የኢትዮጵያ ቡና እና የሀበሻ ሲሚንቶ የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት እና አንዳንድ ነጥቦች
ጥቅምት 24, 2008

-         ፋብሪካው በቀጣዮቹ አስር ወራት ለክለቡ ሁለት ሚሊዮን ብር ይከፍላል

-         የሀበሻ ቢራ የስፖንሰር ሺፕ ገንዘብ ከመጪው ጥር ጀምሮ ማሻሻያ ይደረግበታል 

በይርጋ አበበ

የሀበሻ ቢራ አክሲዮን ማህበር እህት ኩባንያ የሆነው ሀበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በጣምራ ለመስራት ከክለቡ ጋር መፈራረሙን በትናንት ምሽቱ ዘገባችን ማስነበባችን ይታወሳል። በሁለቱ ወገኖች ስምምነት መሰረትም ፋብሪካው ከክለቡ ጋር ለመጪዎቹ አምስት ዓመታት የክለቡ የማሊያ ላይ ስፖንሰር ሲሆን ክለቡ በበኩሉ በተጫዋቾች ማልያ የቀኝ ደረት ላይ የፋብሪካውን ምልክት ይለጥፋል። ስምምነቱን የፈረሙት በኢትዮጵያ ቡና በኩል የክለቡ ስራ አስኪያጅ እና የቦርድ ጸሃፊ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ እና በሀበሻ ሲሚንቶ በኩል ደግሞ የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር መስፍን አቢ ናቸው።

Ethiopia Coffee Signed Sponsorship Agreement with Habesha Cement


ከስምምነቱ በኋላ በሁለቱም ወገኖች አጠር ያለ መግለጫ ከተሰጠ በኋላ መድረኩን ለጋዜጠኞች ጥያቄ የከፈቱት አቶ ገዛኸኝ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችም መልስ ሰጥተዋል። ሁለቱን ወገኖች ተጠቃሚ የሚያደርግ a win–win deal ስምምነት መሆኑን የገለጹት አቶ ገዛኸኝ ወልዴ የስምምነት ሰነዱ አምስት ክፍሎች አሉት ብለዋል። በውሉ ስምምነት መሰረትም ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ የሚታሰብና በመጪው ሰኔ 30 በሚጠናቀቅ ውል ሲሚንቶ ፋብሪካው ለቡና ሁለት ሚሊዮን ብር ይከፍላል። ይህም በወር 200 ሺህ ብር ማለት ነው። ሲሚንቶ ፋብሪካው ገና ምርት ያልጀመረ በመሆኑ በዚህ ዓመት የመጨረሻ ወራት ላይ ምርት እንደሚጀምር ታሳቢ የሚያደርግ ፋብሪካ መሆኑን የገለጹት የቡናው ስራ አስኪያጅ “በሚያዝያ ወር መጨረሻ ላይ በምናደርገው ድርድር ፋብሪካው ክለባችንን ስፖንሰር የሚያደርግበትን የዋጋ ዝርዝር እንከልሰዋለን። ከአሁኑ የተሻለ ገንዘብም እንደሚከፍል እናምናለን” ብለዋል። ሀበሻ ቢራ እና ሀበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር እህት ኩባንያ በመሆናቸው በሁለቱ ተቋማት መካከል ቡናን ስፖንሰር በማድረግ የሚደረግ ፉክክርም ሆነ የልዩ ፍላጎት ጥያቄ ወይም Conflict of Interest አይኖርም ሲሉ ተናግረዋል።

የበሀሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር መስፍን አቢ በበኩላቸው ኩባንያቸው በአሁኑ ሰዓት ምርት እያመረተ አለመሆኑን ገልጸው ነገር ግን ወደ ፊት ምርት ማምረት ከመጀመሩ በፊት ለህዝቡ አስተዋውቆ መቅረብ ስላለበት ከቡና ጋር ለመስራት መወሰናቸውን ታግረዋል። ኢትዮጵያ ቡናን በልዩነት የመረጡበትን ምክንያት ያስቀመጡት ኢንጅነር መስፍን “ሀበሻ ቢራ ከ13500 በላይ ኢትዮጵያዊያን ያቋቋሙት ድርጅት ነው። ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብም ህዝባዊ መሰረት ያለው ክለብ በመሆኑ ከእኛ የቢዝነስ አካሄድ ጋር የሚስማማ ሆኖ ስላገኘነው ነው። ስለዚህ ምርት ከመጀመራችን በፊት ወደ ገበያው ቶሎ ለመግባት እንደ ቡና ያለ ህዝባዊ መሰረት ካለው ክለብ ጋር አብሮ መስራት ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል” በማለት ተናግረዋል።

ከዚህ በታች ደግሞ ከጋዜጠኞች የተነሱ ጥያቄዎችን በተለይም የኢትዮፉትቦል ዶትኮም ዘጋቢ ያነሳቸውን ጥያቄዎች እና የተሰጡትን ምላሽ እናቀርባቸዋለን።

ከዓመታት በፊት ሀበሻ ቢራ ከቡና ጋር የገባው የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ገንዘቡ አነስተኛ ነው ተብሎ ሲጠየቅ “ፋብሪካው ምርት ስላልጀመረ ነው ምርት ሲጀምር የሚያደርገውን የስፖንሰር ሺፕ ገንዘብ ይጨምራል ተብሎ ነበር። አሁን ቢራ ፋብሪካው ምርት ማምረት ጀምሯልና ለክለቡ እየከፈለ ያለው የገንዘብ መጠን ተስተካክሏል ወይስ አልተስተካለም? የገንዘቡ መጠንስ ምን ያህለ ደርሷል? ከሀበሻ ሲሚንቶ ጋር የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ስትፈራረሙም ፋብሪካው ምርት ማምረት አልጀመረም። አሁን የተደረሰው ስምምነትስ ክለቡን በገዝንዘብ በኩል ምን ያህለ ተጠቃሚ ያደርገዋል? የሚሉትን ጥያቄዎች ነበር የኢትዮፉትቦል ዶትኮም ጋዜጠኛ የጠየቀው።

ጋዜጠኛው ከመጀመሪያውም ጥያቄውን ያቀረበው ለክለቡ የቦርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ እና ለክለቡ ዋና ጸኃፊ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ በመሆኑ መልስ የሰጡትም ሁለቱ የክለቡ ኃላፊዎች ናቸው። አቶ ገዛኸኝም ሆኑ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ለኢትዮፉትቦል ዶትኮም ዘጋቢው ሲመልሱ፤ ሀበሻ ቢራ ምርት ሳይጀምር ለአራት ዓመታት ከባለ አክሲዮኖች በሰበሰበው ገንዘብ ቡናን ስፖንሰር በማድረግ የቁርጥ ጊዜ አጋርነቱን አሳይቶናል። ምርት ማምረት ሲጀምር ደግሞ በውላችን መሰረት የክፍያው መጠን እንደሚስተካከል ስለተነጋገርን በቅርቡ የውይይታችንን የመጨረሻ ሀሳብ ይፋ እናደርጋለን እስከዛ ግን ትንሽ ታገሱ ሲሉ ተናግረዋል።

