ወደ ግማሽ ፍጻሜ ማለፋችን ይገባን ነበር አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ
ህዳር 21, 2008

በይርጋ አበበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሴካፋ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ የታንዛንያ አቻውን በመለያ ፍጹም ቅጣት ምት አሸንፎ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፉን ተከትሎ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ በመግለጫቸው እንዳስታወቁት በቡድናቸው ላይ ያደረው የድካምና ተደራራቢ ጉዳት ቢያሳስባቸውም ጨዋታውን በማሸነፋቸው ግን ድሉ ይገባን ነበር ብለዋል። ከጨዋታው በኋላ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ለአገር ውስጥ ለውጭ አገር ጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት “የሴካፋ ህግ ጎድቶናል እንዲህ ስል ግን በህጉ የተጎዳነው እኛ ብቻ ነን እያልኩ ሳይሆን የእኛ ተጋጣሚ የነበሩት ታንዛንያዎችም ተጎድተዋል። ምክንያቱም በ24 ሰዓታት ልዩነት ጨዋታ ማካሄድ በተጫዋቾች ላይ ጉዳትና ድካም ማሳደሩ አይቀርምና” ያሉ ሲሆን አያይዘውም “ልጆቼ አብዛኞቹ ወጣቶችና በሴካፋ ልምድ የሌላቸው እንደመሆኑ መጠን በድሉ ደስተኛ ነኝ” ብለዋል።

ለአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ከቀረበላቸው ጥያቄዎች መካከል አንዱ “የቡድነዎ አጨዋወት በተለይ በአማካይ ክፍሉ ላይ የተደራጀ እና የተቀናጀ አልነበረም። በተለይ የአማካይ ተከላካዩ የጋቶች ፓኖም ሚና በግልጽ የታየ አልነበረም ይህን እንዴት ያዩታል” የሚለው ይገኝበታል። አሰልጣኙም የጥያቄውን ተገቢነት ገልጸው የጋቶችን ቦታ በተለይም ኤልያስ ማሞን ወደኋላ መልሶ በማጫወት ሊደፍኑት እንደሞከሩ ገልጸዋል። በእለቱም በተለይ ሁለት የመለያ ፍጹም ቅጣት ምት የመለሰውን ግብ ጠባቂው አቤል ማሞን አድንቀውታል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሴካፋ ሩብ ፍጻሜ የታንዛኒያ አቻውን አሸንፎ ለግማሽ ፍጻሜ ማለፍ ቢችልም በጨዋታው ያሳየው አጨዋወት ግን ጥሩ አለመሆኑን ተከትሎ ከደጋፊው ተቃውሞ ደርሶበታል። በተለይ ኳስን ተቆጣጥሮ በመጫወትና ቡድንን በመምራተ በኩል ከፍተኛ ክፍተት ታይቶበታል። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ በሴካፋ ውድድር አንድ ቡድን 20 ማስመገብ የሚችለው 20 ተጫዋቾችን ብቻ በመሆኑ እና ቡድኑም ከያዛቸው ተጫዋቾች መካከል ቋሚ ተሰላፊዎቹ እንደ ራምኬል ሎክ ሳላዲን ባርጌቾ እና ስዩም ተስፋዬ አይነት ተጫዋቾች መጎዳታቸው ቡድኑን ርቃኑን አስቀርተውታል ማለት ይቻላል። በተለይ የተከላካዮቹ ሁለቱ አምበሎች ሳላዲን እና ስዩም መጎዳታቸው ቡድኑን የጎዱት በችግር ጊዜ የማረጋጋትና የመምራት ችሎታቸውንም ይዘው ስለተጎዱ በብዙ መልኩ ነው ቡድኑ ላይ ተጽእኗቸውን ያሳጡት።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Gezegeta [813 days ago.]
 ምንም ነገር ብትናገር አያምርብህም:: ሴካፋ አንተ ምን አይነት ኮች እንደሆንክ ቁልጭ አድርጎ ለሕዝቡ አሳይቷል ይልቅ ዝም ብለህ ቦታውን ልቀቅ ለሌሎች ለሚችሉት.....you are loooooossssssser

Eyasu [813 days ago.]
 እንዴት ይደብራል የሚሰጠው አስተያየት ምንም አይችልም ኧረ አባሩት

Keneddey [813 days ago.]
 ቆይ ዩጋንዳ ላይ ምን ምክንያት እንደምትደረድር ለመስማት ቸኩያለሁ ይሄን ደካማ ስብስብ ይዘህ:: ይልቅ 2 በረኛ ለማስገባት ለማሰለፍ ጥያቄ አቅርብ አለበለዚያ ዩጋንዳ እንደማትችል ያስፎግሩሃል ይቀልድብሃል

Melaku [813 days ago.]
 ምን ማፈሪያ የሆነ ሰው ነው ባካችሁ ወደ ግማሽ ፍፃሜ መግባታችን ይገባን ነበር ይላል አይኑን በጨው አጥቦ ከምድብህ እንዴት እንዳለፍክ እረሳከው እንዴ ?!

እንድሪስ [812 days ago.]
 የጋርድዮላ ሀያልነት ለኢትዮጵያ አይጠቅም ም ዮሀንስ በርታ ይበልልን

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!