ዋልያዎቹ ከዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በጊዜ ተሰናበቱ
ህዳር 07, 2008

በይርጋ አበበ 

የምስራቅ አውሮፓዋ ሀያል አገር ሩሲያ ለምታዘጋጀው 21ኛው የዓለም ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ሲያካሂድ የቆየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ በኮንጎ ብራዛቢል አቻው ተሸነፈ። ከማጣሪያው ውጭም ሆኗል። ነገ ወደ አገሩ ይመለሳል።
የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ ዛሬ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በኮንጎ ብራዛቢሉ ስታዴ አፎንሶ ስታድየም የተካሄደ ሲሆን ዋልያዎቹ ጎል በማስቆጠር ቀዳሚዎች ነበሩ። የጎሏ ባለቤት ደግሞ የቀድሞው የደቡብ ፖሊስ አጥቂ ጌታነህ ከበደ ነው። 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ በኮንጎ ቢሸነፍም የፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በሚካሄደው የሴካፋ ዋንጫ እና ጥር 7 ቀን በሚጀመረው የቻን ዋንጫ ይወዳደራል። በሴካፋ ዋንጫም ለድል ከሚጠበቁት ቡድኖች ቀዳሚው ነው።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Mali [794 days ago.]
 ከሴካፋም ዋንጫ በጊዜ የሚሰናበት ይምስለኛል ብሔራዊ ቡድናችን :: ምክንያቱም ጥሩ አሰልጣኝ አይደለም ያለን ምንም እንኳን ጥሩ ጥሩ ብሔራዊ ቡድናችንን መጥቀም የሚችሉ ተጫዋቾች ቢኖሩንም በዮሃንስ አምባገነንነት እነ ምንተስኖት .... ተስፋዬ..... በሃይሉ.... አስራት..... ባዬ..... ናቲ..... አይነት ልጆች አለመመረጣቸው በጣም ያሳምማል:: shame on you Yohanes !

Gizegeta [793 days ago.]
 ብሔራዊ ቡድናችን በኮች ሰር ሰውነት ቢሻው እየተመራ እየሰለጠነ ቢሆን ኖሮ atleast ቡድናችን ኮንጎን ማሸነፍና ወደ ቀጣዩ የምድብ ድልድል ውስጥ መግባት አያቅተውም ነበር :: በዮሃንስ እስከተመራን ድረስ ምንም ጥሩ ነገር አንጠብቅም ሴካፋ ላይ ምንም ነገር ለቡድኑ ይሰራል ብዬ ተስፋ አላደርግም::

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!