የታላቁን ጋዜጠኛ ‘ታላቅነት’ የመሰከረ ማህበር
ሐምሌ 07, 2015

በይርጋ አበበ

ላለፉት 36 ዓመታት በኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጆሮ አዲስ አይደለም። ከብስክሌት ውድድር እስከ ቦክስ እና እጅ ኳስ እንዲሁም ቮሊቦል እና ፈረስ ጉግስ ስፖርቶችን በመዘገብ ይታወቃል። ቅርጫት ኳስ እና ካቴንም ለመዘገብ አይሰንፍም። ቴኳንዶ እና ዳርትም ቢሆኑ በጋዜጠኛው ሙያዊ እውቅና ተሰጥቷቸው የተዘገቡ ስፖርቶች ናቸው። በአጭሩ ጋዜጠኛው ያልዘገበው የስፖርት አይነት አለ ማለት ስፖርቱ አገር ውስጥ አልገባም ማለት ነው። እግር ኳስን ከልቡ ይወዳል ሆኖም ከአዲስ አበባ ዋናው ስታዲየም ይልቅ ከትንሿ ስታዲየም የሚካሄዱ ውድድሮችን ተገኝቶ በመዘገብ ትኩረት ያልተሰጡትን ስፖርቶች ትኩረት እንዲያገኙ አድርጓል ጋዜጠኛ ሰለሞን ገብረእግዚያብሔር።

Solomon Gebregziabhere ESJA  Life Award 2008


በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ ቮሊ ቦል ፌዴሬሽን በብሔራዊ ሆቴል ጠቅላላ ጉባኤውን ባካሄደበት ዕለት የአንድ ክለብ አሰልጣኝ እጃቸውን አውጥተው “እውነት ለመናገር የእኛን ስፖርት ዘወር ብሎ የተመለከተ ጋዜጠኛ አለ? አለ ካላችሁ ንገሩኝ። ለእኔ ግን ክልል ላይም ሆነ አዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየም ላይ ጸሀይና ብርድ ሳይበግረው ውድድሮችን ተከታትሎ የሚዘግብ ጋዜጠኛ የማውቀው ሰለሞን ገብረእግዚያብሔርን ብቻ ነው ብዬ ብናገር ስህተት አልሰራሁም” ብለው ተናገሩ። በወቅቱ የተሰበሰቡት የፌዴሬሽኑ ተወካዮችና እኛን ጋዜጠኞችን ጨምሮ ሁሉም ተሰብሳቢ በአሰልጣኙ አስተያየት ተስማምተን ለንግግራቸው ጭብጨባ ለገስናቸው። የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበርም የህይወት ዘመን ተሸላሚ አድርጎ በመምረጥ የጋዜጠኛውን ታላቅነት እውቅና የሰጠው ይህንን ሰው ነው።
ጋዜጠኛ ሰለሞን ገብረእግዚያብሔር የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር የህይወት ዘመን ተሸላሚ አድርጎ ሲመርጠው ሽልማቱን ለመውሰድ ወደ መድረክ ሲወጣ አይኖቹ በእንባ ተሞልተው ነበር። የተደረገለትን ሽልማት በተመለከተም “እውነት ለመናገር የምናገረው የለኝም። በእውነቱ የስፖርት ጋዜጠኝነት አስደሳች ስራ ነው እስካሁንም ደስ እያለኝ የሰራሁት ስራ ነው” ያለ ሲሂሆን ባርደረቦቹ ላበረከቱለት ሽልማትም ምስጋናውን አቅርቧል። ሰለሞን ግን ይህን ብቻ ተናግሮ ዝም አላለም “እናንተ የሙያ አጋሮቼ ሆይ የስፖርት ጋዜጠኝነት ማለት እግር ኳስ እና አትሌቲክስ ብቻ አይደለም። ሁሉንም ስፖርቶች ተከታትላችሁ በመዘገብ ለህዝብ አድርሱ” ሲል የአደራ ቃሉንም ሰጥቷል።

