ኢትዮጵያ ቡና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የእርዳታ ማሰባሰቢያ ጨዋታ አዘጋጀ
ህዳር 09, 2008

በይርጋ አበበ

 ዛሬ ከቀትር በኋላ ለዝግጅት ክፍላችን ክለቡ ባደረሰን መረጃ መሰረት ህዳር 16 እና 19 ቀን 2008 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም እና በባህር ዳር ሁለገብ ብሔራዊ ስታዲየም ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችን አዘጋጅቷል፡፡ የጨዋታዎቹ ዓላማም በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች ገቢ በማሰባሰብ ለችግራቸው በመድረስ አገራዊ ግዴታውን ለመወጣት መሆኑን የክለቡ መግለጫ አመልክቷል፡፡

የኢፌዴሪ ወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር እውቅና የሰጠው ይሄው የበጎ አድራጎት ጨዋታ የሚካሄደው የሴካፋ ጨዋታዎች በሚካሄዱበት ወቅት ቢሆንም በመሃል ባለው የእረፍት ጊዜ እንደሆነ ታውቋል፡፡ አዲስ አበባ ላይ የሚካሄደውን ጨዋታ የሚፋለሙት ቡና ከወላይታ ድቻ ሲሆን ባህር ዳር ላይ የሚካሄደውን ደግሞ ቡና ከዳሽን ቢራ ይሆናል፡፡ ጨዋታዎቹንም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ በሙሉ በስታዲየሞች ተገኝተው ለወገኖቹ እንዲደርስ ክለቡ መልዕክቱን አስተላልፏ፡፡

የክለቡ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ደሰላኝ “አጠቃላይ የስፖርት ቤተሰቡም የአላማውን ትልቅነት በመረዳት  በተጠቀሰው ቀን ፣ ቦታና ሰዓት በመገኘት ድጋፋችሁን እንድታርጉ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ፡፡ በሚድያው በኩልም ለውድድሩ በቂ ሽፋን እንዲሰጠው እየጠየቅን የመግቢያ ዋጋዎቹን በተመለከተ በቅርቡ የምናሳውቅ” ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

ጨዋታዎቹን መመልከት ለምትፈልጉ እንዲያመቻችሁ ከዚህ በታች ፕሮግራሞቹን አቅርበናቸዋል፡፡
ሀሙስ ኅዳር 16 ከቀኑ 11፡30 ኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ድቻ በአዲስ አበባ ስታዲየም!!
እሁድ ኅዳር 19 ከቀኑ 10 ሰዓት ዳሽን ቢራ ከኢትዮጵያ ቡና በባህር ዳር ብሔራዊ ሁለገ ስታዲየም ይካሄዳሉ፡፡ :

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
felexsami [825 days ago.]
 እኔ የማዝነው ሃላ ላይ ለሚያለቅሱት ወላይታ ድቻና ዳሽን ስፖርት ክለብ ነው ቡላ ገለባን ካሸነፉት ደጋፊው ሰርቪሳቸውን ወንፊት ነው የሚያደርጉላቸው ስፖርታዊ ጨዋነት የማያውቅ ክለብ ቢኖር ቡላ ገለባ ነው::

Marta [825 days ago.]
 ቡና የተባለ ክለብ አይመቸኝም በደጋፊዎቹ ድንጋይ ከተፈነከቱት ስፖርት ወዳድ ሰዎች አንዱ እኔ ነኝ:: ስለዚህም ቡና ከማንም ጋር ቢጫወት ስታዲየም ገብቶ እነሱን ማየት ምቾት አይሰጠኝም:: በዚህ ላይ የስድብም ዲፕሎማና ዲግሪ ባለቤቶች ናቸው ምኑን የድንጋይ ብቻ :: sorry ወገኔን ስታዲየም ገብቼ ብደግፍ ጥሩ ነበር .......ግን ድንጋያቸውን ስለምፈራ መግባት ፈራሁኝ ....... በቃ ስታዲየም ሄጄ ከፍዬ እወጣለሁ::

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!