አሰልጣኙን ምን ነካቸው ?
ጥቅምት 25, 2008

ፈለቀ ደምሴ
ለኢትዮ ፉትቦል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ እግር ኳሳዊ በሆነ ቋንቋ ከጋዜጠኞች እና ከደጋፊው ጋር የተግባቡ አይመስልም፡፡ ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ አሰልጣኙ በ21-02-2008 በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በስፖርት 365 ፕሮግራም ላይ ቀርበው በሰጡት  ቃለምልል ላይ ጋዜጠኞችን በጅምላ እና በተናጠል ሲወቅሱ እና በ3 ከፋፍለው ለማሸማቀቅ ሲሞክሩ ተደምጠዋል፡፡
 
ከዚህ ቀደም አሰልጣኙ ወደመንበራቸው ሲመጡ ምንም እንኳን አመጣጣቸው አወዛጋቢ ቢሆንም የዚህ ፁሁፍ አቅራቢ ለእግር ኳሱ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ በማለት ከደገፉት ሰዎች መካከል አንዱ ነበርና ፌዴሬሽኑ የኮቺንግ ስታፍ ሊያሟሉላቸው እንደሚገባ እና በተለይ የፊዚካል እና የሳይኮሎጂ ባለሙያ እንደሚያስፈልጋቸው ሲጠይቅ በፌዴሬሽኑ በኩል አሰልጣኙ የጠየቃቸውን ለማሟላት ፈቃደኛ መሆናቸውን ሲገልጹ አሰልጣኙ ግን ባለሙያ መጥቶ በአጭር ጊዜ ለውጥ ማምጣት ስለማይቻል እኔ እውቀቱ እና ልምዱ ስላለኝ ከባልደረቦቼ ጋር እየሰራን እንወጣዋለን በማለት መልሰዋል፡፡ አሁን አሁን ግን እንደምናየው ለአሰልጣኙ ለራሳቸው የስነ-ልቦና ባለሙያ እና ከሚዲያው እና ከተመልካቹ የሚያግባባቸው አስተርጓሚ እንደሚያስፈልጋቸው ነው፡፡ ይህንንም ስል ያለበቂ ምክንያት አይደለም ከዚህ ቀደም አንድ እውቅ ያገራችን ጋዜጠኛ ለጠየቃቸው ሙያዊ ጥያቄ በቂ መልስ ስላልተሰጠው ጥያቄዬ አልተመለሰልኝም በማለት ሲጠይቅ ጋዜጣዊ መግለጫውን የጦርነት አውድማ አድርገውት ነበር ፡፡

ሙሉ ጋዜጣዊ መግለጫው ቅጂ ያለን በመሆኑ ሁሉንም ለማቅረብ ረጅም ቢሆንም አስልጣኙ ሊማሩበት ከቻሉ ግን ልናውሳቸው እንቸላለን
ቀን 28/09/2007   ቦታ ኢንተር ኮንትኔታል ሆቴል
ጠያቂ ከብስራት ስፖርት   መልስ ሰጪ አስልጣኝ ዮሃንስ ሳሕሌ
ጋዜጠኛው፡- ጥያቄዬ እየተመለሰልኝ አይደለም፡፡
ዮሐንስ፡- መስመርህን ያዝ ካልገባህ አልገባኝም በል አንተ በሚገባህ ግን አልነግርህም አንተ እግር ኳስ ተጫዋች አይደለህም፣ አላሰለጠንክም፣ አልተጫወትክም አንብበህ ነው የምትነግረኝ እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ የት ነው አንተ ኳስ የተጫወትከው፣ የት ነው ያሰለጠንከው
ጋዜጠኛው፡ - እኔ እኮ ጋዜጠኛ ነኝ መጠየቅ አለብኝ፣ መብት አለኝ
ዮሐንስ፡- ስለዚህ ነው የምትጠይቀው ጥያቄ ይቅርታ አድርግልኝ ሌሎችም አሉ
ጋዜጠኛ፡- እድሌን ስለተጠቀምኩ ጥያቄዬ መልስ ማግኘት አለበት፡፡ ግን ይቅርታ ወደ ቀጣዩ እንሂድ
ዮሐንስ፡- በጣም ጥሩ አሁን ተግባባን ግን እኔን ስትጠይቀኝ አንተ 
ጋዜጠኛ፡- እሺ በቃ ወደ ቀጣዩ ይሂዱ
ዮሐንስ፡- እንዴ ኮንትሮል አታድርግ እንጂ አንተ ጠያቂ አንተ አቁሙ እንዴት ነው ነገሩ! አቶ___ ትንሽ ስርዓት ይኑርህ እንጂ አንተ ጠያቂ አንተ አቁሙ አንተው በቃ አንተው ሂዱ አንተ ማነህ አንተ ይሄ ስርዓት ያለው አይመስለኝም አካሄድህ ስርዓት ያለው አይመስለኝም፡፡ ስርዓት ይኑርህ በስነስርዓት ጠይቅ መልሱ ካልተሰጠህ አልተሰጠኝም በል እንጂ ወዲዘህኛው ቀጥል አንተ ምንም ልትነግረኝ አትችልም እኔን፡፡
ጋዜጠኛው፡- መልሱ ስላልተሰጠኝ መጠየቅ አልችልም እንዴ?
ዮሐንስ፡- ብንከባበር ጥሩ ነው እኛ እንድናቆም አትነግረንም
ጋዜጠኛ፡- እሺ ለሌሎች እድሉ ይሰጡ

አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ቁጡ በመሆናቸው እና ጋዜጠኞች ላይ በሚያደርጉት ጫና ከዕለት ወደ ዕለት ጠንካራ ጥያቄዎች ወደእሳቸው ማድረስ ከጋዜጠኛው በኩል የተቀዛቀዘ መሆኑን እንደ ድል ነው የቆጠሩት አሰልጣኙ በእሁድ የስፖርት 365 ፕሮግራም ላይ ጋዜጠኛውን በ3 የከፈሉት ሲሆን አንደኛው የጋዜጠኝነት ስነምግባር ያለው ፖዘቲቭ ነገሮችን ብቻ ወደ ህዝቡ ጋር የሚያደርስ ነው ብለዋል፡፡ አሰልጣኝ ዮሃንስ እንዳሉት ከሆነ ትክክለኛው ጋዜጠኛ ፖዘቲቩን ብቻ እየመረጠ መጠየቅ እና ወደህዝቡ ማቅረብ አለበት ነው።

አሰልጣኙ አዳሉት 2ኛው ከመስመር የወጣ ጋዜጠኛ አለ ለምሳሌ መልስ ልሰጥልህ እችላለሁ ባለፈው እሁድ ከብሩንዲ ስንጫወት በግል አላውቀውም በጋዜጠኝነትም አላውቀውም የሆነ ዶት ኮም ነው ያለኝ፡፡ አሁን ስትጫወቱ የምታገቧቸው ጎሎች የቆሙ ኳሶች አታገቡም ችግር አለባችሁ አለ ደነገጥኩኝ ምክንያቱም ከብሩንዲ ጋር ስንጫወት 3ቱም የቆሙ ኳሶች ናቸው ከፔናሊቲው ጭምር አሁን እዚህ ጋር ምንድነው የግለሰቡ ሀሳብ ብለህ ትጠይቃለህ፡፡ አለማወቁ ኳሱን አያውቀውም ወይስ ሌላ አጀንዳ አለው አንተ በንዴት ሌላ ነገር እንድትናገረው ነው የሚፈልገው ምክንያቱም እኔ ታርጌት ነኝ፡፡ እዛ ጋር ነው ወይስ አገኘሁት ነገር አለ፡፡ እንዳልኩህ ቅድም ውድድሩ በዛን ቀን ስለተደረገው ጨዋታ ትቶ ሌላ ቦታ ሄዶ ይጠይቅሃል ከዛም ያላልከውን አለ የሚሉ አሉ ለምሳሌ እኛ ሳኦቶሜ ጋር የተጫወትን ለታ የተወሰኑ ሰዎች ሜዳ ላይ የእነ ሳላዲንን ስም ይጠሩ ነበር ያን ሰዓት ላይ እኛ አሸንፈን ስንገባ የኔ ተጫዋቾች ተናደው የውኃ ላስቲክ ይወረውሩ ነበር፡፡ ኮች ምንድነው እኛ እኮ ኢትዮጵያዊ ነን እኛ ከጊዮርጊስ እኛ ከቡና ነኝ ምን አድርጉ ነው የሚሉን በማለት ተናግረዋል ፡፡
 
