ዋልያዎቹ በዛሬው ጨዋታ አምበላቸውን ያገኛሉ
ህዳር 15, 2008


ዛሬ ከቀኑ በሶስተኛው ሩብ የሶማሊያን ብሔራዊ ቡድን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምበሉን ስዩም ተስፋዬን ከእረፍት መልስ ለጨዋታው ብቁ ሆኖ እንደሚቀርብ ታወቀ። ምክትል አምበሉ ሳላሀዲን ባርጌቾ እና አጥቂው በረከት ይሳቅ በጉዳት እንዲሁም ግብ ጠባቂው ታሪክ ጌትነት ሀዘን ምክንያት ጨዋታው የሚያልፋቸው ይሆናል። 

አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በዛሬው ጨዋታ ለጋቶች ፓኖም እረፍት ይሰጡታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በምትኩም በሀይሉ ግርማ ይሰለፋል ተበሏል። የቡናው አማካይ ባለፉት አምስት የብሔራዊ ቡደን እና አንድ የክለብ ጨዋታ ያሳየው ብቃት ጥሩ አለመሆኑን ተከትሎ ተደጋጋሚ ትችቶች ደርሶበት ነበር። 

18 ተጫዋቾችን ይዞ ወደ ሐዋሳ የተጏዘው የአሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ስብስብ የመከላከያው ምንይሉ ወንድሙ እና የአዳማ ከነማው ታከለ ዓለማየሁ ከስብስቡ ውጭ ተደርገዋል። 

የአጥቂ ችግር እንዳለበት የሚነገረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሁለቱን ወጣት አጥቂዎች ከስብስቡ ውጭ ማድረጉ አነጋጋሪ ሆኗል። 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተደለደለበትን ምድብ አንድን ሁለት ጨዋታዎችን ያሸነፈው የታንዛንያ ብሔራዊ ቡድን በስድስት ነጥብ ይመራዋል። 

በሌሎች ጨዋታዎች ትላንት በተካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ታንዛንያ ሩዋንዳን ሁለት ለአንድ አሸንፏል። ዩጋንዳ ደግሞ ዛንዚባርን አራት ለባዶ ረምርሞታል። በዚህ ውጤት የተነሳም የሰርዲዮቪች ሚሉቲን ሚቾ ቡድን ዩጋንዳ የምደቡ አናት ላይ ሲቀመጥ ዛንዚባር ደግሞ የደረጃውን ግርጌ በብቸኝነት ሊይዝ ችሏል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
student zaman ambachaw [751 days ago.]
 INKUWAN DAS ALAN GO TO FROM THIS___GUNN

Dinberu tekle [749 days ago.]
 sekafa wanchan ethiopia kalanesach ye ethiopia eger kawas neger waga yelewum.

Waliyawe [748 days ago.]
 ዮሃንስ ለዋሊያው ማለት ቤኔቴዝ ለሪያል ማድሪድ እንደ ማለት ነው የሚገባው ይገባዋል .......

Nati 4 Killo [748 days ago.]
 @ menge-t አዎ ከሱዳን መልስ 40 ምንጭ ገብቶ ነበር ከዛም ጊዮርጊስን ተቀላቀለ ልጁ የዋሊያው ቁልፍ የሆነ ልጅ ነበር ምን ዋጋ አለው በዮሃንስ ከተገፋት ተጫዋቾች ውስጥ አንዱ ነው!

Samuel Bezabeh [748 days ago.]
  I said so mant times like this ይህንን ስብስብ ይዞ አሳፋሪ ውጤት ይዞ ከቻንም እንደሚመለስ ምንም ጥርጥር የለውም ኧረ የፌዴሬሽኑ ሰዎች ዮሃንስን አባሩልን ?!!! በግፍ ከብሔራዊ ቡድኑ የታለፉ ምርጥ ብቃት ላይ ያሉት ልጆች በአስቸኳይ ቡድኑን ይቀላቀሉ:: የአሁኑ የዮሃንስ ስብስብ አይደለም ለአለም ዋንጫ አይደለም ለአፍሪካ ዋንጫ አይደለም ለቻን ለሴካፋ የሚመጥኑ አይደሉም::

Tariku [748 days ago.]
 እንደ ዮሃንስ አይነት አምባገነን እኔ ብቻ ያልኩት ይሁን ባይ እኔ ብቻ አዋቂ ከብሔራዊ ቡድኑ ክብር ይልቅ ለራሱ ክብር የሚሰጥ የሚሰራ አይነት አሰልጣኝ ሃገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታ አታውቅም::

felexsami [748 days ago.]
 me also before i wrote this comment በጣም ያሳፍራል ቀድሞም ስንጮህ የነበረው ለዚህ ነበር:: ዮሃንስ ማለት ከህዝቡና ከጋዜጠኞች ጋር እልህ ነው የተያያዘው:: መመረጥ የሚገባቸውን ልጆች ሆን ብሎ የራሱን ቡድን ሰራ ለመባል ስለሚፈልግ ብቻ ዘለላቸው:: ይኸው እንዳየነው በሜዳችን በደጋፊው ፊት በሯንዳ ሽንፈትን አከናንቦናል እናመሰግነዋለን...... ገና ይቀጥላል !!! ዮሃንስ ይሄን የደካማ ሃገሮች ውድድር የሴካፋን ዋንጫ ቢያሸንፍ እንኳን ማንም አይገርመውም አይደንቀውም ነበር ! ያውም ሃገራችን ላይ ተዘጋጅቶ:: በጣም የሚገርመውና የሚደንቀው ነገር ግን አይደለም ለፋይናል ከምድቡ ማለፉን እጠራጠራለሁ በጣም ያሳፍራል shame on you Yohanes ! I like this slogan ተከብረሽ የኖርሺው በሠውነት ቢሻው ! ዮሃንስ መጣና አረገሽ እንዳሻው !!!

Gezegeta [748 days ago.]
  ይሄ አምባገነን አሰልጣኝ ነኝ ተብዬ በዚህ ግትር አቋሙ ብሔራዊ ቡድናችንን ያዋርደዋል ያሰድበዋል በጣም የማዝነው ብሔራዊ ቡድኑን መጥቀም የሚችሉ ስንት ጀግና ተጫዋቾችን መምረጥ እየቻለ የራሱን ቡድን ሰራ ለመባል ስለሚፈልግ ብቻ ልጆቹን ገፋቸው ሃገራችንንም በትንንሽ ቡድኖች ሳይቀር አስደፈረን. g

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!