቃቸው ኪዳኔ


ተከላካዮች፦ ስዩም ተስፋዬ፣ ነጂብ ሳኒ፣ ሳላዲን ባርጌቾ፣ አስቻለው ታመነ፣ ያሬድ ባየህ፣ አንተነህ ተስፋዬ፣ ዘካሪያስ ቱጂ እና አዲሱ ተስፋዬ ናቸው። 


አማካዮች፦ በሀይሉ ግርማ፣ ጋቶች ፓኖም፣ ኤልያስ ማሞ፣ ቢኒያም በላይ፣ ታከለ ዓለማየሁ፣ አስቻለው ግርማ እና ቢኒያም በላይ ሲሆኑ በፊት መስመሩ ደግሞ ራምኬል ሎክ፣ ዳዊት ፈቃዱ፣ በረከት ይሳቅ፣ መሀመድ ናስር፣ ምንይሉ ወንድሙ እና ይሁን እንደሻው ናቸው።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Zele [808 days ago.]
 ድንቄም ኢንስትራክተር ሃሃሃሃ እናየዋለን እኮ በሴካፋ ሃገሮች በገዛ ሜዳው ሲያሰድበን ሲያስቀልድብን

Gizegeta [808 days ago.]
 እስቲ ደግሙ ግትሩ የዋልያው ኮች ምን አይነት በድን ይቅርታ ቡድን ማለቴ ነው ምን አይነት ቡድን ሰርቶ እንደሚያሳፍረን እንደሚያሳቅቀን ለማየት ጓጉቻለሁ.......

felexsami [808 days ago.]
 መመረጥ የሚገባቸውን ልጆች አሁንም ዘለላቸው አይደል የስራህን ይስጥህ ዮሃንስ :: በጣም የሚገርመኝ ቆይ ሰውዬው ቡድኑን ከያዘ ስንት ጊዜ ሆነው ? በየጊዜው የተለያዩ ተጫዋቾችን ይጠራል.... ያባርራል !.... ይጠራል ......ያባርራል ! ይጠራል ...... ያባርራል ! ይጠራል ..... ያባርራል ! ይጠራል ........ ያባርራል ! ምንድነው አላማው ይህ ሰውዬ ቡድኑ እስከዛሬ ድረስ ቋሚ 11 ተጫዋቾች የሉትም

Abugella [808 days ago.]
 በሃይሉ አሰፋ , ምንተስኖት, ናቲ, ተስፋዬ, ባዬ ገዛሃኝ እነዚህ ልጆች ከማን አንሰው ነው ያልተመረጡት ???? ኧረ ኢትዮ ስፖርት ጠይቁልን በምን መስፈርት ነው ይሄ ሰውሄዬ ተጫዋቾችን የሚመርጠው ?

Alex, from west gojjam, [804 days ago.]
 Ye selhadin seyid ena omed dikuri alemeselef betam yebudnun akuam endiwerd yadergewal, enezih techawachoch aydelem le ethio lelela yemihonu nachew, omed mechawet yalebet degmo ke attaker behuala, tederabi attaker new mehon yalebet, ahun yalew ye club akuam astemamagn yimeslachihual???

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!