 
አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በ2ኛ መደብ የመደቡት ጋዜጠኞችን የሰጡት ስያሜ እና ምሳሌ 80 ሚሊዮን ህዝብን ከሚወክል የአንድ ሀገር ብሔራዊ ቡድን ከወከለ አሰልጣኝ የማይጠበቅ  በማንአለብኝነት የተሰጠ ንግግር ማለት ይቻላል፡፡ ለዚህም ነው አሰልጣኙ ሳይኮሎጂ ባለሙያ ያስፈልጋቸዋል ያልነው፡፡ አሰልጣኝ ዮሐንስሰ ራሳቸው እንደነገሩን በአሜሪካን ሀገር የተለያዩ ሥራዎችን በመስራት በርካታ ዲግሪዎችን እንደያዙ ነው ታዲያ የተማረ ሰው እዴት ይዋሻል እኛ አሰልጣኝ ከመጡ ጀምሮ ከአዲስ አበባ እስከ ባህር ዳር ያሉትን ቃለምልልሶች በሪከርድ ይዘናል ፡፡
 
አሰልጣኙ ከመስመር ከወጡት ጋር የመደቡት አንዱ የዚህን ፁሁፍ አቅራቢ እና የድህረገፁን ጋዜጠኛ ሲሆን ብሩንዲው ድል በኋላም ሁላችንም በከፍተኛ ደስታ እና ጭፈራ እደተዋጥን  ነበር ወደ ጋዜጣዊ መግለጫው የገባነው፡፡ በመጀመሪያ አሰልጣኙ ለጋዜጠኛው እድል ከመስጠታቸው በፊት ሁሉም የመጣበትን የሚድያ አድራሻ እዲናገር ለአስተባባሪው ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፉ ጋዜጠኛውም በጨዋነት እንኳን ደስ ያለህ በማለት መጠየቅ ጀመረ እድሉ በተራው ወደ ኢትዮ ፉት ቦል ዶት ኮም ሲደርስ በታዘዘው መሰረት አድራሻችን በማሳወቅ በእለቱ በርካታ ኳሶች በክንፍ በኩል ሲሻገሩ  ይባክኑ ነበር በቆሙ ኳሶች ላይ በኔ እይታ ብዙም ኦን ታርጌት የሚያድርጉ ተጫዋቾች የሉም በዚህ ላይ  የተሰራው በቂ ነው ወይስ ሌላ ሊጠሯቸው ያሰቧቸው ተጫዋቾች አሉ በማለት ጥያቄውን በአግባቡ የማስረዳት እድል በሌለበት ሁኔታ አስልጣኙ ተቀብለው ተሳስተሃል ሪጎሬዎችን ጨምሮ 3 ጎሎች በቆሙ ኳሶች ነው ያገባነው በማለት በወቅቱ ከኤሊያስ ማሞ በተሻገሩ  ኳሶች የተቆጠሩትን ግቦች በማንሳት መልሰዋል አዚህ ላይ በሲቲ ካፑ ያሳየውን አንቅስቃሴ በማየት በመልሱ ጨዋታ ኤሊያስን መምረጣቸው ውጤታማ እንዳደረጋቸው ሁሉ በተጨማሪ የሱ አይነት በቆሙ ኳሶች ላይ ብቃት ያለው ተጫዋች ቢያካትቱ ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚችሉ በቀናነት የተጠየቀን ጥያቄ ሌላ መልዕክት አለው ብለው መውሰድ እና ጥያቄውን አዛብተው በቆሙ ኳሶች ጎል አላገባህም አለኝ በማለት ለመዝለፍ እና ለማሳጣት መሞከራቸው በተጨማሪም በቀጥታ ሰርጭት የተላለፈ እና በሪከርድ የተያዘን ጥያቄንና የጠያቂን አድርሻ አዛብቶ ማቅረብ ተገቢ አይመስለንም፤ለመሆኑ በጠየቁት መሰረት አድራሻውን የተናገረውን አና በርካታ ገንቢ ጥያቄዎችን ከባህርዳር እሰከ አዲስ አበባ ሲያበረከትላቸው የነበረን የዚህ ፅሁፍ አቅራቢም ሆነ ድህረ-ገጽን አላውቀውም ብለው ካጣጣሉ ሃሳቡን በቀናነት ወስደውታል ለማለት ይከብዳል በወቅቱ ለስፖርት 365 አዘጋጆች መልስ ለመስጠት በተደጋጋሚ ከባለደረባዬ ጋር ቴክስት በማድረግ የሞከርን ቢሆንም ከአዘጋጆቹ ፍቃድ አላገኘንም እዚህ ላይ አሰልጣኝ ዮሃንስ ጠያቂው እርስዎ እዳሰቡት ይጠቅማል ያለውን ሀሳብ ከማቅረብ ውጪ ምንም አይነት አላማም ሆነ ሃሳብ የለውም ከዚህ ቀደም እርስዎ ወደ አሰልጣኝነት ሲመጡም ሆነ በባህርዳር የኬንያ እና የሌሴቶ ጨዋታ ብሔራዊ ቡድኑንም ሆነ እርስዎን የሚያበረታታ እና ትክክለኛ ዘገባ ሲሰራ የነበረን ሚድያ እና ጋዜጠኛ ግን በግድ ጠላቴ ነው ብሎ ማለት የጤነኝነት አይመስለንም እናም ከዚህ ቀደም እንደጠየቅነው ለተጫዋቾቹ ብቻ ሳይሆን ለራስዎትም ነገሮችን እያጣመሙ የሚያማክሩ ግለሰቦች ሣይሆን የስነ ልቦና ባለሞያ ያስፈልግዎታለ፡፡
 
 የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ባወጣው ደንብ መሠረት አሰልጣኙንም ሆነ ተጫዋቾችን በግል ማንም ሚድያ እንዳያናግር በማዘዙ እና ጋዜጠኞች ስለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቂ መረጃ ማግኘት ባለመቻላቸው ምክንያት በተገኘው አጋጣሚ ያለፉ ጨዋታዎችን በምሳሌ በመጥቀስ መረጃ ለማግኘት በመሞከራቸው አሰልጣኙ እንደ አላዋቂነት አድርገው አቅርበውታል፡፡ ሌላው እንደወንጀል የቆጠሩት በሳኦቶሜ ጨዋታ ህዝቡ በግራ እና በቀኝ ሳይከፋፈል ብሔራዊ ቡድኑ በሳኦቶሜና በቡሩንዲ ተሸንፎ በሲሸልስ ነጥብ ጥሎ በመምጣቱ በነበረው ቁጭት እና በመልሱ አዲስ አበባ ላይ በተደረገው ጨዋታ ግቦች ከመቆጠራቸው በፊት ብሄራዊ ቡድናችን አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት ሰዓት የእነሳላዲን ስም እየጠራ ሲቃወምዎት ነበር ተብለው  ሲጠይቁ የመለሱት  '' ሁሉም ኢትዮጵያን ይውዳል አለውቅም ምን ተለእኮ ያለው ሰው ምን አውቃለሁ እኔ አላቅም ምንም የማውቀው ነገር የለም እማቀው ምንድን ነው እኔ እነዚህ ልጆች የኢትዮጵያን ባንዲራ ለብሰው ሜዳ ላይ ገብተው 3ለባዶ እያሸንፉ የሚጮህ ከሆነ የግለሰብ ስም የሚጠራ ከሆነ ኢትዮጵያዊነት ነው ይሄ ኢትዮጵያ የዮሀንስ ሳህሌ አይደለችም የአንድ ግለሰብ አይደለችም 3ለባዶ አሸንፎ ግለሰብ የሚጠራ ከሆነ ሌላ ተልእኮ አለ ማለት ነው የእግር ኳስ አይደለም "' በማለት በመመለስዎ ይህንንም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት  በመተላለፉ እና ህዝቡ ጋር ስለደረሰ ምክንያት ይቅርታ ይጠይቁ በማለት ሀሳቡ የሰጠውን ጋዜጠኛ ሲወቅሱ እና ሲያብጠለጥሉ ተደምጠዋል፡፡ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ይቅርታ መጠየቅ ያስከብራል እንጂ አያሳፍርም በሳኦቶሜ የመልስ ጨዋታ ሙሉ ለሙሉ ከግራ ጥላ ፎቅ እስከ ቀኝ ጥላ ፎቅ ባንድ ድምጽ ሶስተኛው የማሸነፊያና የማስተማመኛ  ግብ አስኪቆጠር ድረስ እርስዎን በመቃወም ወደ ሜዳ እንዳይደርሱ እና ቤንች ላይ እንዲቀመጡ    ያደረግዎትን የስፖርት አፍቃሪ ጥቂቶች በማለት ለማስተባበል መሞከርዎ አግባብ አይደለም፡፡ እዚህ ላይ አንድ ምሳሌ ልንገርዎ ከዚህ ቀደም አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ተቀይሞሃል እና ታረቅ ሲባሉ እኔ ከቡና ደጋፊ ጋር ምንም ቅያሜ የለኝም ሆኖም ኢትዮጵያ ቡና የህዝብ ክለብ ነው በርካታ ደጋፊ ያለው የሚከበር ነው ተቀይሞሃል ካላችሁኝ ባላምንበትም መታረቅ ሳይሆን እኔ እራሴ ይቅርታ እጠይቃለሁ በማለት ስቴዲየሙን በመዞር ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ አሰልጣኝ ዮሐንስ እርስዎ ግን በስደት ለረጅም አመታት በሀገር ስላልነበሩ ባህላችንን የረሱት ይመስለኛል ወይም የነጮቹም ስልጣኔ ብዙም አይታይብዎትም፡፡ ከዚህ ቀደም በባህርዳር ቆይታችን የቡድኑ መሪ የነበሩት አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ በጥሩ ሁኔታ እያማከሩ እያረገቡ ይመርዎት አደነበር አስተውለናል ፌዴሬሽኑ የስፖረት ሰይኮሎጂስት የመቅጠር አቅም ከሌለው የቀድሞው የቡድን መሪውን ተመልሰው ቢያግዝዎት መልካም ነው፡፡

