በሶስት ምድብ የተከፈለው የሴካፋ ውድድር በሶስት ከተሞች ይካሄዳል
ህዳር 01, 2008


በይርጋ አበበ

በአፍሪካ ምድር ከሚካሄዱ እድሜ ጠገብና እድገት አጠር የእግር ኳስ ውድድሮች መካከል ቀዳሚ የሆነው የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋነጫ ወይም ሴካፋ ከኅዳር 11 እስከ 25 ድረስ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የሚካሄድ ይሆናል። ውድድሩን ለማዘጋጀት ኃላፊነት የተጣለባት ኢትዮጵያም አደራውን ለመወጣት ከሰሜን እስከ ደቡብ ኢትዮጵያ ያሉ ያላለቁ እና በእድሜ ብዛት ያረጁ ስታዲየሞቿን ለመጠቀም እንደተገደደች ተነግሯል።

በዚህም መሰረት በምድብ አንድ የተደለደሉት አስተናጋጇ ኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳን፣ ታንዛኒያን እና ሶማሊያን ሲሆኑ፣ ኬኒያ ዩጋንዳ ብሩንዲ እና ጂቡቲ በምድብ ሁለት እና በምድብ ሶስት ደግሞ ከአራት ዓመታት በፊት እንደ ዶሮ ብልት የተገነጣጠሉትን ሁለቱን ሱዳኖች መለትም ደቡብ ሱዳን እና ሱዳንን፣ ተጋባዧን ማላዊን እና ዛንዚባርን አገናኝቷል።

ውድድሮቹ የሚካሄዱት በእድሜ ጠገቡ የአዲስ አበባ ስታዲየም፣ ግንባታው ገና ባልተጠናቀቀው የባህር ዳር ብሔራዊ ሁለገብ ስታዲየም እና አርቲፊሻል ሳር በለበሰው የሀዋሳ ስታዲየም ነው። የምስራቅ አፍሪካን ዋንጫ ኢትዮጵያ አራት ጊዜ ስታነሳ ሁለቱን ዋንጫዎች ማንሳት የቻለችው በአስራት ኃይሌ አሰልጣኝነት ሲሆን አንዱን ደግሞ በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው መሪነት ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ዋንጫን ሁለት ጊዜ ያነሳው ሩዋንዳ ኪጋሊ ላይ ሲሆን ሁለቱን ደግሞ አዲስ አበባ ላይ ነው።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Yirga andarge [800 days ago.]
 ዘገባው ስተት አለበት ምድቡ የሚለው ኢትዮዽያ;ሶማሊያ;ዛምቢያና ታንዛንያ ናቸው ሩዋንዳ እኛ ምድብ አይደለችም ተጋባዥ አገር ማላዊ ሳትሆን ዛምቢያ ናት

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!