በቡና ተገፍቶ ድሬዳዋ የሄደው ኮከብ
ህዳር 14, 2008

በይርጋ አበበ

በኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ከፍተኛ አድናቆትና ከበሬታ ካላቸው ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው። ክለቡ በታሪኩ የመጀመሪያውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ሲያነሳ የቡድኑ ኮከብ ነበር። ሜዳ ሲገባ ለለበሰው ማልያ ያለውን ይሰጣል ይሉታል። ኳሷ እግሩ ስር ስትገባ ደግሞ ለተመልካች አዝናኝ ጨዋታን በማሳየት የተካነ ነው። ኢትዮጵያ ቡናን ለሁለት ዓመታት በአምበልነት የመራ ሲሆን ለክለቡም ከፍተኛ ፍቅር እንዳለው ደጋግሞ ይናገራል ዳዊት እስጢፋኖስ።

ከክለቡ ጋር ባሳለፈባቸው ከስድስት ዓመታት በላይ በደጋፊውና በአሰልጣኞቹ የተወደደው ዳዊት እስጢፈፋኖስ በ2007 ዓ.ም አንድበ ዕለት የወጣችዋ ጀንበር ግን ለክለቡና ለዳዊት መለያየትን ይዛ መጣች። ባለፉት ሰባት ወራት በላይ ደግሞ ሁለቱ ወገኖች ጉዳያቸውን ይዘው ወደ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በመሄድ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ደጅ ሲጠኑ ቆይተው በመጨረሻም ፌዴሬሽኑ የዳዊትን ጥያቄ ተቀብሎ የቡናን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ውሳኔ ሰጠ። እናም ዳዊት እስጢፋኖስ ከኢትዮጵያ ቡና እንዲለቅ መልቀቂያው ይሰጠው ክለቡ ደግሞ ከተጫዋቹ አለኝ የሚለውን ገንዘብ አንስቶ እንዳይከራከር “ውሾን ያነሳ ውሾ” ብሎ እንዲተው ደነገገ።

ከፌዴሬሽኑ የይሁንታ መልስ ያገኘው የቀድሞው የቡና አምበል ከቀድሞ ክለቡ ጋር ያለውን ጉዳይ በሙሉ መፍይሄ ሰጥቶ ከጨረሰ በኋላ ወደ ፀሀይ መውጫዋ ድሬዳዋ በማቅናት ለቀጣዮቹ ስድስት ወራት የሚያቆየውን ስምምነት መፈራረሙ ተነግሯል። ዳዊት እስጢፋኖስ በተለይ ከኢትዮፉትቦል ዶትኮም ጋር በስልክ ባደረገው ቃለ ምልልስ በቡና በነበረው ቆይታ ደስተኛ እንደነበረ ገልጾ አሁን ወደ ድሬዳዋ ማቅናቱም የእግር ኳስ አንዱ አካል መሆኑን ተናግሯል። ለስድስት ወራት ስምንት መቶ ሺህ ብር ወይም በየወሩ 133 ሺህ 333 ብር እንደሚከፈለው ተገልጿል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
AbduilBunna [820 days ago.]
 ስድ ባለጌ የሆነ ተጫዋች ነው ቡናን እወዳለሁ እያለ ደጋፊውን ይሸነግላል ሜዳ ላይ ግን ምንም ነገር አይሰራም ለለበሰው ማሊያ ተሯሩጦ መጫወት እንኳን የማይችል ተጫዋች ነው መሄዱ ጥሩ ነው ተገላገልነው በዚህ ላይ ጥሩ ፀባይ ዲሲፒሊንድ የሆነ ተጫዋች አይደለም የክለቡ አመራሮች የወሰዱበት እርምጃ ትክክል ነው ቡናን አይመጥንም

gamo [820 days ago.]
 ኧረ ኢትዮ ፉትቦል ምን አይነት ዘገባ ነው እንዴ የክለቡ ልሳን እኮ ነው የምሰላችሁት ልጁን እኮ ጠንቅቀን እናውቀዋለን በአመት ውስጥ ፰ ወይም ፱ ጨዋታ ለሚያደርግ ተጫዋች በደጋፊውና በአሰልጣኞቹ የተወደደው ዳዊት እስጢፈፋኖስ ምናምን ትላላችሁ እንዴ

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!