ኢትዮጵያ በምስራቅና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ
ህዳር 17, 2008

የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ከተጀመረ ረጅም አመታትን አስቆጥሯል።  የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ1980 15ኛውን ዋንጫ ካዘጋጀበት ጊዜ ጀምሮ አሁን በሀገራችን የተዘጋጀውን ሳንጨምር 3ጊዜ ውድድሩን ያዘጋጀ ሲሆን ሁለት ጊዜ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን  የዋንጫ ባለቤት ሆኗል። በ1999 ዓ.ም በተዘጋጀው ውድድር ከመካከለኛው አፍሪካ ተጋባዥ ሆኖ በመጣው ጠንካራው የዛምቢያ ቡድን በመሸነፉ ለዋንጫ ሳያልፍ ቀርቷል።

ኢትዮጵያ በምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ  በሚል ርእስ የኢትዮፉትቦል ዶት ኮም ድረ ገጽ ባልደረባ ፈለቀ ደምሴ ሐምሌ 2005 ዓ.ም በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ  ባዘጋጀው የኢትዮጵያ እግር ኳስን የሚዳስስ   መጽሐፉ ላይ ምእራፍ ዘጠኝ ከገጽ 102-110 ጠቅለል አድርጎ ታሪኩን ባጭሩ አስቀምጦታል ። ባልደረባችን በሰጠን ፈቃድ መሰረት ለኢትዮ ፉትቦል ዶት ኮም ተከታታዮች ታሪኩን እንዲያነቡት  በማሰብ መጽሐፉ ላይ የሰፈረውን እንዳለ ከዚህ ቀጥሎ አቅርበነዋል።

መልካም ንባብ!  መልካም እድል ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን!

ኢትዮጵያ በምስራቅና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ 

የሴካፋ የእግር ኳስ ሻምፒዮና መከናወን የጀመረው እ.ኤ.አ በ1927 ዓ.ም ነው፡፡ ይሁን እንጂ ውድድሩ ይዘጋጅ የነበረው በዞኑ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አማካይነት አልነበረም፡፡ ይህ ውድድር ጎሴጅ ካምፕ ተብሎ ይካሄድ የነበረ ሲሆን ሻምፒዮናውን ስፖንሰር በማድረግ በበላይነት ይመራ የነበረው መሠረቱን ኬንያ አድርጎ የቆየው ጎሴጅ ሳሙና አምራች ፋብሪካ ሲሆን በወቅቱ ሀገራቱ በቀኝ ግዛት ስር በመሆናቸውና ውድድሩም በቅኝ ገዢዎች ተፅእኖ ስር እንደነበር ይታወቃል፡፡ 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አጎራባች በሆኑት በኬኒያ በኡጋንዳ፣ በሱዳን፣ በታንዛኒያ፣ በሶማሊያ መካከል የምሥራቅ አፍሪካ የወዳጅነት ዋንጫ ደንቡን በማዘጋጀት ከላይ ለተጠቀሱት ሀገሮች ፌዴሬሽኖች ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽንና ለፊፋ አቅርባ በማስፅደቅ የመጀመሪያውን ውድድር ከሚያዝያ 30 እስከ ግንቦት 7 ቀን 1958 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አዘጋጅታለች፡፡ ለዚህም ውድድር መጀመር የአቶ ይድነቃቸው ተሰማ አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደነበር የታሪክ መፅሐፍት ይዘግባሉ፡፡  

በዚህ ውድድር ኬኒያ፣ ታንዛኒያና ሶማሊያ ለተካፋይነት መልስ ባይሰጡም ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ኡጋንዳ በውድድሩ ተካፋይ ሆነው ኢትዮጵያ ኡጋንዳን 5ለ0 አሸንፋ ከሱዳን ጋር 1ለ1 በመለያየቷና በአንፃሩ ሱዳን ኡጋንዳን 2ለ1 በማሸነፏ ኢትዮጵያ በግብ ብልጫ የመጀመሪያው የምሥራቅ አፍሪካ የወዳጅነት ዋንጫ ባለቤት ለመሆን መብቃቷ ይታወሳል፡፡ 

