የዋልያቹ ጉዞ ወዴት?
ህዳር 12, 2008

በይርጋ አበበ

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌድሬሽን በአገር ወስጥ ሊግ የሚጫወቱ ተጫዋቾች በቻ የሚሳተፉበትን የቻን ወድድር በዚህ ዓመት አጋማሽ ላይ በሩዋንዳ ያካሂዳል 21ኛው የዓለም ዋንጫ ሊካሄድ ሶስት ዓመታት ይቀሩታል የ2017 የጋቦኑ የአፍሪካ ዋንጫ ሊካሄድ ደግሞከአንድ ዓመት ያነሰ ጊዜ ብቻ ይቀረዋል። እነዚህ ውድድሮች ከመካሄዳቸው ቀደም በሎ ደግሞ በውድድሮቹ የሚሳተፉ አገራት የማጣሪያ ጨዋታ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። በአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ የሚሰጥነው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንም በእነዚህ ሶስት ታላላቅ ውድድሮች ላይ ለመሳተፍ የማጣያ ጨዋታችን ሲያካሀድ መቆቱ ይታወሳል። በዚህም ምክንያት ባፉት ሁለት ወራት ብቻ ብሄራ ቡድኑ ከሲሸልስ ከቦትስዋና ከብሩንዲ ከሳኦቶሜ እና ከኮንጎ ጋር በድምሩ ስምንት ጨዋታዎችን ማካሄድ ችሎአል።

ከላይ የተጠቀሱት ውድድሮች እና ጨዋታዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ሰሞኑን ደግሞ በአዲስ አበባ ስታዲየም 38ኛው የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ በመካድ ላይ ይገኛል። በዚህ ውድድር ላይም በሄራ ቡድኑ ከዋናው ቡድኑ ላይ ምንም አይነት ተጨዋች ሳይጨምር እና ሳይቀንስ በውድድሩ በመሳተፍ ላይ ይገኛል። ትናንትና አመሻሽ ላይም ከሩዋንዳ ብሄራ ቡድና ጋረ ተጫውቶ አንድ ለባዶ መሸነፉ ይታሳል። ከአምስት ቀናት በፊት ደግሞ በዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ከኮንጎ ብሄራ ቡድን ጋር ባደረገው የደርሶ መልስ ጨዋታ በድምሩ ስድስት ለአራት ተሸንፎ ከውድድሩ ውጭ መሆኑ አይዘነጋም። ታድያ ብሄራ ቡድ ጉዞው ወደየት እያመራ ነው?ከዚህ በታች ስለትናንትናው ጨዋታ የተመለከትናቸውን አንዳንድ ነጥቦች ላይ አንስተን እናቀርባን።  

 አጥቂ

የትናንትናው ቡድን ከታዩበት ዘርፈ ብዙ ክፍተቶች መካከል ቀዳሚው የአጥቂ መስመሩ ነበር ቢባል ማጋነን አይሆንም። ምክንያቱም አዲሱ የፈረሰኞቹ አጥቂ ራምኬል ሎክ ብቻውን በተሰለፈበት ጨዋታ ከጀርባው ሆኖ የሚያግዘው ተጫዋች ካመኖሩም በላይ ራምኬል ም በራ ለጎል የተፈጠረ እውነተኛ ጎል አዳኝ ተጫዋች ተደርጎ የሚወሰድ ልጅ አይደለም።በዚህ የተነሳም አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ በእለቱም ሆነ በተጫዋች ምርጫቸው ከሰሯቸው ስህተቶች መካከል በዚህ ቦታ ላይ በቂ እና አስተማማኝ ሊባ የሚችሉ ተጫዋቾችን አለመምረጣቸው ነው። ለዚህ ቦታ እንደ ባዬ ገዛኸኝ ወይም ታለ አለማየሁ አይነት ልጆቸን በቡድናቸው ቢያካትቱ መልካም ነበር ብዬ አስባሁ። ምንይሉ ወንድሙም ቢሆን ከስብስባቸው ውጭ መሆን ያልነበረበት ተጫዋች ነው።

አማይ ተከላካይ

በዚህ ቦታ ላይ ብሄራ ቡድኑ ክፍተት እንዳበት ስንናገር የአሁኑ የመጀመሪያችን አይደለም። አገሪቱ ውስጥ በእንጻራነት በቂ ታጫዋች አለ ተብ የሚታመነው የአማይ ተከላካይ ቦታ ላይ የሚጫወቱ ልጆች በብዛት መኖራው ነው። አሰልጣኝ ዮሃንስ ግን አሁንም ቡድናቸውን መገንባት የፈለጉተ በቡናው ጋች ፓኖም ላይ ብቻ ከሆነ ሰነባብተዋል። የጋምቤላው ተወላጅ ግን ቦታውን በብቃት ሸፍኖ ሲጫወት አይታይም።

ጋቶች በክለቡም ሆነ በብሄራ ቡድን ደረጃ አማይ ተካላካይ ቦታ ብቁ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ ጊዜ አሳይቷል። በትናንትናው ጨዋታም ሆነ ባለፉት አራት ተከታታይ የብሄራ ቡድኑ ጨዋታዎች በአማካይ ተከላካይ ቦታ በኩል ብሄራ ቡድኑ ተደጋጋሚ ጥቃት ሲፈጸምበት ነው የታየው። ስለዚህ ይህ ቦታ የተወሰነ ቀዶ ጥገና የሚያስፈልገው ቦታ መሆን አለበት ተብሎ ይታመናል። ለዚህ ደግሞ ቦታውን በአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህ ስብስብ ውስጥ የተካተተው በሀይሉ ግርማ ወይም ከስብስቡ ውጭ የሆኑት ተስፋዬ አለባቸው እና ናትናኤል ዘለቀ ሊይዙት የሚገባ ቦታ መሆኑን በሂደት እያሳዬ ያለ ቦታ ነው። ካዚያ ግን ብሄራዊ ቡድኑ በዚህ ቦታ የተነሳ ብቻ ተደጋጋሚ ጥቃት የሚደርስበት እንደሚሆን ለማወቅ ጠንቋይ መቀለብ አይጠይቅም።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
tulu [821 days ago.]
 we also see the good performance of elias&biniam ...this should give our hope still alive to continue our support for our team.,

JustThinkin [821 days ago.]
 The above article just described the question I raised in the comments section. Why arnt Getaneh, Shimelis and Walid not included in the squad? I read the coach saying he was limited to 20 players. Then why not pick your best 20, and include the above three? Yesterday would have been a different story.

