የሴካፋ ግማሽ ፍጻሜ እና ካምቦሎጆ
ህዳር 22, 2008

የዋልያዎቹ እና የዩጋንዳ ጨዋታ የጊርጊስ ደርቢ ሆኖአል

ጊዜው እንደ ኢትዮጵያ የዘመን ስሌት 1997 ዓ.ም ሲሆን በካምቦሎጆ የአስራ ሀይሌው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከኬኒያ አቻው ጋር በሴካፋ የግፍጻሜ ጨዋታ እየተጫወቱ ሲሆን የኬኒያው ተጫዋች በቀይ ካርድ ከሜዳ ይሰናታል። የኬኒያውን ተጫዋች ከሜዳ መሰናበት ተከትሎ በአንተነህ አላምረው እና በአሸናፊ ግርማ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአማካይ መስመር በኬኒያ አቻው ላይ የመሀል ሜዳ እና የጎል ሙከራ የበላይነቱን መውሰድ ቻለ። በመጨረሻም የአስራት ሀይሌ ልጆች ከመመራት ተነስተው አቻ መሆን ሲችሉ አሸናፊውን ለመለየት የመለያ ምት ተሰጠ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንም በታኩ ሶስተኛውን የሴካፋ ዋንጫ በማንሳት ካምቦሎጆን ከአፍ እስከገደፉ ሞልቶ የነበረውን የኳስ ተመልካች እና በየቤቱ በትልቪዥን መስኮት ጨዋታውን ይመለከት የነበረውን ኢትዮጵያዊ በደስታ ጮቤ አስረገጡ።

ዋልያዎቹ አምበል ዘውዱ በቀለ ዋንጫውን ለመቀበል ወደ ክቡር ትሪቡን ከማምራቱ በፊት ድምጻዊ መሀሙድ አህመድ ከክቡር ትሪቡን በመውረድ ይትባረክ እንደ አብርሃም የሚለውን ግሩም መዝሙር በመጫወት ደጋውን አዝናና። ጨዋታውን በርዲዮ በቀጥታ ያስተላልፍ የነበረው ደምሴ ዳምጤ በበኩሉ የመለያ ፍጹም ቅጣት ምቱ ሲመታ የአድማጭን ቀልብ በሚስብ ገለጻው የጨዋታውን ከባድነት አስረዳ። ይህ ታክ ከተፈጸመ ዘንድሮ 11ኛ ዓት ሆነው።

የኢትዮጵያ ብሄራ ቡድን ከ11 ዓመት በኋላ በአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ እየተመራ በ38ኛው የሴካፋ ዋንጫ ለግማሽ ፍጻሜ መድረሽ ችሎአል። የዋልያዎቹ ተጋጣሚ አገር ደግሞ ልክ እንደ ኬኒያ ሁሉ የኢትዮጵያን እግር ኳስ ጠንቅቀው የሚያውቁት ዩጋንዳዎች ናቸው። ዩጋንዳዎች ከተከላያቸው አይዛክ ኡሴንዴ እና ከታላቁ ግብ ጠባቂያቸው ሮበርት ኦዶንካራ በተጨማሪ አሰልጣኛቸው ሰርዲዮቪች ሚሉቲን ሚቾ በቅዱስ ጊዮርገፊስ እግር ኳስ ክለብ ያለፉ በመሆናቸው የኢትዮጵያን ብሄራዊ ቡድን ጠንቅቀው የሚያውቁ ያደርጋቸዋል። ጨዋታውም በዋልያዎቹ እና በፈረሰኞቹ መካል የሚካሄድ አስመስሎታል።

በሌሎች የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ሩዋንዳ ከሱዳን ይገናኛሉ። ጨዋታዎቹ ነገ በአዲስ አበባ ስታየም ወይም በተለምዶ በካምቦሎጆ የሚካሄዱ ሲሆን የአዲስ አበባ እግር ኳስ አፍቃሪም በስታየም በመታደም ጨዋታዎቹን ቢመለከት ለዋልያዎቹ ጥንካሬ ስለሚሰጥ ስታዲየም መግባቱን ባያቆም ይመከራል።

