ኢትዮጵያ ቡና እና ሀበሻ ሲሚንቶ ለአምስት ዓመታት ሊጣመሩ ተማማሉ
ጥቅምት 23, 2008


በይርጋ አበበ

ኢትዮጵያ ቡና ለመጭዎቹ አምስት ዓመታት ከሀበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ ጋር አብሮ የሚሰራበትን ስምምነት ዛሬ ቸፈራረመ። የሁለቱ ወገኖች ስምምነት ለመጭዎቹ አምስት ዓመታት የጸና ይሆናል ያሉት የቡናው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ናቸው። የሐበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ ዋና ስራአስኪያጅ ኢንጅነር መስፍን አቢ በበኩላቸው የበርካታ ደጋፊ ባለቤት ከሆነውና ህዝባዊው ኢትዮጵያ ቡና ጋር አብረን ለመስራት ስምምነት ላይ በመድረሳችን ደስተኛ ነን ብለዋል። 

ሀበሻ ሲሚንቶ የሀበሻ ቢራ እህት ኩባንያ በመሆኑ አሁን ቡና እና ሀበሻ ሲሚንቶ የደረሱበት ስምምነት ቀሀበሻ ቢራ ላይ ምንም አይነት አሉታዊ ተጽዕኖ አይፈጥርም ብለዋል። 
ገና ወደ ምርት ያልገባው ሀበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ ከዚህ ወር ጀምሮ ለመጭዎቹ አስር ወራት ሁለት ሚሊዮን ብር ለቡና የሚከፍል ሲሆን ፋብሪካው ወደ ምርት ሲገባ ደግሞ የገንዘቡ መጠን ይጨምራል ተብሏል። 

ፕሪሚየር ሊጉ ከ40 ቀናት እረፍት በኇላ መካሄድ ሲጀምር ኢትዮጵያ ቡና የሀበሻ ሲሚንቶ ማስታወቂያ የተለጠፈበት ማልያ ለብሶ የሚገባ ይሆናል። የሀበሻ ሲሚንቶ ምልክት በክለቡ ማልያ ላይ የሚለጠፈው ከማልያው ቀኝ ደረት ላይ ይሆናል። የክለቡ አምበል መስዑድ መሀመድ የሀበሻ ሲሚንቶ አርማ ያረፈበትን ማልያ አስተዋውቇል። 
በስምምነቱ ዙሪያ ዝርዝር መረጃዎችን በነገው ዝግጅታችን ይዘን እንመለሳለን።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Mamush [773 days ago.]
 እቺ የኔም ጥያቄ ነበረች tnx Jaimibarca መ. ይወርዳል ጃልሜዳ ነው መልሱ

YoniSanjawe [772 days ago.]
 በመጀመሪያ እንደ አንተ አይነቱ ባለጌ ስድ ጋጠወጥ አይነቱ የቡላ ገለባ ደጋፊ የአብነትን ስም የመጥራት ሞራል የለውም:: ቡላ ገለባ ክለብ እንደ አብነት አይነት በሳል የስፖርት አመራር ስለሌላችሁ ዘወትር በቅናት ቅጥል እርርርርርርርር እንደምትሉ ማንም የሚያውቀው ሀቅ ነው:: የቡላ ገለባ አመራሮችን ብናያቸው 100 አለቃ ፥ 50 አለቃ፥ 70 አለቃ ናቸው:: እነዚህ ሰዎች ደግሞ እንኳን ቡላ ገለባ ክለብን ሊያስተዳድሩ ሊመሩ ቤተሰቦቻቸውን እንኳን በአግባቡ መምራት የሚችሉ ሰዎች አይደሉም:: ለዛም እኮ ነው የናንተ ክለብ በየአመቱ ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ የምትሉት... የምትባሉት.... የምትጨራረሱት:: መቼ ነው ሰላም ኖሯቹ የሚያውቀው ???!!! ደጋፊው ... አመራሩ .... ተጫዋቹ ....ባለጌ ፍንዳታ በጣም የሚገርመውና የሚያሳዝነው ቡላ ገለባ የተባለን ክለብ ለመደገፍ መስፈርቱ ክራይቴርያው ባለጌ መሆን ፥ መሳደብ ፥ ድንጋይ መወርወር ፥ መፈንዳት ፥ እናትና አባትን አለማክበር ነው እንዴ ??? በመጨረሻም እኛ ኳስ እንጫወታለን ላልከው ኳስ ማለት ሰርከስ ወይም መሃል ባልገባ ማለት አይደለም:: ኳስ ጨዋታ ማለት በኳሱ መሃል ሜዳ ላይ ሰርከስ መስራት ማለት አይደለም :: ወደፊት ሄዶ ጎል ማስቆጠርና ማሸነፍ ማለት ነው:: ቡላ ገለባ ግን ይሄን ማድረግ ሲያቅታችሁ ዘወትር ኳስ ተጫውተን ነው የተሸነፍነው እያላችሁ ዲስኩር ትነፋላችሁ:: መጫወት ማለት ምን ማለት ነው ወደፊት ሄዶ ጎል ማስቆጠር ማለት አይደለም እንዴ ? ካልሆነ በቃ ቡድናችሁን የሰርከስ ቲም አድርጉት ምክንያቱም ትጫወታላችሁ ግን የጎሉን አቅጣጫ ስለማታውቁት ::

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!