የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚ አባሉን አገደ
ህዳር 04, 2008

ፈለቀ ደምሴ

የኢትዮጵያ የሴት እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን ከካፍ በተከታታይ ለ4 ግዜ የተላከለትን የምዘገባ ጥሪ በአግባቡ ተቀብሎ ምዝገባ ባለማድረጉ ምክኒያት  ካሜሩን ላይ ከሚዘጋጀው የሴቶች የ2016 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ውጪ መሆኑን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥፋተኛ ናቸው ያላቸውን የጽህፈት ቤት ሀላፊውን አቶ ዘሪሁን ቢያድግልኝን እና የአይቲ  ባለሙያዋን ወይዘሮ ዘውድነሽ ይርዳውን ከስራ ማሰናበቱን እንዲሁም ሥራቸውን ባግባቡ አልተወጡም ያለቸውን የፌዴሬሽኑ የቡድን መሪ የሥራ አስፈጻሚ አባልና እና የሴቶች እግር ኳስ የበላይ ሀላፊ የሆኑትን  አቶ ዮሴፍ ተስፋዬን ማገዱን አርብ ህዳር 3ቀን ከጠዋቱ 3 ሰአት ኢንተር ኮንትኔታል ሆቴል ላይ በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አሳውቋል፡፡
eff conference on women s football


ፌዴሬሽኑ መግለጫውን በሰጠበት ቀን 12 ሰአት ላይ በፌዴሬሽኑ እገዳ  የተጣለባቸው አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ በሂለተን ሆቴል ጋዜጠኞችን ጠርተው መግለጫ የሰጡ ሲሆን በመግለጫቸውም "እገዳው ያለአግባብ ነው የተደረገብኝ ሁሉም የሥራ አስፈጻሚ በጋራ ኃለፊነቱን መውሰድ አለብን በማለት ሰፊ ማብራሪያ ሰጥጠዋል፡፡"

eff central comeete

በፌዴሬሽኑ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ለፌዴሬሽኑ ባለስልጣናት ከጋዜጠኞች  ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን አቶ ዮሴፍ በጠቅላላ ጉባኤ የተመረጡ ስለሆነ  እናንተ ማገድ ትችላላችሁ ወይ?  ለምንስ አዚህ ተገኝቶ ለመናገር እድል አልተሰጠውም ? ፌዴሬሽኑ ለወንዶቹ እና ለሴቶቹ ብ/ቡድን አኩል አመለካከት አለው ወይ? ክለቦች በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ አንዲሰጣቸው እየጠየቁ ነው አንድ ክለብ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ ጠይቋል ይህን እዴት ታዩታላችሁ ?  አቶ ጁነዲን የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ካይሮ ድረስ ሄደዋል እዚሁ ሆነው በኢሜል እና በፋክስ መጨረስ አይችሉም ነበር ወይ?ፌዴሬሽኑ መግለጫን ለመስጠት አልዘገየምን ? ለጥፋቱ የታገዱት ብቻ ናቸው ተጠያቂዎቹ እናንተስ ሃላፊነት ወስዳቸሁ ይቅርታ ለምን አትጠይቁም ?የሴቶች ቡድን አናቋቁም ሲሉ የነበሩ ክለቦች አናንተን ተጠያቂ እያደረጓችሁ ነው ነገ ቡድናቸውን ቢያፈርሱ ምን ማድረግ ትቸላላችሁ? ይህ ሌላ ችግር አያመጣምን ?የቡድን መሪ በየጊዜው ለምን ይቀያየራል ከመሃከላችሁ እግር ኳስን ተጫውተው ያለፉ እና በኢንተር ናሽናል ዳኝነት በካፍ እና በፊፋ ያገለገሉ ባለሙያዎች  እያሉ አቅምና ችሎታ የሌላቸው ለምን ይመደባሉ ? የአይቲ ባለሙያዋ የታገደችበት ምክኒያት ምንድን ነው? በስራችሁ ለይ አማተር አገልጋይ መሆናችሁ ችግር አይፈጥርባችሁም? በመተዳደሪያ ደንባችሁ አንቀጽ 36 መሰረት ፕሬዘዳንቱ የጽሕፈት ቤቱን ሓላፊ ስራ ይቆጣጠራሉ ይላል 4ኛ ቁጥር ላይ በስራ አስፈጻሚ አባላት መካከል ያለውን ልዩነት በበላይነት ይመራል ይላል 7ኛው ላይ ደግሞ የፌዴሬሽኑ ሥራዎች በትክክል መሰራታቸውን የማረጋገጥ ሓለፊነት አለበት ይላል መተዳደሪያ ደንቡ አንዲህ የሚል ከሆነ አቶ ጁነዲን ተጠያቂ ስለሚሆኑ ለምን በፈቃደኝነት ስራ አይለቁም ?