በተያያዘ ዜና በ38ኛው የሴካፋ ውድድር ከፍተኛ ጎል አግቢነቱን የሱዳኑ አታር ኤል ጣሂር በአራት ጎሎች እየመራ ሲሆን ነገ ከኢትዮጵያ ጋር የሚጫወተው የዩጋንዳው ሚያ ፋሩክ የሩዋንዳው ቱሴንጌ ጃገኩስ እና የታንዛኒያው ጆን ቦኮ በእኩል ሶስት ጎሎች ይከተላሉ። በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በኩል ከአንድ ጎል በላይ ያስቆጠረ ተጫዋች አለመኖሩን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
ክብር ለኮች ሰውነት ቢሻው [779 days ago.]
 ዛሬ ዮሃንስ ላይ ዩጋንዳዎች የሚቀልዱበት ይመስለኛል:: በዳካማዎቹ የምስራቅ አፍሪካ ሃገሮች ሲቀለድበት የከረመው ፌክ ኮቻችን በእድልና በፀሎት ጥሩ ሶስተኛ ሆኖ ያለፈው ዮሃንስ ዛሬ በምስራቅ አፍሪካዋ ጠንካራ ቡድን የብዙ ጊዜ ሻምፒዮኗ ዩጋንዳ ይሄ የመንደር ቲም የመሰለው ቡድኑ አይሆኑ ሲሆን ሲፈረካከስ ይታየኛል ሚቾም ጥሩ ነገር ያሳየናል ብዬ እጠብቃለሁ::

Marta [779 days ago.]
 ዛሬ ሚቾ ጥሩ ነገር ያሳየናል ምርጥ ቡድን ሰርቷል በጣም ሊደነቅና ሊከበር የሚገባው የአፍሪካን ፉትቦል በተለይ የምስራቅ አፍሪካን ፉትቦል ጠንቅቆ የሚያውቅ ምርጥ አሰልጣኝ ነው:: ዛሬ ዮሃንስ ምን እንደሚውጠው እኔንጃ በጠባብ ጎል ከተሸነፈ እድለኛ ነው ::

Leul Mekonen [779 days ago.]
 በዛሬው እለት የዮሃንስ ደካማ ቡድን ምን የሚግጥመው ይመስላቹሃል በዩጋንዳ ? ግምታችሁን ከተሰጡት ምርጫዎች ውስጥ ይምረጡ ጣል ጣል አድርጉ ? ትክክለኛውን ግምት ላገኘ ሽልማት አለው የ ፻ ብር ካርድ ሀ| 3 ለ 1 ይሸነፋል ለ| 2 ለ 0 ይሸነፋል ሐ| 4 ለ 1 ይሸነፋል መ| ሁሉም መልስ ነው

gamo [779 days ago.]
 መ. ሁሉም መልስ ነው ሃሃሃሃሃሃ ምርጥ ጥያቄ ነው

Abdu from Awassa [779 days ago.]
 ሐ| 4 ለ 1 ይሸነፋል

Dani man [779 days ago.]
 ሀ| 3 ለ 0 ይሸነፋል

Hana [779 days ago.]
 ሠ. 2 ለ 1 ይሸነፋል

Gizegeta [779 days ago.]
 @ ኳስ ጤነኛ ሰው ከሆንክ ጭንቅላህ ማመዛዘን የሚችል ቢሆን ኮች ሰውነት ቢሻው ለሃገሩ ምን ታሪክ እንደሰራ ማመዛዘን አያቅ ት ህም ነበር ለነገሩ አነተ ጭፍን የሆነ ክለብ እየደገፍክ አይምሮህ ጭፍን ሆናል የዮሃንስ ቡድን ከ ሰውነት ቢሻው ቡድን ይሻላል ትላለህ::

Leul Mekonen [779 days ago.]
 le ኳስ :- ኧረ ዝም በል የሰውነት ቢሻው ቡድን ይከብድሃል ሰውነት ማንም ላይደርስበት ከፍ ብሎ የተ ሰቀለ የጀግኖች ጀግና የሆነ ምርጥ አሰልጣኝ ነው

felexsami [779 days ago.]
 የሰውነት ቢሻው ስም መወደሱ ምነው አቃጠለህ ሰውነት ቢሻው እኮ ስራ ሰርቶ ውጤት አምጥቶ ነው በሕዝብ ልብ ውስጥ የገባው:: ይልቅ ለአንተ ምርጡ ኮች ለሆነው ዮሃንስ ምከረው ከጋዜጠኞችና ከደጋፊዎች ጋር ከሚነታረክ ስራ ስራ እንደ ኮች ሰውነት ቢሻው በለው አለበለዚያ ቦታውን ለተገቢው ሰው ልቀቅ

Sisaye [779 days ago.]
 2 ለ 1 ዮሃንስ የሚሸነፍ ይመስለኛል

Lemeneh [779 days ago.]
 የኔ ግምት Ethiopia 1 - 3 Uganda

AbduilBunna [778 days ago.]
 የዩጋንዳ ቲም ትላንትና ምን እንደነካው እኔንጃ እንደወትሮው አልነበረም ኢትዮጵያን በቀላሉ ያሸንፋል ተብሎ ተጠብቆ ነበር ምክንያቱም ሚቾ ጥሩ ቡድን ሰርቷል የአፍሪካ ዋንጫና የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ላይ እንዳየነው ቡድኑ ጥሩ ነው ::

mola misgun [777 days ago.]
 ለወደፊት ማሰብ የሚሻል ይመስለኛል

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!