ሁለቱ የክለቡ ኃላፊዎች አክለውም ሀበሻ ቢራ ምርት የጀመረው በቅርቡ ቢሆንም ለኢትዮጵያ ቡና ጠንካራ አጋርነቱን እያሳየ ይገኛል። ለሰርቢያዊው አሰልጣኝ ደመወዛቸውን ጨምሮ የቤት ከራይና የመኪና ወጭን ጨምሮ ከውጭ አገር ለመጡት ተጫዋቾች ወርሃዊ ደመወዝ እየከፈለ ያለ ፋብሪካ ነው። ከዚህ በተረፈም ክለባችን ባሸነፈ ቁጥር ለተጫዋቾቹ ጉርሻ ወይም ቦነስ የሚሆን ገንዘብ እስከ አንድ ነጥም ስድስት ሚሊዮን ብር የመደበ ድርጅት ነው። ለተጫዋቾች ለጉርሻ የመደበው ገንዘብ ሲሰላም በየጨዋታው እስከ 3200 ለእያንዳንዳቸው ይደርስ ይሆናል። ከዚህ ፋብሪካ ጋር ያደረግነው የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ወደ ፊት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እናረጋግጥላችኋለን ብለዋል። ከሀበሻ ሲሚንቶ ጋር የተደረገውን ስምምነት በተመለከተም ፋብሪካው ምርት ያልጀመረ ቢሆንም ለክለቡ የሚከፍለው ገንዘብ ከባለ አክሲዮኖች የተሰበሰበ ገንዘብ በመሆኑ ወደ ፊት ምርት ሲጀምር ከዚህም በላይ የሆነ ክፍያ እንደሚፈጽም ተናግረዋል።

ከክለቡ የውስጥ ምንጭ ባገኘነው መረጃ ለማወቅ እንደቻልነው ሀበሻ ቢራ በዚህ የውድድር ዓመት ብቻ ለኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ እስከ ስድስት ሚሊዮን የሚገመት ገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
felexsami [841 days ago.]
  @ ሲራክ ታዲያ ለምን ትሳተፋላችሁ ? ወሬ አለብህ ፋጣሪ ይንቀልልህ:: ዝም ብለህ የመንደር ወሬ ኣታውራ መንደርተኝ ወረኛ መሆንህን ታስፎግራለህ

Samuel Bezabeh [841 days ago.]
 በጣም የሚገርመኝ የቡና ገለባዎች ወሬሬሬ ነው ኧረ ባካችሁ ተፋቱን ለድክመታችሁ ለሽንፈታችሁ ሁልጊዜ የቅዱስ ጊዮርጊስን ስም ማንሳት ምን ይሉታል መከላከያ እኮ ነው የቀጠቀጣችሁ ኧር ወደ ክልል ወጥታችሁ ባየናችሁ በገዛ ሜዳችሁ እንደዚህ የሆናችሁ ወጣ ስትሉማ ፫ ጎል ፬ ጎል እየቀመሳችሁ ነው የምትመጡት.....

jaimibarca [841 days ago.]
 ሽልማት የሚያስገኝ ጥያቄ ቡላ ገለባ በዘንድሮ ፕሪምየር ሊግ ላይ ስንተኛ ሆኖ ይጨርሳል ሀ. 5 ኛ ለ. 10ኛ ሐ. 9ኛ መ. ይወርዳል

Samuel Bezabeh [841 days ago.]
 መ. ይወርዳል ጃል ሜዳ

Yoni Sanjawe [841 days ago.]
 መ. ይወርዳል ጃል ሜዳ የሚወርድ ይመስለኛል

Yoni Sanjawe [841 days ago.]
 የተመዘገበ ደጋፊ ሳይኖርህ ደጋፊ ብዙ አለን ስትል አለማፈርህ ያሳፍራል የተመዘገቡና መታወቂያ ካርድ ያላቸው ወራዊ ክፍያ የሚከፍሉ የቡላ ገለባ ደጋፊዎች ቢቆጠሩ 1 ሺህ አይሞሉም ሳንጃው ጋር ብትሄድ መታወቂያ ካርድ ያላቸውና ክፍያቸውን በአግባቡ የሚከፍሉ ከ 15 ሺህ በላይ ናቸው ሌላው ነገር የቡላ ገለባ ደጋፊ በቡድኑ ዘወትር እንደተቃጠለ እንዳረረ የጨጓራ.... የደም ብዛት.... የራስ ምታት ....በሽተኛ እንደሆናችሁ ነው because you are suporting loser team !

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!