ሳላዲን ባርጌቾ ዋልያዎቹን አምበልነት ይመራል
ህዳር 11, 2008

በይርጋ አበበ

ዛሬ ከደቂቃዎች በኇላ በሚጀመረው የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ አገሮች ዋንጫ ጨዋታ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሳላዲን ባርጌቾን አምበል አድርጎ መምረጡን አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ አስታወቁ።

አሠልጣኝ ዮሐንስ ከደቂቃዎች በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አምበሉ ስዩም ተስፋዬ እረፍት፣ ታሪክ ጌትነት እና ዳዊት ፈቃዱ በደረሰባቸው ጉዳት ከውድድሩ ውጭ ሆነዋል። የምንጫወተውም ዋንጫ ለማንሳት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ብሔራዊ ቡድናችን ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ተደጋጋሚ ጨዋታ ምክንያት በተጫዋቾቹ ላይ ጉዳት እና ድካም እንዳሳረፈባቸው አሠልጣኙ አክለው ተናግረዋል።

ተጋጣሚዎቻችሁን ምን ያህል ታውቃቸለህ ተብለው የተጠየቁት ኢንስትራክር ዮሐንስ ሲመልሱ"ተጋጣሚዎቻችንን የምናውቅበት እድል አልነበረንም። ስለተጋጣሚዎቻችን በሚገባ ማወቅ የምንችለው  ከመጀመሪያ ጨዋታችን በኃላ ይሆናል " ብለዋል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!