 በእሁዱ የስፖርት 365 ፕሮግራም አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በቻን ውድድር ገና ከብሩንዲ ጋር ሳንጫወት ቡድኑ ለቻን ውድድር ቢያልፍም ምንም ውጤት አያመጣም በማለት በአንድ የሬዲዮ ጣቢያ በጋዜጠኛ እንደተተቹ በመናገር ሲኮንኑ ታይተዋል እሳቸውም ጋዜጠኛው ለምን እንዴት እንዳለ አልገባቸውም ለመጠየቅም አልሞከሩም ቃለመጠይቁን ያዘጋጀላቸው ጋዜጠኞቹ ግን ገብቶት እሱ  የስታይል ጥያቄ ነው ቢሏቸውም አልተረዱም ግን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ያለ አንድ ተመልካች እንኳን በጨረፍታ ሀሳቡን ቢሰማ ማን እንዳለው እና ለምን እንዳለው ስለሚያውቅ ብዙም ቅሬታ አይሰማውም ወይ ይቀበላል ወይ አይቀበልም እሳቸው ግን ይህንን እንደወንጀል ቆጥረው ሲኮንኑ እና የጋዜጠኞች ማህበር የለም ሀይ ባይ የለም በማለት ቃለመጠይቁን ላዘጋጀላቸው ጋዜጠኞች ሲጠይቁ ነበር፡፡ ለመሆኑ ማሕበር እከሌ እንዲህ አርገህ ስራ እዚሁ ጋር ፣ እከሌን ለምን ተቸህ ሊል ነው እንዴ የሚቋቋመው፡፡ ሌላው አሰልጣኙ  ቡሩንዲ ላይ እኛ በጦር ተከበን ተዋክበን በፍራቻ ተውጠን ስንጫወት ብንሸነፍ ምን ይደንቃል ብለዋል ለመሆኑ ብሩንዲ ይህን ያህል የሚያስፈራ ከሆነ ከብሩንዲው አሰልጣኝ ጋር ግብግብ የገጠሙት እና ለብሩንዲው አሰልጣኝ መውጣት ምክንያት የሆኑት እንዴት እንደሆነ ያውቁታል፡፡ ኤፍሬም አሻምን በቀይ ያስወጣውን ተጫዋች በእጅዎ ምልክት ምን ነበር ያሳዩት እውነት ፈርተው ነበር ለምን ይዋሻል፡፡ እርስዎ ጋዜጠኞችን በወቀሱበት ሚድያ በቀጥታ ስርጭት ሁሉንም እየሰማን ነበር።
 
