የብሔራዊ ቡድን የመጨረሻዎቹ 18 ተጫዋቾች ከነገ ጠዋት ልምምድ በኋላ ይታወቃሉ
ህዳር 03, 2008

- ዋሊድ አታ ላይሰለፍ ይችላል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ነገ ከቀኑ አስር ሰዓት ከኮንጎ ብራዛቢል ጋር ላለበት የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ተጫዋቾቹ በጥሩ ዝግጅትና የማሸነፍ ስነ ልቦና ላይ እንደሚገኙ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ተናገሩ። አሠልጣኝ ዮሐንስ ከውጭ አገር ከመጡት ተጫዋቾች መካከል አጥቂው ጌታነህ ከበደ በልምምድ ሜዳ እና ቡድኑ እርስ በእርስ ባደረገው ግጥሚያ ከሌሎች አጥቂዎች የተሻለ ብቃት አሳይቷል ሲሉ ተናግሯል። 

Head Coach Yohanse Sahle briefing journalists for the Congo game


ከውጭ አገር የሚመጡት ተጫዋቾች ብቃታቸውን የምናውቅበት እድል ስላልነበረን ቀደም ብለው ቡድኑን እንዲቀላቀሉ አድርገናል ሲል የተናገረው ኢንስትራክተር ዮሐንስ፤ ልጆቹም በተለይ ሽመልስ በቀለ እና ጌታነህ ከበደ በተባሉት ቀን መገኘት ችለዋል። ዋሊድ ግን በትራንስፖርት ችግር ዘግይቶ ቡድኑን መቀላቀሉን ተናግረዋል።

 አሰልጣኝ ዮሐንስ አያይዘውም ስለተከላካዩ ዋሊድ አታ ሲናገሩ ዋሊድ አታ አየሩ እንዳልተስማማውና በትናንቱም ሆነ በዛሬው ልምምድ በተገቢው መጠን እንዳልሰራ የተናገሩ ሲሆን ነገ ጠዋት ቡድኑ በሚያካሂደው ልምምድ የዋሊድን መጨረሻ አንደሚያውቁ ነው የገለጹት። አሠልጣኙ የመጨረሻውን 18 አባላትን የያዘውን ቡድኑን ይፋ ማድረግ እንዳልተቻለም ተናግረዋል። ቡድኑ የመጨረሻ ልምምዱን የሚሠራውም ነገ ከንጋቱ 12:30 እስከ አንድ ሰዓት ይሆናል ብለዋል። 

ሁለቱ ቡድኖች ነገ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን አካሂደው የመልሱን ጨዋታ ደግሞ የፊታችን ረቡዕ በኮንጎ ብራዛቢሏ መዲና ያካሂዳሉ። አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌም ቡድኑ ቀጣዩን ዙር እንዲቀላቀል የሚያስችለውን ውጤት እንዲያስመዘግቡ ነገ በሜዳቸው የሚያካሂዱትን ጨዋታ በበላይነት እንደሚወጡ ተናግረዋል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
vibvngba [762 days ago.]
 1

vibvngba [762 days ago.]
 1

vibvngba [762 days ago.]
 1

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!