ከላይ ለተጠየቁት ጥያቄዎች አቶ ጁነዲን ሲመልሱ አቶ ዮሴፍን ህጉ በሚፈቅድልን መሰረት ጊዚያዊ እገዳ ነው ያደረግነው ሙሉ ለሙሉ ስልጣን ያለው ጠቅላላ ጉበኤው ነው በዚህ መድረክ እዲገኝም ጋበዝነው ፍቃደኛ አልሆነም እኔ ካፍ በሄድኩበት ጊዜ እጣው ከመውጣቱ በፊት ብትነግሩን ኖሮ መፍትሄ ይኖረው ነበር ስላሉን እሱም ይሄን ባለማድረጉ ነው ካፍ ካይሮ በሄድኩበት ወቅት የተለያዩ ጉዳዩን የሚመለከታቸውን የካፍ ሰዎች እስከ ኢሳ ሃያቱ ድረስ በማናገር ባደረግነው ጥረት ከተመዘገቡት ተወዳዳሪ ሀገራት በሚወጣ ቡድን ሊያስገቡን ቃል ገብተውልናል ይህም እድል በኔ ግምት ሀምሳ ሀምሳ ነው እድሉ ይህን በጽሁፍ ጭምር ሰጥተውናል።  ለሴቶቹ ትኩረት አትሰጡም ለተባለው አሁን ጥሩ ውጤት ያሥመዘገበውን ከ20 አመት በታች ቡድን ያልነበረውን ይህ ስራ አስፈጻሚ አይደል እንዴ ያቋቋመው ይህ ችግር ሳይፈጠር በፊትስ ከ17 አመት በታች ቡድን አዲቋቋም አድርገናል  ተጫዋቾቹን እና ቡድን መሪዎችን ጠይቁ እስቲ ከሃገር ውጪም ቡርኪና ፋሶ ጋና በሀገር ውስጥ ከባህር ዳር እሰከ ሃዋሳ  በየጊዜው እየደውልን በቦታው እየተገኘን አልተከታተልንም። ጋዜጠኛ ደግም አንተ ከቡድኑ ስላልተለየህ ልትመሰክር ትችላለህ ታዲያ ምኑ ላይ ነው ትኩረት ያልሰጠነው ይህ ሰህተት ስለተፈጠረ ከፆታ ጋራ ባናገናኘው ጥሩ ነው፡፡ ክለቦች ማብራሪያ ስጡን ላሉት አሁን ስራችንን ስለጨረስን ማብራሪያውን እነሰጣቸዋለን። ጠቅላላ ጉባኤ ይጠራ ለተባለው ጠቅላላ ጉባኤ የሚጠራበት የራሱ ህግ አለው። የካይሮ ጉዞ ለምን አስፈለገ ለተባለው በግምባር ሄደን በመነጋገራችን እደሉ የሚመቻችበትን ተስፋ ይዘን መጥተናል ሙሉ ለሙሉ ቢሳካልን ኖሮስ እንደሃላፊነት ጠፋ ብሎ ከመቀመጥ መሞከሩ የተሻለ ነው፡፡ ዮሴፍ ብቻ ነው ወይ እናንተስ አላጠፋችሁም ወይ ለተባለው ለዚህ ነው ይህንን መግለጫ ያዘጋጀነው፡፡ መግለጫ ለመስጠት ዘገያችሁ የተባለው ልክ ነው ግን ነገሮችን በደንብ አጣርተን ለማቅረብ በማሰብ ነው፡፡ 

ፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አበበ ገላጋይ በበኩላቸው  አቶ ዮሴፍ ፌዴሬሽኑን ወክለው ካይሮ በሄዱበት ወቅት በስብሰባው ለይ ከተሰጣቸው 11 አጀንዳ አንዱ በካሜሩን አዘገጅነት የሚዘጋጀው የ2016 የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ጉዳይ ተነስቷል የሴቶች ብ/ቡድን ችግሩን ለማስተካከል እድሉም ነበር እሳቸው ግን አላየሁም ብለዋል ሰነዱን አቶ ጁነዲን ይዞ ስለመጣ እያንዳዱን ጉዳይ መርምረን ነው ውሳኔ የሰጠነው፡፡

ፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ቾክ በሃገር ጉዳይ መነጋገራችን ጥሩ ነው። እኛ እንደ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ በነበረው ችግር ለህዝቡ ይቅርታ ነው መጠየቅ ያለብን። አንድ የኛ ዲፓርትመንት ሰራተኛ ላደረገው ስህተት ውድቀት እንደሆነ በሚገባ መርምረን አይተናል። በዚህም አቶ ዮሴፍ የናንተ አባል በስብሰባው ላይ ነበር ተብሎ ከካፍ ደብዳቤ ስለተጻፈልን እና ከቡድን መሪነቱ በተጨማሪ የሴቶች ቡድን የልማት ኮሚቴ ሰብሳቢ ስለነበረ ተጠያቂ አድርገነዋል ፡፡

አቶ ጁነዲን፡-  ኃለፊነቱን በጋራ እንወስዳለን። አማተር መሆናችሁ  ያስቸግራችኋል ለተባለው አዎ ያስቸግራል በተለያየ ቦታ ተሆኖ ነው የሚወሰነው በየቀኑ ተገናኝቶ አይሠራም የቡድን መሪን በተመለከተ እንደሰዉየው ሁኔታ ነው የምንወስነው የተመደቡት ሰዎች በግል ሥራ ምክኒያት ሲሄዱ የሚመቸውን አንመድባለን ከዚህ ቀደም የነበረው አሰራር እዲህ ሰለነበረ ነው። ወደፊት እንደ ሁኔታው እናየዋለን ከካፍ መልእክቶች ሚመጡት በኢሜል ነው ቦታው ላይ ያለ ስው ከላሳወቀ እንዴት ነው ተጠያቂ የማይሆነው  ስልጣንን በተመለከተ ይሄን ያህል ሙጭጭ ተብሎ በጉጉት የሚቀመጡበት አይደለም ይሄ ነገር ቀርቦልኝ ይሄን ሳላደርገው ስለቀረሁ የምል በት እና ህሊናዬን የሚያስጠይቅ ነገር ቢኖር አደርገዋለሁ እንደ አገር አደራ ጉዳዩ ያማል በግሌ ግን ቀርቦልኝ መልስ ያልሰጠሁበት ነገር የለም ፡፡ 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተቋም በይፋ ይቅርታ መጠየቅ ነበረበት በማለት ጋዜጠኞች ለፌዴሬሽኑ ቅሬታቸውን አሰምተዋል ፡፡

አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ በግላቸው በጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገኝቼ ለመናገር ታግደሀል ስለተባልኩ እና እኔን በተመለከተ የተሰጡት መግጫዎች ተአማኒነት የጎደላቸው በመሆኑ እና ሃሳቤን የመግለጽ መብት ስላለኝ ነው ይህን መድረክ ያመቻቸሁት በማለት በሴቶች ብሄራዊ ቡድን ለተፈጠረው ስህተት የሉሲዎቹን ቡድን አባላት እና የኢትዮጵያን ህዝብ እጅግ በተሰበረ ልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ ብለዋል ፡፡
Ato Yosef Tesfaye

የፌዴሬሽኑ የቡድን መሪ እና የሴቶች እግር ኳስ ሰብሳቢ እና በካፍ የሴቶች ቡድን ተውካይ ነኝ በዚህም መሰረት በለፉት አመታት ስራዬን ባገባቡ የተወጣሁ ሲሆን አንተ በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ልምዱ እና እውቀቱ ስላለህ በማለት ሀላፊነቱን የሰጠኝ ፌዴሬሽኑ ነው ፡፡ብሄራዊ ቡድኑ ምዝገባው እንዳመለጠው ሁላችንም የሥራ አስፈጻሚዎች በወቅቱ አላወቅንም ነበር እኔ በተካፈልኩበት የካፍ ሥብሰባ ላይ እጣ አልወጣም አንዳንድ ሚዲያ ላይ የተነገረው ትክክል አይደለም በእለቱ ስለምዝገባ የተነሳ ነገርም የለም እኔ ከዚህ ሳልነሳ ገና ሁሉም ነገር አብቅቷል። ካፍም ለምን አልተመዘገባችሁም ሊለኝ አይችልም አላለኝም ምክኒያቱም ኦገስት 31 ላይ ምላሽ ባለመስጠታችን ነገሩ አብቅቶለታል ይህ ደግሞ የጽህፈት ቤቱ ችግር ብቻ ሳይሆን ሙሉ ለሙሉ የሁላችንም ተጠያቂነት ነው። በዚህ መሰረት በኔ ላይ ብቻ የተወሰነው ውሳኔ አግባብ አይደለም ለኔ  ሥራ አስፈጻሚ ውሳኔውን የወሰኑበት መንገድ  ሕዝቡ በተፈጠረው ነገር ተቆጥቷል ሚዲያውም ሊያስቀምጠን ሥላልቻለ ውሳኔውን ተቀበል ሁኔታውን አይተን ከ15 ቀን በዃላ ወደቦታው አንመልስሃለን ሲሉኝ የሄዱበት መንገድ አግባብ ስላለሆነ እገዳውን ተቃውሜአለሁ ከዚህ ቀደም በፌዴሬሽኑ ውስጥ የነበሩ የአሰራር ችገሮችን እቃወም ስለነበር ከተወሰኑት የሥራ አስፈጻሚዎች ጋር መቃረን ነበረኝ ከዚህም ውስጥ የአቶ ሰውነት መባረር እና የባሬቶ መምጣት እና በተጨማሪ መባረሩ ላይ መንግስት የሰራተኛ ደሞዝ ጨምሮ የኛ ሰራተኞች ከአመት በላይ ጠይቀው ምላሽ ባለማግኘታቸው ይሕን በመጠየቄ በሽልማት አሰጣጥ እና በተለያዩ ችግሮች ላይ በቀናነት ፌዴሬሽኑን መምራት ስላልቻሉ ፕሬዘዳንቱ በፈቀደኝነት ስልጣናቸውን አዲለቁ ጥያቄ አቅርቤአለሁ በማለት አሁን ፌዴሬሽኑ ከወሰነባቸው የእገዳ  ውሳኔ ጋር ያቀርቡት የነበረው ተቃውሞ ሊያያዝ እንደሚችል በማስገንዘብ የፌዴሽኑን ውሳኔ እንደሚቃወሙት ገልጸዋል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
phjwuoap [829 days ago.]
 1

phjwuoap [829 days ago.]
 1

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!