የሴካፋ ሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ በካምቦሎጆ ይጀመራሉ
ህዳር 20, 2008

በይርጋ አበበ

11 አባል አገራትንና አንድ ተጋባዥ አገርን ይዞ 38ኛ ውድድሩን በኢትዮጵያ እያካሄደ ያለው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ዛሬ በሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ይቀጥላል። ጨዋታዎቹ የሚካሄዱትም በእድሜ ጠገቡ የአዲስ አበባ ስታዲየም ይሆናል። የውድደሩ ሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም መካሄድ የሚጀምሩትም በተጋባዥ አገሯ ማላዊ ከዩጋንዳ ጋር ይገናኛሉ። ጨዋታው የሚካሄደውም በእኩለ ቀን 7፡00 ሰዓት ላይ እንደሚሆን ከፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ክፍል የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

የማላዊ እና የዩጋንዳ ጨዋታ እንደተጠናቀቀ ደግሞ አስተናጋጇ ኢትዮጵያ ከታንዛኒያ ይገኛሉ። ሁለቱ ቡድኖች በምድብ ማጣሪያው በአንድ ምድብ ተደልድለው የነበረ ቢሆንም ታንዛኒያ ከምድቧ በአንደኛ ደረጃ ስላለፈች እና ኢትዮጵያ ደግሞ በምርጥ ሶስተኛ ደረጃ ያለፈች በመሆኑ በሩብ ፍጻሜው ሊገናኙ ችለዋል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ 9፡30 ሲሆን እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

የአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ቡድን ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ እየታየበት ያለው የአቋም መውረድ እና የራስ መተማመን መሸርሸር በዛሬው ጨዋታም በጫና ውስጥ ሆኖ ጨዋታውን እንዲያካሂድ ሳያደርገው እንደማይቀር ይጠበቃል። ብሔራዊ ቡድኑ ለዛሬው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ የደረሰውም በታንዛኒያዎች ድጋፍ ነው ማለት ይቻላል። ታንዛኒያ እና ኢትዮጵያ ባሳለፍነው ቅዳሜ አመሻሽ ላይ በሃዋሳ ስታዲየም ያደረጉትን ጨዋታ አንድ እኩል በሆነ ውጤት እንዲያጠናቅቁ ያስቻሉት የታንዛኒያው ተከላካይ በራሱ ጎል ላይ በማስቆጠሩ ነበር። ተከላካዩ ጎሉን ባያስቆጥር ኖሮ ምናልባት ዋልያዎቹ ምርጥ ሶስተኛ ሆነው ለማለፍ ይቸገሩ ነበር ማለት ይቻላል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Waliyawe [782 days ago.]
 ዛሬ ከፍተኛ ተቃውሞ ይጠብቀዋል ዮሃንስ

JustThinkin [782 days ago.]
 What does the last sentence mean?

Gedfew Mulugeta [782 days ago.]
 ኢትዩፒያ 2 _ 1 ታ

eliyas adama [781 days ago.]
 ስለ ዋልያዎቹ ዮሀንስ አስብበት

ዳንኤል [781 days ago.]
 Sir Coach Sewinet Bishawe our Heroooooo for give us !!! ከነ ስሕተቱም፣ ከነ ጠባዩም፣ ከነጉድለቱም፡፡ ይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡ አበሻን በአንድ እግሩ ያስቆመ፤ ለሃያ አራት ሰዓታት የመግቢያ ትኬት ፍለጋ ያሰለፈ፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የብሔራዊ ቡድኑን ዐርማ የያዙ ቲሸርቶች እንዲቸበቸቡ ያደረገ፤ ሕዝብ እንደ መንጋ ንብ አንድ ዓይነት ዜማ እንዲያዜም ያስቻለ፤ ሽማግሌን እንደ ሕጻን ያስጨፈረ፤ ሕጻንን እንደ ሽማግሌ ያስተከዘ፤ የፓርቲና፣ የዘር፣ የእምነትና የባህልን አጥር አስጥሶ ወገንን በአንድነት ገመድ ያስተሣሠረ፤ ይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡ ተረስተን ነበረ፤ ረስተንም ነበረ፤ ርቀን ነበረ፤ ተርቀንም ነበረ፤ ተርተን ነበረ፤ ተረት ሆነንም ነበረ፤ እግርን ከኳስ አውጥተን ለሩጫ ብቻ አውለነው ነበረ፤ እንዲያ በሩጫ ዓለምን አስደምመን፣ ኳስ ሜዳ ግን ዘጠና ደቂቃ መሮጥ አቅቶን ደክሞን ነበረ፡፡ ሕዝባችን ከካምቦሎጆ ኳስ ወደ ዲ ኤስ ቲቪ ኳስ ፊቱን አዙሮ ነበረ፡፡ ይህንን ቀይሮ በአፍሪካ ምድር ከ31 ዓመታ በኋላ ብቅ እንድንል ያደረገ፤ በዓለም መድረክ ‹እኛም አለንበት› እንድንል ያስቻለ - ይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡ ዳንኤል ክብረት

Ashenafi Kebede [781 days ago.]
 ምን አቃጣይ የሆን አሰልጣኝ ነው ዮሃንስ የሚባል ሰው ብሔራዊ ቡድኑን የመንደር የሰፈር ቲም አስመሰለው አደረገው እኮ:: ኧረ አባሩት ወደዛ ,,,,,,,,, የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰውነት ቢሻውን ይቅርታ መጠየቅ አለበት ይቅር በለን ኮች ሰውነት ቢሻው !

Babi [781 days ago.]
 ምን አይነት ቡድን ነው የሰራው ? ምን አይነት ልጆች ነው የሰበሰበው አሰልጣኙ ? ከማሪያኖ ባሬቶ የባሰ ሆነብን እኮ ዮሃንስ

Samifelex [780 days ago.]
 እኔ የማዝነው የምናደደው በማይችል ኮች እየሰለጠነች ላለችው ሃገሬ ነው ሃገራችን ላይ ለተዘጋጀ ደካማ ውድ ድር ቡድን መስራት የማይችል አሰልጣኝ ምኑን አሰልጣኝ ሆነው .....

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!