ሳላዲን ሰይድ በህመም ምክንያት ለኮንጎ ብራዛቪል ጨዋታ እንደማይደርስ ኢት.እግ.ኳስ.ፌዴ አስታወቀ።
ጥቅምት 25, 2008

ዛሬ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነን ክፍል ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መረጃ መሰረት ሳላዲን ሰይድ  ህዳር 4 እና 7 ቀን 2008 ዓ.ም ለዓለም ዋንጫ  ማጣሪያ ብሄራዊ ቡድኑ ከኮንጐ ብራዛቪል ጋር ላለበት ጨዋታ  ፌዴሬሽኑ ጥሪ ቢያደርግለትም በህመም ምክንያት ሊመጣ እንደማይችል ገልጿል። 
Saladin Seid


ፌደሬሽኑ የላከውን ማስታወሻ ከዚህ በታች እንዳለ አቅርበነዋል። ፌደሬሽኑ ለላከው ማስታወሻ አባሪ ማስረጃዎችን አያይዟል።ለስፖርት መገናኛ ብዙሃን በሙሉ


ጉዳዩ፣ ኢንተርናሽናል ተጫዋች ሳላዲን ሰይድን ይመለከታል፣

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ህዳር 4 እና 7 ቀን 2008 ዓ.ም ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከኮንጐ ብራዛቪል ጋር ላለበት ጨዋታ ለተጫዋች ሳላዲን ሰይድ ጥቅምት 17 /2008 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ለአልጄሪያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከክለቡ ፈቃድ እንዲሰጥልን የጠየቅን ቢሆንም ጥቅምት 23/2008 ዓ.ም ለሳላዲን ስልክ በመደወል የአውሮኘላን ትኬት እንዲቆረጥለት አመቺውን ቀን ሲጠየቅ እንዳመመውና ልምምድ እየሰራ እንዳልሆነ ገልጾልናል፡፡

በተጨማሪም ጥቅምት 24 ቀን 2008 ዓ.ም ከክለቡ ችግሩን የሚገልጽ ደብዳቤ ለፌዴሬሽኑ ደርሶታል፡፡ ይሁን እንጂ በአንዳንድ ስፖርት ሚዲያ ሳላዲን በፌዴሬሽኑ ጥሪ ሳይደረግለት አሞኛል ብሎ ተናግሯል የሚለው ትክክል ያልሆነ እና ከእውነት የራቀ መሆኑ እንዲታወቅ ፌዴሬሽኑ ያሳስባል፡፡

ለዚህም ማስረጃ ሁለት አባሪ አያይዘን የላክን መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!