 በቻን ውድድር በዚህ አጨዋወት ብናልፍም ቡድኑ የትም አይደርስም ብሎ ሀሳብ የሰጣቸው ጋዜጠኛ የተበቀሉ መስሏቸው ጋዜጠኞችም  የሚሸሸጉበት የሚገቡበት አጥተው እኛ ነን ያስጠጋናቸው አልጋ ይዘን ምግብ አብልተን አጠጥተን የረዳናቸው በማለት ወደ ቦታው የተጓዙትን ሁለት ጋዜጠኞችን ክብር በሚነካ ሁኔታ ተናግረዋል፡፡  

 ጋዜጠኛው ስርዓት የለውም ባሉት ሚዲያ ስርኣት ባጣ ሁኔታ ሲያብጠለጥሉ ተስተውለዋል፡፡ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በሥራቸው ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ ሚዲያውን በሀይል በጫና ፀጥ በማድረግ ከጥቂት ግለሰቦች ጋር ብቻ    ለመጓዝ የመረጡ ይመስላል ይህንን ለማለት ያስቻለኝ ከዚህ ቀደም ለሳቸው ገንቢ ሃሳብ እና ትችቶችን ላቀረበ ጋዜጠኛ በማህበራዊ ድህረ ገጽ የሳቸው ደጋፊ ነኝ ያለ ግለሰብ ጋዜጠኛውን በሃይመኖቱ እና የሌለበትን ሀጢያት በማሸከም አሳፋሪ እና አስነዋሪ ጽሁፍ በመጻፍ ለመሸማቀቅ የተሞከረ ሲሆን አኔም ይህን ለመጻፍ ስነሳ ይህ አንደሚሆን እና አሰልጣኙ ወደ ቻን ስላለፉ ይቅርብህ የሚል ምክር አዘል ማስጠንቀቂያ ደርሶኝ ነበር ግን አንድ ግለሰብ ትልቅ አደራ እና ሃላፊነት ተሰጥቶት ወደገደል እስኪገባ መጠበቅ አግባብ አይደለም። አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ  ስራ ከጀመሩ ጀምሮ የነበሩ ቃለምልልሶች በእጃችን ይገኛሉ፡፡ በቅንነት እና በቀናነት እርሳቸውን ለማገዝ መረጃ የሚሰጧቸውን እና የሚጠይቋቸውን ጋዜጠኞች የሚያሸማቅቅ እና ቁጣ የተቀላቀለበት መልስ መስጠት የጀመሩት ወደ  መንበሩ ገና እንደመጡ ነበር፡፡ ይህ ደግሞ እሳቸውም ሆነ እግር ኳሱን የሚጠቅም አይደለም እና አሁንም ደግመን ደጋግመን  ለአሰልጣኙ ሳይኮሎጂስት እና በእግር ኳሱም  ቋንቋ ከጋዜጠኛው እና ከህዝቡ የሚያግባባቸው አስተርጓሚ ቢመደብላቸው ጥሩ ነው፡፡

ፈለቀ ደምሴ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
felexsami [839 days ago.]
  wooooooow tnx Ethiofootball.com for info. really what kind of arrogant stupid coach we have.shame on you ethiopia foot ball federation

Mali [839 days ago.]
 ኤፍሬም አሻምን በቀይ ያስወጣውን ተጫዋች በእጅዎ ምልክት ምን ነበር ያሳዩት ??? ha ha ha .....shame on you dictator Yohanes Maferiya nehe !

