ቡና የስታድየም መግቢያ ዋጋ ይፋ አደረገ
ህዳር 13, 2008

በይርጋ አበበ

ከ8 _15 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ርሃብ ላይ መገኘታቸውንና ለዚህም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በፍጥነት ሊደርስላቸው እንደሚገባ ማሳሰቡን ተከትሎ የተለዩ ድርጅቶች እጃቸውን በመዘርጋት ላይ ይገኛሉ። በዜጎቻችን ርሀብ ላይ መውደቃቸውን ተከትሎ የሚጠቅበትን ለማድረግ የተነሳው ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የፊታችን ሐሙስ እና እሁድ የሚከናወኑ ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች አዘጋጅቷል። 

ቡና ጨዋታዎቹን የሚያከናውነው ከወላይታ ድቻ እና ዳሽን ቢራ ጋር ነው። የክለቡ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ደሳለኝ ዛሬ አመሻሹ ላይ ለኢትዮፉትቦል ዶትኮም በስልክ ቃለ ምልልስ ባደረጉበት ወቅት ክለቡ የፊታችን ሐሙስ ከወላይታ ድቻ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ የስታድየም መግቢያ ዋጋውን ግልጽ አድረገዋል። 
በዚህም መሠረት ክቡር ትሪቡን 200፣ ጥላፎቅ 100፣ ከማን አንሸ በወንበር 50፣ ካታንጋ 20፣ ከማን አነሸ ያለወንበር 15 እና ሚስማር ተራ 10 ብር መሆኑን አሳውቀዋል። 

በተያያዘ ዜና የፊታችን ዕሁድ ኢትዮጵያ ቡና ከዳሽን ቢራ በባህር ዳር ስታድየም ለሚያካሂደው ጨዋታ ከ15 በላይ አውቶብሶች ክለቡ ማዘጋጀቱን አቶ ሙሉጌታ አክለው ገልጸዋል። 

ለወገን ደራሽ ወገን ስለሆነ ሁሉም ስፖርት አፍቃሪ የክለብ ድጋፍ ልዩነቱን ወደ ጎን ብሎ ስታድየም ተገኝቶ ጨዋታዎቹን በመመልከት ለወገኑ እንዲደረስም ጥሪ አቅርበዋል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!