2ኛው የምሥራቅ አፍሪካ የወዳጅነት ዋንጫ ከየካቲት 12 እስከ 19 1959 ዓ.ም በሱዳን ካርቱም ከተማ በኢትዮጵያ በታንዛኒያ፣ በሱዳንና በኬኒያ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል በጥሎ ማለፍ መልክ ተከናውኗል፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ ኬኒያን 2ለ0 ሱዳን ታንዛኒያን በተጨማሪ ሰዓት 1ለ0 በማሸነፍ ለፍፃሜ ጨዋታ ደርሰው ነበር፡፡ ቀደም ሲል አዘጋጅዋ ሱዳን ገቢው ወጪውን ስለማይሸፍንልኝ የፍፃሜው ውድድር በደርሶ መልስ ይሁንልኝ ብላ ጠይቃ ስለነበር ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ውድድር 1ለ1 ተለያይተው በመልሱ ግጥሚያ ሱዳን ብሔራዊ ቡድናችንን 5ለ3 በማሸነፍ የዋንጫው ባለቤት ለመሆን በቅቷል፡፡ 3ኛው የምስራቅ አፍሪካ የወዳጅነት ዋንጫ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት በኢትዮጵያ፣ በሱዳን፣ በኡጋንዳ፣ በታንዛኒያ፣ በሶማሊያና በኬኒያ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል ከታህሳስ 27 እስከ ጥር 4 ቀን 1961 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ ተደርጎ ነበር፡፡ በዚህም ቡድኖች በሁለት ምድብ ተከፍለው ውድድራቸውን አከናውነዋል፡፡ በአንደኛው ምድብ ኢትዮጵያ ሶማሊያን 7ለ0 ኡጋንዳን 4ለ0 በማሸነፍ በሁለተኛው ምድብ ሱዳን ኬንያን 1ለ0 ታንዛኒያን 3ለ0 አሸንፎ ለፍፃሜው ውድድር ደርሰው ሱዳን አዲስ አበባ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያን ቡድን አሸንፎ የዋንጫ ባለቤት ሆነ፡፡ ይህም ውድድር ቀርቶ የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሀገሮችን እንዲያጠቃልል ተደርጎ መዘጋጀት ቀጠለ፡፡ ኢትዮጵያም በዚህ ኮንፌዴሬሽን በተዘጋጀው ውድድር ሳትካፈል ቆይታ በ1976 ዓ.ም ኬኒያ ላይ በተዘጋጀው ውድድር መሳተፍ ቀጠለች፡፡ 

የኢትዮጵያ ቡድን በኬንያው ውድድር አጥጋቢ ውጤት ባያገኝም ኮንፌዴሬሽኑ 15ኛውን የምስራቅና መካከለኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ውድድር ኢትዮጵያ እንድታዘጋጅ በመወሰኑ ታህሳስ 3 ቀን 1980 ዓ.ም በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ሲጀመር  በአአዲስ አበባ ምድብ ኢትዮጵያ፣ ታንዛኒያ፣ ዛንዚባርና ኬኒያ በአስመራው ምድብ ኡጋንዳ፣ ዛምቢያ፣ ዚምባብዌና ማላዊ ተመድበው ነበር፡፡ በመክፈቻ ዕለት አዲስ አበባ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከታንዛኒያ ጋር 0ለ0 ተለያየ፡፡ በአሥመራው ውድድር መክፈቻ ዚምባብዌና ማላዊ 1ለ1 ተለያዩ፡፡ ይህ ውድድር በመከናወን ላይ ሳለ የማላዊ ቡድን መሪ የነበሩት ሚስተር አልሰተን በሳባ ስታዲየም በልብ ድካም ሕይወታቸው አለፈች፡፡ በሳቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የማላዊ ቡድን ወደ ሀገራቸው በመመለሳቸው የአሥመራው ምድብ ውድድር በ3 ቡድኖች መካከል ተደረገ፡፡ 

የአዲስ አበባ ምድብ 2ኛ ቀን ግጥሚያ የተከናወነው በኬኒያና በዛንዚባር ቡድኖች መካከል ሲሆን ውጤቱም 0ለ0 ነበር፡፡ ኬኒያ ታንዛኒያን 3ለ2 ሲረታ የኛም ቡድን እድሉን ለማለምለምና ለግማሽ ፍፃሜ ለማለፍ ዛንዚባርን ማሸነፍ ነበረበት፡፡ የኢትዮጵያ ቡድን 90ውን ደቂቃ ሙሉ አጥቅቶ ተጫውቶ ግብ ማስቆጠር ግን አልቻለም፡፡ ወሳኙ ግጥሚያ ከኬኒያ ጋር በተደረገው ነበር፡፡ 

