ሴካፋ ነገ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ይጀመራል
ህዳር 10, 2008

በይርጋ አበበ

የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ነገ በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ይጀመራል።  ጨዋታው የሚጀምረው ከቀኑ ስምንት ሰዓት ሲሆን የመጀመሪያውን ጨዋታ የሚያካሂዱትም በምድብ ሁለት የተደለደሉት ብሩንዲ እና ዛንዚባር ናቸው። ለአራተኛው የቻን ዋንጫ ለማለፍ ከዋልያዎቹ ጋር 180 ደቂቃ ተፋልመው ቡጁንቡራ ላይ ሁለት ለባዶ አሸንፈው አዲስ አበባ ላይ ሶስት ለባዶ የተረቱት ብሩንዲዎች በዛንዚባር አቻዎቻቸው ላይ የአሸናፊነት ግምት አግኝተዋል።

በምድብ አንድ የተደለደሉት አስተናጋጇ ኢትዮጵያ እና የክፍለ አህጉሩ ጠንካራ ቡድን የሆነው ሩዋንዳ ከቀኑ አስር ሰዓት ይገናኛሉ።   በወጣቱ አየርላንዳዊው  ጆኒ ማክስተረይ- Johnny McKinstry-  የሚሰለጥኑት ሩዋንዳዎች ለዋልያዎቹ ፈታኝ እንደሚሆኑ ይጠበቃሉ። የፊታችን ጥር የቻን ዋንጫን የምታዘጋጀው ሩዋንዳ በዚያ ውድድር ጠንካራ ቡድን ይዛ ለመቅረብ ከነገ ጀምሮ የሚካሄደውን የሴካፋ ዋንጫን ለቡድኗ ማዘጋጃ እንደምትጠቀምበት ይጠበቃል። በበዚህም ምክንያት ቡድኑ ካለው ወቅታዊ ጠንካራ አቋም እና ከአሰልጣኙ ጠንካራ ታክቲካል ብቃት አኳያ በነገው ጨዋታ ጠንካራ ፉክክር የሚታይበት ጨዋታ ያደርጋሉ ተብሎ ይገመታል።

የአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ከኮንጎ ብሔራዊ ቡድን ጋር ላደረገው ግጥሚያ ከተመረጡት 26 ተጫዋቾች መካከል ሶስቱ ብቻ ማለትም ከውጭ አገር የመጡት ዋሊድ አታ፣ ጌታነህ ከበደ እና ሽመልስ በቀለ በስተቀር ቀሪዎቹ 23 ተጫዋቾች ለሴካፋው ውድድር የተዘጋጁ ናቸው። ከዚህ ውስጥ ግን የዳዊት ፈቃዱ በጉዳት ከውድድሩ ውጭ መሆን አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ፊታቸውን ወደ ሌሎች አማራጮች እንዲያዞሩ ያደርጋቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
jon [824 days ago.]
 በቀድሞው የፈረሰኞቹ አለቃ ሰርዲዮቪች ሚሉቲን ሚቾ የሚመሩት የፖል ካጋሜ ልጆች ሩዋንዳዎች ለዋልያዎቹ ፈታኝ እንደሚሆኑ ይጠበቃሉ። አረ በፈጠራችው ኢትዮ ፉትቦሎች ተሳስታችዋል ሚሉቲን ሚቾ የኦጋንዳ ብሔራዊ ብድን አሰልጣኝ እንጂ የሩዋንዳ አይደለም አስተካክሉ

jon [824 days ago.]
 በቀድሞው የፈረሰኞቹ አለቃ ሰርዲዮቪች ሚሉቲን ሚቾ የሚመሩት የፖል ካጋሜ ልጆች ሩዋንዳዎች ለዋልያዎቹ ፈታኝ እንደሚሆኑ ይጠበቃሉ። አረ በፈጠራችው ኢትዮ ፉትቦሎች ተሳስታችዋል ሚሉቲን ሚቾ የኦጋንዳ ብሔራዊ ብድን አሰልጣኝ እንጂ የሩዋንዳ አይደለም አስተካክሉ አሁን ያሉት የሩዋንዳ ብሔራዊ ብድን አሰልጣኝ Johnny McKinstry ናቸው::

ethioootballmoderator [823 days ago.]
 Dear jon, Thanks or the reminder, we made the correction.

ethioootballmoderator [823 days ago.]
 Dear jon, Thanks or the reminder, we made the correction.

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!