ከ20 አመት በታች የኢትዮጵያ የሴቶች ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ጋና ላይ የመልስ ጨዋታውን ያደርጋል
ጥቅምት 28, 2008

ፓፓዋ ኒው ጊኒ ለምታዘጋጀው የታዳጊ የሴቶች የዓለም ዋንጫ ለማለፍ  ከ20 አመት በታች የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን  ዛሬ 12:00 ሰአት ላይ የመልስ ጨዋታውን ባባያራ ኩማሲ ስታዲየም ላይ  ከጋና አቻው ጋር ያደርጋል። ሁለቱ ቡድኖች አዲስ አበባ ላይ  ከ15ት ቀን በፊት ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታቸው 2ለ2   አቻ መለያየታቸው የሚታወስ ነው። 

Under 20 Ethiopian Women's Team

የጋና ብሄራዊ ቡድን ከአፍሪካ እጅግ ጠንካራ የሆነና በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች በመሳተፍ ከፍተኛ ልምድ ያለው ብሔራዊ ቡድን ቢሆንም በአሰልጣኝ አስራት አባተ የሚሰለጥኑት ታዳጊዎቹ  የኢትዮጵያ እምቡጦች የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታቸውን  የቡርኪና ፋሶ   ብሄራዊ ቡድንን በሜዳው    በሎዛ አበራ ሁለት ጎሎች አማካኝነት 2ለ0 ማሸነፋቸው ይታወሳል። ከሜዳቸው ውጪ የማሸነፍ አቅም እንዳላቸው ያስመሰከሩት የኢትዮጵያ እምቡጦች ዛሬም ከሜዳ ውጪ በሚያደርጉት የመጨረሻ ፍልሚያ እጃቸውን እንደማይሰጡ ይጠበቃል። ለውጤቱም ማማር አዲስ አበባ ላይ ከጋና ጋር 2ለ2  በተለያዩበት ጨዋታ ሁለቱንም ጎሎች ያስቆጠረችው  የጎል አዳኟና የቡድኑ አምበል ሎዛ አበራ  ትልቁን ሚና ትጫወታለች ተብሎ ይጠበቃል።

በአዝናኝና ውጤታማ አጨዋወት ስታይሉ ከፍተኛ ድጋፍና አድናቆትን ከተመልካቹ ያተረፈው የኢትዮጵያ የሴቶች ታዳጊ ቡድን ወደዓለም ዋንጫ ለማለፍ የጋና አቻውን ማሸነፍ ወይም ከሁለት ጎል በላይ አስቆጥሮ አቻ መውጣት ይጠበቅበታል።  

በዛሬው ጨዋታ የኢትዮጵያ ታዳጊ ቡድን አሰላለፍ እንደሚከተለው ሊሆን እንደሚችል  የኢትዮ.እግ.ኳስ ፌዴ. የህዝብ ግንኙነት ወንድምኩን አላዩ ከስፍራው በላከው ማስታወሻ ገልጾልናል።

በረኛ: ታሪክዋ ባርገኔ 
ተከላካይ: ሰብለ ቶጋ፣ ሀሳቤ ሙሶ፣ ፋሲካ በቀለ፣ሃብታም እሸቱ፣ መዲና አወል
አማካኝ: ሰናይት ቦጋለ፣ ትግስት ያዴታ፣ አዲስ ንጉሴ
አጥቂ: አይናለም አስማማው፣ ሎዛ አበራአምበል.
ቅያሬ: ፍሬህይወት ገብሩ፣ምስር ኢብራሂም፣ሄለን እሸቱ፣እታለም አመኑ፣ ወርቅነሽ መልመላ፣ሰርካዲስ ጉታ፣ቤዛዊት ተስፋዬ

ኢትዮ ፉትቦል የታዳጊ የሴቶች ብሄራዊ ቡድናችን መልካም እድልን ይመኛል!

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Tilahun haile [769 days ago.]
 It is best news

Tilahun haile [769 days ago.]
 It is best news

Zerihun [768 days ago.]
 በአቀራረቡ ሁሉ ተደስቼዋለሁ

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!