የኬኒያ ቡድን አስቀድሞ ግብ አስቆጠረ፡፡ የማለፍ እድሉን አሰፋ፡፡ ደጋፊው በጭንቀት ስሜት ላይ እንዳለ ሙሉጌታ ወልደየስ አሳልፎ የሰጠውን ሙሉጌታ ከበደ ከጎል በማወሃድ የሕዝቡን መንፈስ ከሀሳብ መለሰው፡፡ ጊዜ ይከንፍ ጀመር፡፡ ኬኒያውያን ጊዜ ያባክኑ ጀመር፡፡ ከሙሉአለም እጅጉ ጋር በፈጠረው ግጭት አንድ ተጨዋች በመውጣቱ ኬኒያውያን በጎደሎ ነበር የተጫወቱት መደበኛው ጨዋታ ሊያልቅ ትንሽ ደቂቃዎች ሲቀሩ የቅጣት ምት ተገኘ፡፡ ሙሉጌታ ከበደ ጊዜ ሳይሰጥ የቅጣት ምቱን መትቶ ብቻውን ቦታ ይዞ ለሚጠብቀው ለሙሉጌታ ወልደየስ ሰጠ፡፡ ሙሉጌታም ሁለተኛውን ግብ አስቆጠረ፡፡ ስታዲየሙ በሆታ ቀለጠ፡፡ የኢትዮጵያ ቡድን ለግማሽ ፍፃሜ አለፈ፡፡ 

በውድድሩ ደንብ መሠረት የአዲስ አበባ ምድብ ሁለተኛ የሆነው የኢትዮጵያ ቡድን ከአሥመራ ምድብ በአንደኛነት ያለፈውን የኡጋንዳን ቡድን በከፍተኛ የጨዋታ ብልጫ 3ለ0 በማሸነፍ የአሥመራው ምድብ ሁለተኛ የሆነውን ዚምባብዌም ዛንዚባርን 1ለ0 በማሸነፍ ለዋንጫው ፍልሚያ ደረሱ፡፡ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም አካባቢ ትኬት ለመግዛት በሰው ተሞላ፡፡ ጠጠር ቢወረወር ጠብ በማይልበት ሁኔታ ከረፋዱ 5 ሰዓት አካባቢ ስታዲየሙ ሞልቷል፡፡ ማስተናገድ የሚችለውን ተቀብሎ ከ5 ሰዓት በኋላ ስታዲየሙ በሮች ተዘጉ፡፡ ከገባው ተመልካች ሌላ በርካታ ሕዝብ ነበር የተመለሰው፡፡ የኢትዮጵያ ሰንደቅ-ዓላማ ዙሪያውን አደመቀው፡፡ የወቅቱ የክብር እንግዳ ፕሬዚዳንት መንግስቱ ኃይለማርያም በአዲስ አበባ ስታዲየም ተገኙ፡፡ 

የዕለቱ ዋንጫ ፍልሚያ ተጀመረ፡፡ ተመልካቹ ‹‹ማታ ነው ይኸው ነው አመሌ፤ ወደ ጎል ጎል!›› እያለ ድጋፉን ቀጠለ፡፡ ገና ጨዋታው ሲጀመር ዚምባቢዌዎች የጨዋታውን የበላይነት ያዙ፡፡ በ19ኛው ደቂቃም  የመጀመሪያውን ግብ አገቡ፡፡ ተመልካቹ ድጋፍ ማድረጉን ቀጠለ፡፡ ሰዓቱ ከነፈ፡፡ አብዛኛው ተመልካች ተስፋ በመቁረጥ መውጣት ሲጀምር በሮች ተዘጉ፡፡ አማኑኤል እያሱ ለሙሉዓለም እጅጉ ሰጥቶት ሙሉአለም እጅጉ ለገብረመድን ኃይሌ የላካት ኳስ ገብረመድን በጭንቅላቱ በመግጨት አቻ የሚያደርገውን ግብ አገባ፡፡ መደበኛው ጨዋታ ወዲያውኑ ተፈፀመ፡፡ ሕዝቡ ከፍተኛ ድጋፍ መስጠቱን ቀጠለ፡፡ 30 ደቂቃውም አለቀ፡፡ ወደ ፍፁም ቅጣት ምቶች አመሩ፡፡ በረኛው ተካበ አይዟችሁ በማለት ሕዝቡን አነቃቃ፤ ተወርውሮ የመጀመሪያዋን አዳነ፡፡ ሕዝቡ ተደሰተ፤ የኛዎቹ አገቡ፡፡ አሁንም 2ኛውን አዳነ፤ በቀለ ብርሃኔ ሳተ፡፡ መንግስቱ ሁሴንም ሳተ ስድስተኛውን  ዚምባብዌ ተጫዋች ሳተ፤ ዳኛቸው ደምሴ በድፍረትና በልበ ሙሉነት በመሄድ በረኛው ባልጠበቀው ቦታና አቅጣጫ መትቶ አገባ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ26 ዓመት በኋላ የዋንጫ ባለቤት ሆነ፡፡ 
CECAFA Champion Team 1980 EC