Dani man [820 days ago.]
 Thanks Ethio foot Ball ጥሩ ታዝባቹሃል ! ጥሩ ብላቹሃል ! ብሔራዊ ቡድናችን ብዙ ልጆችን ይፈልጋል:: እንደ ተስፋዬ ቆቦና እንደ ናቲ አይነት ምርጥ የአማካይ ተከላካይ ሃገራችን ውስጥ ማግኘት በጣም ከባድ ነው:: በተለይ ተስፋዬ አለባቸው ብሔራዊ ቡድን ለምን እንደማይመረጥ እኔንጃ ...... ልጁ ፓስፖርቱ የሱዳን ወይም የኤርትራ ነው እንዴ ???? ይሄ ልጅ ባለፈው አመት ያሳየው አቋም ጋቶችን የሚያስንቅ ነው ግን ለምን ዮሃንስ ሊጠራው እንዳልፈለገ የስፖርት ቤተሰቡ ት ዝብትና የዘውትር ጥያቄ ነው ::

Mali [820 days ago.]
  Need our National team these players ..... come on Yohanes wake up still you are sleeping stop fighting with Sport Journalist and fans?! call እነ አስራት:..... እነ ምንተስኖት:..... እነ ተስፋዬ አለባቸው :...... እነ ናቲ:..... እነ በሃይሉ ቱሳ ....እነ ምንያህል.........እነ ባዬ ገዛኸኝ ......

Samuel Bezabeh [820 days ago.]
 ይህንን ስብስብ ይዞ አሳፋሪ ውጤት ይዞ ከቻን እንደሚመለስ ምንም ጥርጥር የለውም ኧረ የፌዴሬሽኑ ሰዎች ዮሃንስን ምከሩት?! በግፍ ከብሔራዊ ቡድኑ የታለፉ ምርጥ ብቃት ላይ ያሉት ልጆች በአስቸኳይ ቡድኑን ይቀላቀሉ:: የአሁኑ የዮሃንስ ስብስብ አይደለም ለአለም ዋንጫ አይደለም ለአፍሪካ ዋንጫ አይደለም ለቻን ለሴካፋ የሚመጥኑ አይደሉም::

Gizegeta [820 days ago.]
 በጣም ያሳፍራል የኮቹ ስራ በገዛ ሜዳው በደጋፊው ፊት ሽንፈትን መከናነቡ ሲጀመር ለሽንፈቱ ተጠያቂው አሰልጣኙ ብቻ ነው:: ስንት መመረጥ የሚገባቸው ተጫዋቾች እያሉ እንደ አስራት መገርሳ ....አዲስ ህንፃ.... ምንተስኖት.... በሃይሉ አሰፋ.... ናቲ....ተስፋዬ .... ባዬ ገዛኸኝ ....አይነቶችን ሆን ብሎ የራሱን ክሬዲት ከፍ ለማድረግ የራሱን ብድን ሰራ ለመባል ዘለላቸው :: በጣም ያሳፍራል ብሔራዊ ቡድኑን ፓርላማ ይመስል በኮታ አድርጎታል :: ስንት ብሔራዊ ቡድኑን መጥቀም የሚችሉ ጀግኖች እያሉ በዚህ ሰውዬ ግትርነት ሳይመረጡ መቅረታቸው እጅግ በጣም ያሳዝናል ያሳፍራል:: ኮች ሰውነት ቢሻው ይግደለን !!! አረ መልሱልን ሰውነት ቢሻውን..... ጀግናውን !!!

አሰፋ [819 days ago.]
 ክለቦች ብቃት ያላቸውን ተጨዋቾች የማፍራት ድርሻቸውን ተወተዋል ለማለት ያስቸግራል, ብሔራዊ ብድናችንን ምንደግፍበት መንገድም እሱ መሆን አለበት ስራ ሳይሰራ ሁሌ ውጤቱ ላይ ማማረር, የቡድኑንም መንፈስ ይግዳል, ቢቻል ቢቻል በርታ በርታ ቢለን እጅ ለ እጅ ተያይዘን ሆሆሆ...ብለን...ብናበረታቸው ሸጋነዉ ቢዬ ኖ

ተረፈ [818 days ago.]
 የመስመር ተጫዎች ያለቀላቸው ኳሶችን ለአጥቂዎች በማድረሱ በኩል ትኩረታቸውን ቢሰበስቡ መልካም ነው, የተከላካይ አማካኞች ንቁና የጨዋታውን ፍሰት በፍጥነት አምብቦ ምላሽ የመስጠት አቅማቸው ላይ ሊሰሩ ይገባል, በአጥቂዎች በኩል እንደተለመደው የቦታ አያያዝና አጠቃቀም ቢያስተካክሉ የመባከን የመንገላታት የመንከራተት ችግራቸውን ከመቅረፍ ባለፍ ፍሰትና ቅርፅ ያለው ጨዋታ ለተመልካቹ ማሳየት ይችላሉ

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!