Gezegeta [839 days ago.]
 before 9 days i said like this ....... ኧረ ኢትዮ ፉትቦል የሰራችሁት ዘገባ ፌር አይደለም ያሸነፍነው ካሜሮንን ወይም ሞሮኮን ነው ያስመሰላች ሁት. ኧረ ተረጋጉ ኧረ ፍሬኑን ያዙት ለሙገሳው በጣም ነው የቸኮላችሁት ደካማዋን ቡርንዲን ያውም በሜዳችን አሸንፈን ኧረ ይደብራል እስቲ እናያችሁ የለ እንዴ ከአልጄሪያና ከኮንጎ ጋር ከተጫወትን በሃላ ምን እንደምትሉ ! ይሄ አምባገነን አሰልጣኝ ነኝ ተብዬ በዚህ ግትር አቋሙ ብሔራዊ ቡድናችንን ያዋርደዋል ያሰድበዋል በጣም የማዝነው ብሔራዊ ቡድኑን መጥቀም የሚችሉ ስንት ጀግና ተጫዋቾችን መምረጥ እየቻለ የራሱን ቡድን ሰራ ለመባል ስለሚፈልግ ብቻ ልጆቹን ገፋቸው ሃገራችንንም በትንንሽ ቡድኖች ሳይቀር አስደፈረን በጣም የማዝነው አንተን እዚህ ቦታ ላይ አስቀምጦ ያለቦታህ ያላቅምህ ስራ ለሰጠህ ፌዴሬሽን ነው. ቆይ ኮንጎ እና አልጄሪያ ላይ እናይሻለን እኮ ! በቡሩንዲ 2 ለ 0 ቡጁምቡራ ላይ ስትቀምሺ የውሃ ፕላስቲኮችን ስትወረውሪ ከቡሩንዲው ኮች ጋር ድብድብ ካልገጠምኩ ስትዪ ነበር....... ቆይ እናይሻለን እኮ ኮንጎ እና አልጄሪያ ላይ ምን እንደምትሰሪ ?! ምን እንደምትወረውሪ ?! ለሽንፈትሽም ምን ምክንያት እንደምትደረድሪ ???!!!

ኳስ [839 days ago.]
 እኔ የማይገባኝ አንድ ነገር አለ። ጋዜጠኞቹ ስለ ኳስ ከአሰልጣኙ በላይ እናቃለን የሚሉ ይመስላል። ይሄ ደሞ ትክክል አይደለም። ጋዜጠኛ ይጠይቃል ለጠየቀው ጥያቄ የተሰጠውን መልስ ይዞ ሳይበርዝ ይዘግባል። ከቻለም የራሱን ሀሳቦች ክሪቲክስ የግለሰብ ስብእና ላይ ሳይንተራስ ይጽፋል እንጂ ከአሰልጣኝ ጋር አተካሮ አይገጥምም። እነደዚህ ሁሉም እየተነሳ አሰልጣኙን የሚሞግት ከሆነ። አሰልጣኙ ምን ሊሰራ ይችላል። ስራው ላይ አተኩሮ ሊሰራ አይችልም። ስለዚህ ጋዜጠኛ ፈለቀ የጻፍከው ክሪቲክ በጎ ነገሮች ቢኖሩትም ኔጋቲቭ ሀሳቦችም አሉበት። አሰልጣኙ ለጋዜጠኞችም ሆነ ለህዝብ ደንታ የላቸውም የሚል አይነት ድምጽ ያለው ጽሁፍ ነው። ይሄ ግን ትክክል አይደለም። አሰልጣኙ ለጋዜጠኞች ደንታ ባይኖረው መብቱ ነው። ምክንያቱም ሁሉም ጋዜጠኛ በሞያው እኩል እውቀትም ሆነ በኳስ ግንዛቤ የተለያየ ነው። አሰልጠኙን የማይመጥን ጥያቄ ሲቀርብለት ሪጀክት ማድረግ ይችላል። ጊዜውንም በማይረባ ጥያቄ ማባከን የለበትም። ሌላው ግን በተለይ አንድ አሰልጠኝ ለዛውም የሀገሩን ብሄረዊ ቡድን እያሰለጠነ ለዛውም የሀገሩን ማሊያ ለብሶ የተጫወተን አሰልጣኝ ። ለህዝቡ ደንታ የለውም የሚል እንደምታ ያለው ጽሁፍ መጻፍ ከፕሮፌሽናል ጋዜጠኛ አይጠበቅም።