ኢትዮጵያ ከ1980 ዓ.ም በኋላ የሴካፋ አሸናፊ መሆን የቻለችው በ1994 ዓ.ም ሩዋንዳ ባዘጋጀችው ውድድር ሲሆን ከአገኘቻቸው ዋንጫዎች ከኢትዮጵያ ውጪ በተዘጋጀ ውድድር ያገኘችው የመጀመሪያው ዋንጫ ነው፡፡ በወቅቱ ብሔራዊ ቡድኑን በአሰልጣኝነት የመሩት አስራት ኃይሌ ነበሩ፡፡ ሻምፒዮናው በሩዋንዳ አስተናጋጅነት ሲከናወን 10 ሀገራት በሦስት ምድብ ተደልድለው መርሃ ግብራቸውን አከናውነዋል፡፡ በምድብ አንድ ኢትዮጵያ፣ የሩዋንዳ፣ ሁለተኛው ቡድንና ዛንዚባር በምድብ ሁለት ታንዛኒያ፣ ቡሩንዲ፣ ኡጋንዳና ጅቡቲ ከምድብ ሦስት ኬንያ፣ ኤርትራ፣ ሩዋንዳና፣ ሶማሊያ ተገናኝተዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ የምድብ ጨዋታ 
ኢትዮጵያ 5 – 0 ዛንዚባር
ሩዋንዳ 1 – 1 ኢትዮጵያ 

ሩብ ፍፃሜ 
ኢትዮጵያ 2 – 2 ቡሩንዲ
- ባዩ ሙሉ 
- ዮርዳኖስ አባይ
በመለያ ምት ኢትዮጵያ 3ለ4 

ግማሽ ፍፃሜ
ኢትዮጵያ 1 – 0 ሩዋንዳ
- ባዩ ሙሉ

ፍፃሜ
ኢትዮጵያ 2 – 1 ኬንያ
- ዮርዳኖስ አባይ
- ማሞ አለም ሻንቆ 
CECAFA Champion Team 1994 EC.


ሌላኛው ኢትዮጵያ አሸናፊ የሆነችበት የሴካፋ ዋንጫ በ1997 ዓ.ም ሲሆን ውድድሩ የተዘጋጀውም ኢትዮጵያ ውስጥ ነበር፡፡ በወቅቱ የውድድሩ ስያሜ ‹‹አላሙዲን ሲኒየር ቻሌንጅ ካፕ›› ይባል የነበረ ሲሆን ስያሜው የተሰጠው ውድድሩን ስፖንሰር ባደረጉት በኢትዮጵያዊው ባለሀብት ሼክ መሀመድ ሁሴን አል-አሙዲ ነው፡፡ በዚህ አሸናፊ ላይ ዘጠኝ ቡድኖች በሁለት ምድብ ተከፍሎ ሲሳተፉ ኢትዮጵያ፣ ቡሩንዲ፣ ሩዋንዳ፣ ዛንዚባር፣ ታንዛኒያ፣ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ሶማሊያ ተካፋይ ናቸው፡፡ 