Solomon Gebregziabhere ESJA  Life Award 2008

ከጋዜጠኛው ሽልማት በኋላ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጭ ያሉ የስፖርት ጋዜጠኞች በሰለሞን ሽልማት መደሰታቸውን የገለጹ ሲሆን የሰንደቅ ጋዜጣ ስፖርት ዘጋቢ የሆነችዋ ጋዜጠኛ ቆንጂት ተሾመ “ይህ ሰው ብዙ ያስተምራል። ስራ እጅ…ግ ይወዳል። ሰውን ሁሉ ያከብራል። በህይወይት ብዙ ነገር የሚጨምር የተረጋጋ እኔ ባልደረባነቱን አይደለም አንድ ንግግሩን መስማት በራሱ መታደል ነው። እሱ የስፖርት ጋዜጠኛ ቁንጮ ነው እግር ኳስ ወይም አትሌቲክስ ብቻ የሚያውቅ ሳይሆን ስፖርት የሚያውቅ የስፖርት ጋዜጠኛ ነው” ስትል ተናግራለች። “ለ36 ዓመታት ራሱን ለአንድ ነገር ብቻ የሰጠ ጋዜጠኛ ነው። ይህ ሽልማትም በእውነት ይገባዋል” በማለት አስተያየቷን አጠናቃለች።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር የስራ አስፈጻሚ አባል የነበረውና አሁን ከአገር ውጭ የሚኖረው ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሻፊ በበኩሉ “ትሁት፣ ሰውን አክባሪ፣ የሌሎች ስሜት የሚሰማው፣ ቀጥተኛ፣ ታማኝ፣ ለሙያ አጋሮቹ የሚቆም፣ ለሙያው ያለውን በሙሉ የሚለግስ፣ ቃሉን የሚጠብቅ፣ ለራሱ የሚታመን፣ እምነት የሚጣልበት፣ ለችግሮች አብሮ መፍትሔ የሚፈልግ፣ በሳል፣ የተረጋጋ እና ሁሌም ጥሩ ነገርን የሚመኝ ታላቅ ሰው” ሲል ሰለሞንን ገልጾታል። ጋዜጠኛ ኢብራሂም አክሎም “ላለፉት 37 ዓመታት የሙያ አጋሮቹ አይተው ሰለሞንን ተገርመውበታል። አድንቀው አክብረውታልም። ዛሬ የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር የህይወት ዘመን የላቀ ተሸላሚ አድርጎ ሲመርጠው የሙያ አቻዎቹ ከመቀመጫቸው ተነስተው ለክብሩ ሲያጨበጭቡለት ደስ ብሎኛል ይገባዋልም” ሲል በፌስ ቡክ አካውንቱ ላይ አስፍሯል።  

ይበልጣል አእምሮ የተባሉ አስተያየት ሰጭ ደግሞ “ለጋዜጠኛ ሰለሞን ክብር ይገባዋል። ሳይሰለችና ሳይደክም ለረጅም ዓመት በተለይም በሀገር ውስጥ ስፖርቶች ላይ ጥሩ ግንዛቤ እንዲኖረን አድርጓል። ጥሩ እይታ ነው የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር በዚህ ስራችሁ ልትመሰገኑ ይገባል” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
peteros [837 days ago.]
 ጋዜጠኛ ሰለሞን ገ/እግዚሐብሔር በጣም ነዉ የምወድህ! ጌታ ይባርክህ!

የምሥራች [833 days ago.]
 ያከበረ ይክበር ማህበሩም ሁላችሁም እሱን እንዳከበራችሁ እናነተም ከእርሱ የበለጠ ያክብራችሁ፡፡ የእድሜ ልክ ልፋቱን አስባችሁ ክብር ሰጥታችሁታልና ለእናንተም እድሜ ከጤና ጋር ያድላችሁ መልካም የሥራ ዘመን ይሁንላችሁ፡፡ አሜን በዚህ ዘመን ታናናሸች በታላላቆች ላይ በሚያፌዙበት፣ በሚቀልዱበት፣ በሚሳለቁበት...በዚህ ዘመን ለታላቃችሁ የአሁን ማንነቱን ብቻ ሳይሆን የቀድሞውን ማንነቱን ለአሁን ልጆች በማሳወቃችሁ/አውቅና በመስጠታችሁ የእናንተን ትልቅነት የሚያሳይ ነውና በእውነት እናንተ የስፖርት ጋጤኞች በርቱ አምላክ ይባርካችሁ፡፡ አሜን ለሰለሞንም እድሜ ከጤና ጋር ያድልልን፡፡ አሜን

Elias [820 days ago.]
 10.000 birr....Really its shame. He served sport journalist the past 37 years...at least you should organize from all sport federations and persons......this is not gift, insulting.

Baible [820 days ago.]
 10.000 birr....Really its shame. He served sport journalist the past 37 years...at least you should organize from all sport federations and persons......this is not gift, insulting.

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!