የፈረሰኛቹ ራምኬል ሎክ የቅዳሜው ጨዋታ እንዳያመልጠው ተሰግቷል
ህዳር 01, 2008

በይርጋ አበበ

የዋልያዎቹ እና የፈረሰኞቹ ጎል አዳኝ ራምኬል ሎክ ባለፈው ዓመት ከሰዎች ጋር ገጥሞት በነበረው ግጭት ምክንያት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል። ይህን ተከትሎም የፊታችን ቅዳሜ ከኮንጎ ብራዛቢል ጋር በሚያደርጉት የዐለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ላይሰለፍ ይችላል ተብሎ ተሰግቷል። 

ራምኬል ከከሳሾቹ ጋር መስማማት ችሎ ክሳቸውን እንዲያነሱ ማድረግ ከቻለ ወይም ፍርድ ቤት ራምኬል ጉዳዩን በውጭ ሆኖ እንዲከታተል የዋስትና መብቱን ከፈቀደለት በቅዳሜው ጨዋታ ይሰለፋል። 

በሌላ ዜና ዋልያዎቹ ለቅዳሜው ደዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ልምምዳቸውን አጠናክረው እየሰሩ ይገኛሉ። ዛሬም ቡድኑ ከሁለት ተከፍሎ ጌም ያደረገ ሲሆን አንደኛው ቡድን አምስት ለባዶ አአሸንፏል። አምስቱን ጎሎች ያስቆጠሩት ዳዊት ፈቃዱ ሶስት እና ጌታነህ ከበደ ደግሞ ሁለቱን አስቆጥሯል። 

የመከላከያው አማካይ ተከላካይ በሀይሉ ግርማ በጨዋታው ጥሩ ብቃት ያሳየ ሲሆን ምናልባትም በነጥብ ጨዋታዎች ከጋቶች ፓኖም ቀድሞ የመሰለፍ እድል ይኖረዋል ተብሎ እንዲጠበቅ ተስፋ እንዲጣልበት ሆኗል። 

ከውጭ አገር የተጠሩት ተጫዋቾች ብሐራዊ ቡድኑን የተቀላቀሉ ሲሆን በዛሬው ጨዋታም ጌታነህ ከበደ እና ሽመልስ አበራ ተሰልፈው ተጫውተዋል። ዋሊድ አታ በበኩሉ ዛሬ ከቱሪክ መነሳቱን ለኢትዮፉትቦል ዶትኮም ተናግሯል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
yirga andarge [833 days ago.]
 ጌታነህ እና ዳዊት መጣመር ከቻሉ ጥሩ ጨዋታ እናያለን ብየ አስባለው በተለይ እማሀል ሽመልስና ኤልያስ ማሞ አብረው ቢጣመሩ መልካም ነው ግን ዋናው አሰልጣኙ ነው

Yoni Sanjawe [833 days ago.]
 @ ethiofootball.com ከሰዎች ጋር በፈጠረው ግጭት ምክንያት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል its not fair በፈጠረው ችግር ሳይሆን ሰዎቹ በፈጠሩበት የዘረኝነት ችግር ተብሎ ይስተካከል::

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!