የኢትዮጵያ የምድብ ጨዋታዎች 
ኢትዮጵያ 2 – 1 ቡሩንዲ 
ሰብስቤ ሸገሬ
ፍቅሩ ተፈራ

ሩዋንዳ 0 – 0 ኢትዮጵያ 
ኢትዮጵያ 2 – 0 ታንዛኒያ
አንተነህ አላምረው
ታፈሰ ተስፋዬ

ኢትዮጵያ 3 – 0 ዛንዚባር
ፍቅሩ ተፈራ
አሸናፊ ግርማ 
ሃይደር መንሱር

ግማሽ ፍፃሜ 
ኢትዮጵያ 2 – 2 ኬንያ
አንተነህ አላምረው 
ታፈሰ ተስፋዬ 
በመለያ ምት ኢትዮጵያ 5 ለ 4 ረታች

ፍፃሜ 
ኢትዮጵያ 3 – 0 ቡሩንዲ 
አንዱዓለም ንጉሴ 
ታፈሰ ተስፋዬ
አንተነህ አላምረው

CECAFA 1997 EC Champion Team


አሁንም ሼህ መሐመድ ሁሴን አል-አሙዲን ሴካፋን በድጋሚ ለተከታታይ ሁለተኛ ዓመት ስፖንሰር በማድረጋቸው ሩዋንዳ የ1998ቱን ውድድር አስተናግዳ ኢትዮጵያ ከሀገሯ ውጪ ለሁለተኛ ጊዜ አሸናፊ መሆን ችላለች፡፡ በውድድሩም አሥር ሀገራት በሁለት ምድብ ተከፋፍለው ተፋልመዋል፡፡ በምድብ አንድ ዛንዚባር፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ቡሩንዲና፣ ኤርትራ፣ በምድብ ሁለት ኡጋንዳ፣ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ሶማሊያና ጅቡቲ ተገናኝተዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ የምድብ ጨዋታዎች 

ኢትዮጵያ 0 – 0 ኡጋንዳ 
ኢትዮጵያ 3 – 1 ሱዳን
ኢትዮጵያ 6 – 2 ጅቡቲ 

ግማሽ ፍፃሜ

ኢትዮጵያ 4 – 0 ዛንዚባር  
ፍቅሩ ተፈራ 3
አሸናፊ ግርማ 

ፍፃሜ
ኢትዮጵያ 1 – 0 ሩዋንዳ 

ክቡር ዶ/ር ሼክ መሐመድ ሁሴን አል-አሙዲ ስፖንሰር ያደረጉትና በ1999 ዓ.ም ሀገራችን ላይ በተደረገው የምስራቅና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ቡድን ለዋንጫ ለማለፍ በግማሽ ፍፃሜ በዛምቢያ ቡድን በመሸነፉ ከውድድር ውጪ ሆኗል፡፡ 

Sewnet 1997 CECAFA Champion

አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በመምራት ካስገኙት ዋንጫ ጋር 1998 ዓ.ም፡፡ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Dani man [817 days ago.]
 ፌዴሬሽኑ ምን አይነት ኮች እንደሾመብን እኮ ግርም ድንቅ እያለን ነው:: በምንስ መስፈርት እንደመረጡት ግራ ግብት ብሎናል:: አየነው እኮ የዮሃንስን ስራ በሃገሩ ላይ የተዘጋጀውን የደካሞች ደካማ ዞን ውድድር ላይ ብድን መስራት እንኳን የማይችል ኧረ በጣም ያሳፍራል:: በቀደምለታም ያሸነፈው የሶማሊያን ቡድን ስለሆነ ነው :: ምን አይነት ብድን ምን አይነት ልጆችን ነው የሰበሰበው?! እሺ ፌዴሬሽኑ አሰልጣኝ ነህ ብሎ ስለሾመው የፈለገውን ተጫዋች የመጥራት የመቀነስ ስልጣን አለው ብለን ዝም አልነው ግን ምንም ነገር የሰራው ነገር የለም ብሔራዊ ቡድኑ ቋሚ 11 እንኳን የለውም:: በየጊዜው ይጠራል .... በየጊዜው ያባርራል :: ኧረ መላ በሉን ኧረ አንድ በሉት ?! እኔ የማዝነው ብሔራዊ ቡድናችንን መጥቀም እየቻሉ በኮቹ ለተገፉት ተጫዋቾች ነው አስራት መገርሳ ..... ምንተስኖት..... ተስፋዬ ቆቦ..... በሃይሉ አሰፋ..... ናቲ..... አዲስ ህንፃ...... ባዬ ገዛኸኝ..... ምንያህል ተሾመ.... ወዘተ እነዚህና ስማቸው የተዘረዘረውና ያልተዘረዘረው ብዙ ተጫዋቾች አቋማቸው ጥሩ እስከሆነ ድረስ ለምን ዮሃንስ ሊጠራቸው እንዳልፈለገ እሱ እራሱ መልስ ያለው አይመስለኝም :: ምንአልባት ልጆቹ በኮች ሰውነት ቢሻው ቡድን ውስጥ ስለነበሩ ይሆን ?!!!

