የአርሰናል ኮቺንግ ስታፍ ከዳሽን ቢራ ጋር በመተባበር በሱሉልታ ሲሰጥ የቆየውን የአሰልጣኞች ስልጠና ትላንት ማምሻውን አጠናቀቀ።
ህዳር 08, 2008

ፈለቀ ደምሴ 

በዳሽን ቢራና በአርሰናል ስፖርት ክለብ መካከል ቀደም ሲል  በተደረሰ ስምምነት መሰረት ከአርሰናል በመጡ ሁለት የእግር ኳስ አሰልጣኞች በመሰረታዊ የእግር ኳስ ተጫዋቾች አሰለጣጠን ዙሪያ ለሁለት ቀን ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና  ትላንት ማምሻውን ተጠናቋል። ሱሉልታ በሚገኘው ያያ ቪሌጅ ሲሰጥ የቆየው ይህ   ስልጠና የቲዮሪና በተግባር የታገዘ ነበር። ስልጠናውን ሁሉንም የፕሪሚየር ሊግ ዋና አሰልጣኖችና ምክትሎቻቸውን እንዲሁም የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞቸን አካቷል። ስልጠናው እንደተጠናቀቀም ስልጠናውን የሰጡት አሰልጣኞች ለሰልጣኖቹ መልካም የስራ ጊዜንና በሥራቸው ውጤታማነትን ተመኝተዋል። ሰልጣኞቹም  በበኩላቸውም በስልጠናው መደሰታቸውን በሚገልጽ ሁኔታ ከአሰልጣኞቹ ጋር ፎቶግራፎችን በመነሳትና አድናቆታቸውን በግል ለአሰልጣኞቹ ሲገልጹላቸው አስተውለናል።
With Arsenal Trainers

በስለጠናው መጠናቀቂያ ላይ በስልጠናው ለተሳተፉ አሰልጣኞች በሙሉ የአርሰናሉ ዋና አሰልጣኝ  አርሰን ዌንገር ፊርማ ያረፈበትን የምስክር ወረቀትCerteficate ተቀብለዋል።  ሰርተፍኬቱን ለሰልጣኞቹ ያበረከቱት የዳሽን ቢራ ዋና ስራ አስኪያጅ ሚስተር ዴቭሊን ሄይንስዎርዝ ከአሰልጣኖቹ ጋር በመሆን ነበር።  የሰርተፍኬት አሰጣጡም ስነስርአት እንዳበቃ ሚስተር ዴቭሊን ሄይንስዎርዝ  ለአሰልጣኞቹ ዳሽን ቢራ ያዘጋጀላቸውን የሀገር ልብስ ሥጦታ አንጋፋsenior አሰልጣኞች እንዲሰጡላቸው በመጠየቅ  የቀድሞው የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ከሞያ ጓደኞቻቸው ገብረመድህን ሀይሌ፣ ጸጋዬ ኪዳነማርያም እና ውበቱ አባተ ጋር በመሆን ለአሰልጣኞቹ ፋብሪካው ያዘጋጀውን ስጦታ ለአሰልጣኞቻቸው አበርክተዋል። 

Sewnet Bishaw Giving the gift to Arsenal Coaches

Webetu Abate and Tsegaye pictured with the triners

ስልጠናው  ምን የተለየ ልምድና እውቀትን ለሰልጣኖቹ እንዳስጨበጣቸው ለማወቅ ስንል ከሰልጣኞቹ ውስጥ ያገኘናትን በታሪክ ብቸኛዋና የመጀመሪያዋ የፕሪሚየር ሊጉ የሴት አሰልጣኝ የሆነችውን  መሰረት ማኒን አነጋግረናት ነበር።  የሚከተለውን መልስ ሰጥታናለች። 
Meseret Mani