ኳስ [839 days ago.]
 እኔ የማይገባኝ አንድ ነገር አለ። ጋዜጠኞቹ ስለ ኳስ ከአሰልጣኙ በላይ እናቃለን የሚሉ ይመስላል። ይሄ ደሞ ትክክል አይደለም። ጋዜጠኛ ይጠይቃል ለጠየቀው ጥያቄ የተሰጠውን መልስ ይዞ ሳይበርዝ ይዘግባል። ከቻለም የራሱን ሀሳቦች ክሪቲክስ የግለሰብ ስብእና ላይ ሳይንተራስ ይጽፋል እንጂ ከአሰልጣኝ ጋር አተካሮ አይገጥምም። እነደዚህ ሁሉም እየተነሳ አሰልጣኙን የሚሞግት ከሆነ። አሰልጣኙ ምን ሊሰራ ይችላል። ስራው ላይ አተኩሮ ሊሰራ አይችልም። ስለዚህ ጋዜጠኛ ፈለቀ የጻፍከው ክሪቲክ በጎ ነገሮች ቢኖሩትም ኔጋቲቭ ሀሳቦችም አሉበት። አሰልጣኙ ለጋዜጠኞችም ሆነ ለህዝብ ደንታ የላቸውም የሚል አይነት ድምጽ ያለው ጽሁፍ ነው። ይሄ ግን ትክክል አይደለም። አሰልጣኙ ለጋዜጠኞች ደንታ ባይኖረው መብቱ ነው። ምክንያቱም ሁሉም ጋዜጠኛ በሞያው እኩል እውቀትም ሆነ በኳስ ግንዛቤ የተለያየ ነው። አሰልጠኙን የማይመጥን ጥያቄ ሲቀርብለት ሪጀክት ማድረግ ይችላል። ጊዜውንም በማይረባ ጥያቄ ማባከን የለበትም። ሌላው ግን በተለይ አንድ አሰልጠኝ ለዛውም የሀገሩን ብሄረዊ ቡድን እያሰለጠነ ለዛውም የሀገሩን ማሊያ ለብሶ የተጫወተን አሰልጣኝ ። ለህዝቡ ደንታ የለውም የሚል እንደምታ ያለው ጽሁፍ መጻፍ ከፕሮፌሽናል ጋዜጠኛ አይጠበቅም።

Jaimibarca [839 days ago.]
 @ ኳስ Offffffffffff ቡዙ ጊዜ የምትሰጣቸው ኮመንቶች ከክለብ ደጋፊነት የፀዱ አይደሉም ብሔራዊ ቡድንና ክለብን ለይተህ ማየት የተሳነህ ጨለምተኛ ነገር ነህ ፥፥ የሰጠውትም ኮመንት ለምን ጠፋ ማለጥ እራሱ ብልግናህን አለማመንህን ያሳያል:: ኢትዮ ፉትቦልም ስለ ዮሃንስ የፃፈውም ነገር ትክክልና ማንኛውም የብሔራዊ ቡድኑ ደጋፊ ሲሰጠው የነበረውን ትችትና ትዝብት ነው:: ዮሃንስ ችግር ያለበት አሰልጣኝ እንደሆነ ለማናችንም ግልፅ ሆኖ ሳለ አንተ ግን ነገሮችን ከምትደግፈው ክለብ አንፃር ስለምትመለከታቸው ለብሔራዊ ቡድኑ ግድም የለህም ጨለምተኛ ራዝነጠቅ ነገር ነህ አቦቦቦቦ ተፋታን ተደበቅ በናትህ ጅብ እንዳይስቅብህ !

Gezegeta [839 days ago.]
 ብዙ ጊዜ የሚሰጣቸው አስተያየቶች ልክ አይደሉም ከብሔራዊ ቡድኑ ይልቅ ግለሰቦችን የሚደግፍ ከኳስ እውቀት ነፃ የሆነ እዚችም እዛችም የሰማትን ነገሮች እዚህ ፔጅ ላይ ኮፒ ፔስት የሚያደርግ ፍሬሽ ማን ነገር ነው

YoniSanjawe [839 days ago.]
 እኔም እዚህ ፔጅ ላይ ብልግና ተናግሮ እኔንም ክፉ ያናገረኝ ይሄ ሰው ነው ምን እንደሆነ አላማው ግልፅ አይደለም ሁልጊዜ ኔጌቲቭ ነገሮችን ነው ኮመንት የሚያደርገው ብሔራዊ ቡድናችንንም የሚመለከተው ከሚደግፈው ክለብ አንፃር ነው የዚህ አይነቱ ሰው ብሔራዊ ቡድናችን እየተጫወተ ቡላ ገለባ አደገኛ እያሉ ከሚያላዝኑት ውስጥ አንዱ ነው

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!