Daniman [816 days ago.]
 I will repeat today also. we have fake coach Yohanes pls leave us alone gooooooooo ፌዴሬሽኑ ምን አይነት ኮች እንደሾመብን እኮ ግርም ድንቅ እያለን ነው:: በምንስ መስፈርት እንደመረጡት ግራ ግብት ብሎናል:: አየነው እኮ የዮሃንስን ስራ በሃገሩ ላይ የተዘጋጀውን የደካሞች ደካማ ዞን ውድድር ላይ ብድን መስራት እንኳን የማይችል ኧረ በጣም ያሳፍራል:: በቀደምለታም ያሸነፈው የሶማሊያን ቡድን ስለሆነ ነው :: ምን አይነት ብድን ምን አይነት ልጆችን ነው የሰበሰበው?! እሺ ፌዴሬሽኑ አሰልጣኝ ነህ ብሎ ስለሾመው የፈለገውን ተጫዋች የመጥራት የመቀነስ ስልጣን አለው ብለን ዝም አልነው ግን ምንም ነገር የሰራው ነገር የለም ብሔራዊ ቡድኑ ቋሚ 11 እንኳን የለውም:: በየጊዜው ይጠራል .... በየጊዜው ያባርራል :: ኧረ መላ በሉን ኧረ አንድ በሉት ?! እኔ የማዝነው ብሔራዊ ቡድናችንን መጥቀም እየቻሉ በኮቹ ለተገፉት ተጫዋቾች ነው አስራት መገርሳ ..... ምንተስኖት..... ተስፋዬ ቆቦ..... በሃይሉ አሰፋ..... ናቲ..... አዲስ ህንፃ...... ባዬ ገዛኸኝ..... ምንያህል ተሾመ.... ወዘተ እነዚህና ስማቸው የተዘረዘረውና ያልተዘረዘረው ብዙ ተጫዋቾች አቋማቸው ጥሩ እስከሆነ ድረስ ለምን ዮሃንስ ሊጠራቸው እንዳልፈለገ እሱ እራሱ መልስ ያለው አይመስለኝም :: ምንአልባት ልጆቹ በኮች ሰውነት ቢሻው ቡድን ውስጥ ስለነበሩ ይሆን ?!!!

Samuel Bezabeh [816 days ago.]
 ይህንን ስብስብ ይዞ አሳፋሪ ውጤት ይዞ ከቻንም እንደሚመለስ ምንም ጥርጥር የለውም ኧረ የፌዴሬሽኑ ሰዎች ዮሃንስን አባሩልን ?!!! በግፍ ከብሔራዊ ቡድኑ የታለፉ ምርጥ ብቃት ላይ ያሉት ልጆች በአስቸኳይ ቡድኑን ይቀላቀሉ:: የአሁኑ የዮሃንስ ስብስብ አይደለም ለአለም ዋንጫ አይደለም ለአፍሪካ ዋንጫ አይደለም ለቻን ለሴካፋ የሚመጥኑ አይደሉም::

felexsami [816 days ago.]
 በጣም ያሳፍራል ዮሃንስ የሚባል ኮች በየጊዜው ዜና ላይ የምንሰማው ቡድኑ ትሬኒንግ ልምምድ አደረገ ሰራ ነው ታዲያ ሜዳ ላይ የምናየው ቡድን ምን አይነት የመንደር የሰፈር ውስጥ ቡድን ሳይሆን በድን የሆነ ቲም ነው

Melaku [816 days ago.]
 ለሁሉም ነገር ተጠያቂው ዮሃንስ የተባለው ፌዴሬሽኑ ትችላለህ ብሎ ኮች ያደረገው ሰው ነው :: ፓርላማ ይመስል ስንት የሚችሉ ልጆች እያሉ ከየክለቡ ተጫዋቾች መረጠ:: ኧረ ያሳፍራል ሃገራችን ላይ የሴካፋ የደካማ ደካማ ዞኖች ውድድር ተካሂዶ እንደዚህ አይነት የመንደር ቲም.... ስብስብ ደካማ ቡድን በታሪክ ታይቶ አይታወቅም:: ይሄ ስብስብ የሱ ነው .... እሱ ነው የመረጠው .....እሱ ነው ያባረረው ስንት የሚችሉ ልጆችን ኧረ ተቃጠልን አባሩልን ዮሃንስ የተባለ ሰውን !