"ከስልጠናው  ያገኘነው ነገር ብዙ ነው። በዋናነት ግን አርሰናል በውጤታማነቱ የሚታወቅበትን የህፃናትና የወጣት እግር ኳስ አካዳሚ አሰለጣጠንና እንዲሁም የአካዳሚውን አሰራርና መዋቅርን   በተመለከተ አሰልጣኞቹ ያካፈሉን ልምድ ነው። ለምሳሌ በህፃናት ስልጠና ዙሪያ ብዙዎቻችን ለህጻናት ይከብዳቸዋል አእምሮዋቸው መቀበል ሊከብደው ይችላል ብለን   በማሰብ ከማናሰለጥናቸው  አንዳንድ የስልጠና አይነቶች ለህፃናት መሰጠት እንደሚችሉና እንዴት በቀላሉ በቀልድና በጨዋታ  መልክ መሰጠት እንደሚችሉ በተግባር አሳይተውናል። ሌላው  ከስልጠናው በዋናነት የምትረዳው ከታች በህፃንነት በየደረጃው  በስፋት መሰረታዊውን የእግር ኳስ  ስልጠና ያላገኘ የእግር ኳስ ተጫዋች  በትልቅ ደረጃ ውጤታማ የመሆን እድሉ ጠባብ መሆኑን ነው። በውጪው አለም  የምናያቸው ተጫዋቾች ከልጅነት ተገቢውን ስልጠና በየደረጃው እያገኙ ስለሚያልፉ በማንኛውም ቦታposition ላይ የሚጫወቱትን ስታይ ሲቸገሩ አይታይም  የኳስ ክህሎታቸውምCreativity ጥሩ ነው።  ወደ ላይ በሚያድጉበትም ጊዜ ከፍ ያለ ስልጠናና የተግባር እንቅስቃሴ ሲሰጣቸው አይከብዳቸውም። ወደኛ ሀገር ስትመጣ  ብዙዎቹ የሀገራችን ኳስ ተጫዋቾች መሰረታዊውን የእግር ኳስ  ስልጠና የሚያገኙት እድሜያቸው ካለፈና በትልልቅ ሊግ ክለቦች ከታቀፉ በኋላ ነው። ይህ በመሆኑም የትልልቅ ሊግ አሰልጣኞች እነዚህን ተጫዋቾች በልጅነታቸው መጨረስ ይገባቸው የነበረውን ስልጠና በመስጠት ይጠመዳሉ በውጤቱም  አሰልጣኞች የሚፈልጉትን ያኽል ውጤት ከተጫዋቾቹ  ለማግኘት ይቸገራሉ። ብሄራዊ ቡድናችንም ላይ የምናየው ችግር አንዱ ከዚህ የመነጨ ነው።  ስለዚህ ነው እግር ኳሳችንን ጥሩ መሰረት ላይ ለመጣል ከታች ጀምረን መስራት ይኖርብናል። ምንም እንኳን በፋይናንስ ጉዳይ  ከኳስ አቅርቦት ጀምሮ የማቴሪያል እጥረት ሊኖር ቢችልም ከትንሹ በመጀመር እያሳደግነው መሄድ እንችላለን። በሁለቱ ቀን ያገኘነውን ጠቃሚ ስልጠናና ልምድ ደግሞ በየክለባችን በምንመለስበት ሰአት በተግባር የሚውልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ጥረት ማድረግ ከኛ የሚጠበቅ ይሆናል። "  ስትል ብቸኛዋ የፕሪሚየር ሊጉ የሴት አሰልጣኝ በስልጠናው ስለተገኘው  ልምድ  ሃሳቧን አካፍላናለች።  

ስልጠናውን የሰጡት አሰልጣኞች በበኩላቸው ሥልጠናው መሰረታዊ የእግር ኳስ አሰለጣጠን ዘዴን  ከታች ጀምሮ የሚያስተምር መሆኑን ተናግረው ሰልጣኞቹ በንቃት የተሳተፉበት በመሆኑ መደሰታቸውን ገልጸዋል።

the trainers

Cultural presentation

እንደዚህ ያሉ በተግባር የታገዙ ሥልጠናዎች  የእግር ኳስ ባለሞያዎቻችንን እውቀትና ልምድ ከማሳደግ አልፎ የሀገራችን እግር ኳስ በአደጉት አገሮች በተለይም በእንግሊዝ የመተዋወቅ እድሉን የሚያሰፋ በመሆኑ  ለተጨዋቾቻችንም ሆነ ለአሰልጣኞቻችን በፕሮፌሽናልነት  የመስራት እድላቸውን የሚያሰፋ ነው። 

ዳሽን  ቢራ ፋብሪካ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ እድገት አጋርነቱን  በማሳየት በአፍሪካ የመጀመሪያ  የተባለለትን ስምምነት ከእንግሊዙ ታላቅ የእግር ኳስ ክለብ አርሰናል ጋር ያደረገውን ስምምነት በአጭር ጊዜ በተግባር በማሳየቱ ሊመሰገን ይገባዋል። ዳሽን ቢራ እያደረገ ያለው በጎ ጅምር ይቀጥል እያልን ሌሎች ድርጅቶችም ሆኑ ክለቦች የዳሽንን አርአያነት በመከተል ለሀገራችን ስፖርት እድገት ተመሳሳይ ስምምነቶችን ቢያደርጉ ይበረታታል እንላለን።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Bedru [793 days ago.]
 Yasebikut tesaka

Bedru [793 days ago.]
 Yasebikut tesaka

Aliyas [793 days ago.]
 እንደዚህ ነዉ z gun

Aliyas [793 days ago.]
 እንደዚህ ነዉ z gun

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!