የቀድሞው ኢንተርናሽናል ዳኛ ልዑል ሰገድ በጋሻው ወደ ናይጄሪያ አቀኑ
ህዳር 05, 2008

ፈለቀ ደምሴ

ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ ናይጄሪያ ከሲዋዚላንድ ለሚያደርጉት የመልስ ጨዋታ ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ልዑል ሰገድ በጋሻው የሁለቱን ሀገሮች ጨዋታ በኮሚሽነርነት እዲመሩ በፊፋ ተመርጠው ወደ ናይጄሪያ ዛሬ አቅንተዋል።
Leulsegede Gashaw

ናይጄሪያ ከሲዋዚላንድ ህዳር 4 ቀን 2008 ዓ.ም ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ 0ለ0 የተለያዩ ሲሆን በመጪው ማክሰኞ የመልስ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል። 

አቶ ልኡል ሰገድ በጋሻው  በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈጻሚ  አባል ናቸው። በዳኝነት ዘመናቸውም በኢንተርናሽናል ውድድሮች ላይ ረዳት በመሆን ኢትዮጵያን በመወከል የተሳተፉ ሲሆን በ2004 በቱኒዚያ በተዘጋጀው 24ኛው እና በ2006 ግብፅ ባዘጋጀችው 25ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በረዳት ዳኝነት መርተዋል።

በምስራቅ አፍሪካ የብሄራዊ ቡድኖችና ክለቦች ሻምፒዮናዎች ቡርኪናፋሶ ባስተናገደችው የአፍሪካ ወጣቶች ሻምፒዮና ፣ፈረንሳይ ባስተናገደችው  የአውሮፓ ታዳጊዎች ሻምፒዮና ፤ በሆላንድ አስተናጋጅነት በተከናወነው የዓለም ወጣቶች ሻምፒዮና ላይ ውድድሮችን በረዳት ዳኝነት መርተዋል። በ2008 ጀርመን ባዘጋጀችው የአለም ዋንጫ እንዲመለከቱ ከተመረጡት እጩ ዳኞች አንዱ በመሆን ተጉዘዋል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!