Yoni [816 days ago.]
 ዮሃንስ እንደማይችል ከዚህ በላይ ማረጋገጫ የለም ቡድን መስራት እንኳን አልቻለም እኮ እዚህ ደካማ ቶርናመንት ላይ ኧረ ኮች ሰውነት ቢሻው ይቅር በለን በድለንሃል

Duressa [816 days ago.]
 ዮሃንስ ተባነነበት አይችልም ይባረር ስንት የሚችሉ አሰልጣኞች አሉ እድሉ ይሰጣቸው አስራት ሃይሌ ስዩም ከበደ ውበቱ አባተ ገብረመድን ሃይሌ

Zerihun [816 days ago.]
 ሆሆሆሆሆሆ ብለን አሰልጣኙን ማስባረር አለብን ብሔራዊ ቡድናችን ተደፈረ ተዋረደ በሱ ዘመን:: ተከብረሽ የኖርሽው በሰውነት ቢሻው ዮሃንስ አደረገሽ የማንም መፈንጫ ገጠመ አልገጠመ I dont care የውስጤ ብሶት ነው የምተነፍሰው ufffffffffffffffffff

Solemagnawe [816 days ago.]
 ኧረ አይነፋም ዮሃንስ የተባለው አሰልጣኝ ከየት ነው ያመጡብን ? ግን እኔ እሱን ብሆን ኖሮ በዚች ሰዓት እንደማልችል አውቄ እቀየስ ነበር ......

Nati 4 Killo [816 days ago.]
 በዮሃንስ ኮች ዘመን የተገፉት ብሔራዊ ቡድኑን መጥቀም እየቻሉ ግፍ የተሰራባቸው ተጫዋቾች (ምንያህል ተሾመ) (በሃይሉ ቱሳ) (አዲስ ህንፃ) (አስራት መገርሳ) (ምንተስኖት) (ተስፋዬ አለባቸው) (ባዬ ገዛኸኝ) (ቢነያም አሰፋ) (አበባው ቡጣቆ )የቀሩ ካሉ ጨምሩበት .........

Eyasu [816 days ago.]
 የሚፈልጋቸውን ተጫዋቾች መረጠ ልምድ ያላቸውን የሰውነት ቡድን ውስጥ የነበሩትን ልጆች የራሱን ክሬዲት ከፍ ለማድረግ ስልፈልገ ብቻ ገፋቸው ግን የሰራው ስራ በግልፅ ታየ በምስራቅ አፍሪካ ቡድኖች ሳይቀር አሳቀቀን አስቀለደብን አሰደበን የስራህን ይስጥህ ዮሃንስ የተባልክ ኮች ለነገሩ አንተ ላይ ጥፋት የለም ግልፅ ባልሆነ ማስታወቂያ የሾመህ ያለቦታህ ያስቀመጠህ ፌዴሬሽኑ ነው::

Gezegeta [815 days ago.]
 እኔ አሁን የሚያሳስበኝ ሴካፋ አይደለም ቻን ነው ሴካፋ ላይ እንደዚህ የሞተ ሬሳ የሆነ የዮሃንስ ስብስብ ቡድን እንዴት ሆኖ ነው ታዲያ እነ ካሜሮንን..... አንጎላን...... ኮንጎን..... የሚቋቋመው ??? ኧረ ባካችሁ አንድ በሉት ይሄን አሰልጣኝ ሃገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታ የማታውቀውን የጎል መአት የጎል ዝናብ ይዞብን እንዳይመጣ ?!

Mulualem [815 days ago.]
 ሰሚ ካለ ዛሬ በጨዋነት መልኩ ዮሃንስ እንዲባረር እንጮሃለን ..... እንጮሃለን...... እንጮሃለን ....

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!