ዋልያዎቹ ወደ ሩብ ፍጻሜ የማለፍ ተስፋቸውን አለመለሙ
ህዳር 15, 2008

በይርጋ አበበ

በ38ኛው የሴካፋ ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታውን በሩዋንዳ የተሸነፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከቀትር በኋላ በሀዋሳ ስታዲየም ያደረገውን ጨዋታ ሁለት ለባዶ ማሸነፍ ችሏል። ዋልያዎቹ የሶማሊያ አቻቸውን ሁለት ለባዶ ባሸነፉበት ጨዋታ ሁለቱንም የማሸነፊያ ጎሎች ያስቆጠሩት የመከላከያዎቹ መሃመድ ናስር እና በሀይሉ ግርማ ናቸው። በተለይ በሀይሉ ግርማ በነጥብ ጨዋታ ለመጀመሪያ ጊዜ ቋሚ ተሰላፊ ሆኖ በተጫወተበት የብሔራዊ ቡድን ጨዋታ በግሉም የመጀመሪያ የብሔራዊ ቡድን ጎሉን አስቆጥሯል።ድሉን ተከትሎም ዋልያዎቹ በተደለደሉበት ምድብ አንድ ከታንዛኒያ በሶስት ነጥብ ተበልጠው እና ከሩዋንዳ ጋር በነጥብም በጎል ክፍያም ተስተካክለው ሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል። የምድባቸውን የመጨረሻ ጨዋታም ቀድማ ከምድቧ በማለፍ ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀለችውን ታንዛኒያን የሚገጥሙ ሲሆን ከታንዛኒያ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ሶስት ነጥብ ማግኘት ከቻሉ ሩብ ፍጻሜውን መቀላቀል ያስችላቸዋል።
Hawassa Stadium

ዋልያዎቹ ዛሬ በሀዋሳ ስታዲየም ያካሄዱትን ጨዋታ ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ተመልካች በስታዲየም ተገኝቶ ተከታትሎታል። ከሀዋሳ ባገኘነው መረጃ ለማወቅ እንደቻልነው ግን ብሔራዊ ቡድኑ የተለመደውን ማራኪ የኳስ ቁጥጥር የተላበሰ ጨዋታ ማሳየት አልቻለም። በሌሎች ጨዋታዎች ዛሬ ቀትር ላይ በሀዋሳ ስታዲየም የተካሄደው የኬኒያ እና የብሩንዲ ጨዋታ አንድ እኩል በሆነ ውጤት ተጠናቋል።  

ባህር ዳር ላይ የተካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ነበሩ። የውድድሩ ተጋባዥ አገር ማላዊ ጂቡቲን ሶስት ለባዶ የረመረመች ሲሆን ሁለቱ ሱዳኖች ግን መሳ ለመሳ ተለያይተዋል። ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ባዶ ለባዶ መለያየታቸውን ተከትሎ ደቡብ ሱዳን ወደ ሩብ ፍጻሜ ለማለፍ ሰፊ እድል ይዛለች። አራት ነጥብ ያለት ደቡብ ሱዳን የምድቧን የመጨረሻ ጨዋታ አንድ ነጥብ ማግኘት ከቻለች ከምድቧ ሁለተኛ ሆና የማንንም ውጤት ሳትጠብቅ ሩብ ፍጻሜውን ትቀላቀላለች።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!