የሴካፋ ውድድር የሰዓት ለውጥ
ህዳር 11, 2008


አንጋፋው የሴካፋ ዋንጫ ዛሬ ከቀትር አለፍ ብሎ 8 ሰዓት ላይ በእድሜ ጠገቡ የአዲስ አበባ ስታድየም እንደሚጀመር ተገልጾ ነበር። ሆኖም ጨዋታው ዛሬ መጀመሩ እንደተጠበቀ ቢሆንም የሰዓት ለውጥ መደረጉን ከኢትዮጵያ እግር ኯስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት ክፍል የደረሰን መረጃ አስታውቇል።

በዚህም መሠረት የውድድሩ መክፈቻ ጨዋታ የሆነውና ብሩንዲ ከዛንዚባር የሚያደርጉት ጨዋታ ከቀኑ በሶስተኛው ሩብ ማለትም 9 ሰዓት ላይ ይካሄዳል።

አስቸናጋጇ ኢትዮጵያ እና የሰርዲዮቪች ሚሉቲን ሚቾው ሩዋንዳ ደግሞ ከአመሻሹ 11 ሰዓት ሲሆን ይጫወታሉ። ቀደም ሲል እንደገለጥነው ዋልያዎቹን በአምበልነት እየመራ የሚገባው የፈረሰኞቹ የኇላ ደጀን ሳላዲን ባርጌቾ ነው።

ኢትዮፉትቦል ዶትኮም ዛሬ ካምቦሎጆ ላይ የሚካሄዱትን ጨዋታዎች በቀጥታ ያስተላልፋል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Gezegeta [755 days ago.]
 ተከብረሽ የኖርሺው በሠውነት ቢሻው ! ዮሃንስ መጣና አረገሽ እንዳሻው…ሁሁሁ

felexsami [755 days ago.]
 በጣም ያሳፍራል ቀድሞም ስንጮህ የነበረው ለዚህ ነበር:: ዮሃንስ ማለት ከህዝቡና ከጋዜጠኞች ጋር እልህ ነው የተያያዘው:: መመረጥ የሚገባቸውን ልጆች ሆን ብሎ የራሱን ቡድን ሰራ ለመባል ስለሚፈልግ ብቻ ዘለላቸው:: ይኸው እንዳየነው በሜዳችን በደጋፊው ፊት በሯንዳ ሽንፈትን አከናንቦናል እናመሰግነዋለን...... ገና ይቀጥላል !!! ዮሃንስ ይሄን የደካማ ሃገሮች ውድድር የሴካፋን ዋንጫ ቢያሸንፍ እንኳን ማንም አይገርመውም አይደንቀውም ! ያውም ሃገራችን ላይ ተዘጋጅቶ:: በጣም የሚገርመውና የሚደንቀው ነገር ግን አይደለም ለፋይናል ከምድቡ ማለፉን እጠራጠራለሁ በጣም ያሳፍራል shame on you Yohanes ! I like this slogan ተከብረሽ የኖርሺው በሠውነት ቢሻው ! ዮሃንስ መጣና አረገሽ እንዳሻው !!!

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!