የኢትዮጵያ እግር ከስ ፌዴሬሽን ጀግኖቹን አመሰገነ
ጥቅምት 28, 2008

በይርጋ አበበ

የፊታችን የካቲት ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሩዋንዳ ለምታስተናግደው አራተኛው የቻን ዋንጫ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለዚህ ተሳትፎ በመብቃቱ ከፌዴሬሽኑ የምስጋና የገንዘብ ሽልማት ተበረከተላቸው። 
EFF  Awards the Walyas for qualifying for Chan

ፌዴሬሽኑ ዛሬ አመሻሽ በካፒታል ሆቴል የገንዘብ ሽልማቱን ባበረከተበት ወቅት የተገኙት የፌዴሬሽኑ ምክትል ገዥ አቶ ተክለወይን አሰፋ የገንዘብ ሽልማቱ መጠን በቂ ነው ብለን ባናምንም ለሰራችሁት መልካም ስራ እውቅና መስጠት ስለፈለግን ነው ዛሬ ጠርተን መሸለም የለግነው ሲሉ ተናግረዋል። 

በሽልማቱ መሠሠትም አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ሃምሳ ሺህ፣ ምክትሉ ፋሲል ተካልኝ ሰላሳ ሺህ እና የግብ ጠባቂዎቹ አዛዥ ዓሊ ረዲ ሃያ አምሥት ሺህ ብር ተሸልመዋል። 

ከተጫዋቾች ደግሞ የግብ መሥመሩ ታማኝ ታሪክ ጌትነትን ጨምሮ አራቱንም ጨዋታዎች ቇሚ ተሠላፊ የነበሩት እያንዳንዳቸው ሠላሳ ሺህ ብር ተሸልመዋል። በሁለተኛው ምድብ የተቀመጡት ደግሞ ሃያ አምስት ሺህ ብር ተበርክቶላቸዋል። በዚህ ምድብ አስቻለው ግርማን ጨምሮ ከአራት ጨዋታዎች በአንዱ ወይም በሁለቱ ተቀይረው የገቡ ወይም የወጡ ናቸው። 

ሃያ ሺህ ብር የተሸለሙት ደግሞ ሳስተኛ ደረጃ ተቨላሚዎች ሲሆኑ በዚህ ምድብ ቢኒያም አሰፋ እና በሀይሉ አሰፋ ይገኙበታል። እነ ኤልያስ ማሞ እና አቤል ማሞ ደግሞ 15 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆነዋል። ከአግዳሚ ወንበር ያልተነሱት ደግሞ አስር ሺህ ብር በመሸለም የበረከቱ ተካፋይ ሆነዋል።

ፌዴሬሽኑ ከተጫዋቾችና አሠልጣኞች በተጨማሪ የቡድኑን ሀኪሞች፣ ትጥቅ ተቆጣጣሪዎችና የቡድን መሪዎቹንም አመስግኗል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Naod [835 days ago.]
 ጥሩ አድርጓል ፌዴሬሽኑ ከፊታቸው ለሚጠብቃቸው ወሳኝ ጨዋታዎች ሽልማቱ ጥሩ ማነቃቂያ ይሆናቸዋል ለተጫዋቾቹ የአሰልጣኙን መሸለም ግን አልቀበለውም በዚህ ግትር አምባገነን አቋሙ ሽልማት መስጠት ይባስ ......................ሆሆሆሆሆሆ Kim Jong-un ሁንብን እንደማለት ነው !

Mali [835 days ago.]
 አሰልጣኙ ምን ስለ ሰራ ነው 50,000 ብር የተሰጠው ? አምባገነን ስለሆነ ? ከህዝብ ጋር ስለተጣላ ? ወይስ የቡርንዲውን ተጫዋች በእጅ ምልክት ስለተሳደበ ??????????

felexsami [835 days ago.]
 እኔ ግርም የሚለኝ ስለ ዮሃንስ አምባገነንነት ምክትል ኮቾቹ ፋሲልና አሊ ለምን ዝምታን እንደመረጡ ግርም ነው የሚለኝ:: የሚሰጡትን ሃሳብ የሚቀበላቸው አይመስለኝም I dont think so.

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!