ዳሽን ቢራ ከአርሴናል አሰልጣኞችን ወደ ኢትዮጵያ በማስመጣት ስልጠና ሊሰጥ ነው
ጥቅምት 27, 2008

በይርጋ አበበ

ከተቋቋመ እና ስራ ከጀመረ ገና ሁለት አስርታትን ያልደፈነው ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ከእንግሊዙ አርሴናል ክለብ ሁለት አሰልጣኞችን ወደ አገር ቤት በማስመጣት ለኢትዮጵያዊያን አሰልጣኞች ስልጠና ሊሰጥ ነው።

ፋብሪካው ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መረጃ ለማወቅ እንደተቻለው ሁለቱ አሰልጣኞች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ስልጠና መስጠት የሚጀምሩት የፊታችን ህዳር 6 እና 7 ቀን በሱሉልታው ያያ ቪሌጅ እና በቀነኒሳ ሆቴል ነው። በስልጠናውም ከፕሪሚየር ሊግ እና ከብሔራዊ ቡድን የተውጣጡ ዋና እና ረዳቶቻቸውን ጨምሮ 30 አሰልጣኞች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በዳሽን ቢራ ፋብሪካ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መክብብ ዓለሙ ፊርማ ለዝግጅት ክፍላችን የተላከው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ከአርሴናል የሚመጡት አሰልጣኞች የሚሰጡት ስልጠና በአገራችን ታሪክ የመጀመሪያው ነው ይላል።

ስልጠናው በዋናነት በመሰረታዊ የእግር ኳስ ተጫዋቾች አሰለጣጠን ዙሪያ ትኩረት እንደሚያደርግ የገለጸው ይሄው ደብዳቤ “ስልጠናው በአገራችን እግር ኳስ ላይ ራሱን የቻለ አወንታዊ አሻራ የሚያኖር ሲሆን ለሰልጣኞችም የምስክር ወረቀት የሚሰጣቸው ይሆናል” ሲል ይገልጻል። ዳሽን ቢራ ፋብሪካ በስሙ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚወዳደሩ ሁለት የወንድ እና የሴት ክለቦች ያሉት ሲሆን ከፋብሪካው የውስጥ አዋቂዎች በደረሰን መረጃ ለማወቅ እንደቻልነውም ለሁለቱ ክለቦች እና በስራቸው ለሚያሳድጋቸው ተተኪዎች በየዓመቱ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ያወጣል። አርሴናል እና ዳሽን ቢራ አብረው ለመስራት የተስማሙት ከአንድ ወር በፊት መሆኑ ይታወሳል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!