ዋልያዎቹ በሜዳቸው ለነሃስ ሜዳልያ ይጫወታሉ
ህዳር 24, 2008

በይርጋ አበበ

በ38ኛው የሴካፋ ሲኒየር ቻሌንጅ ካፕ ትናንተ ከእኩለ ቀን ጀምሮ በተካሄዱ ሁለት የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ወደ ፍጻሜ ያለፉትን ቡድኖች አሳውቀዋል። በውጤቱ መሰረትም ዋለያዎቹ በተጋጣሚያቸው በዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን በደረሰባቸው ሽንፈት ምክንያት የፍጻሜው ተፋላሚ ሳይሆኑ ቀርተዋል። በዚህ የተነሳም በሜዳው የሚጫወተው የአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ስብስብ የነሃስ ሜዳልያ ለማግኘት የሚጫወት ሆኗል። ከዩጋንዳ ጋር ነገ ለፍጻሜ የሚጫወትው ቡድን የአራተኛው ቻን ዋንጫ አዘጋጅ የሆነው የሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድነ ነው። ሩዋንዳዎች የፍጻሜ ተፋላሚነታቸውን ያረጋገጡት ለ80 ደቂቃ በአስር ተጫዋች የተጫወተውን የሱዳንን ብሔራዊ ቡድን በመለያ ምት አሸንፈው ነው። ጨዋታዎቹ ምን መልክ እንደነበራቸው ከዚህ በታች እንመለከታለን።

Ethiopia vs Uganda CECAFA SEMI-FINAL


ቀድሞ የተሸነፈው የሱዳን ብሔራዊ ቡድን

በሴካፋ ዋንጫ እስከ ግማሽ ፈጻሜ በተካሄዱ አራት ጨዋታዎች አነስተኛ የጎል ቁጥር የተቆጠረበት የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ነበር። ቡድኑ በምድብ ማጣሪያው በማላዊ ሁለት ጎለሎች ከተቆጠሩበት ውጭ በቀሪዎቹ ሶስት ጨዋታዎች መረቡን ሳያስደፍር ነበር ለግማሽ ፍጻሜ መድረስ የቻለው። ትናንት በተካሄደው የሩዋንዳ እና የሱዳን ብሔራዊ ቡድኖች የግማሽ ፍጻሜ ጨዋa ታuሱdዳኖች ተከላካያቸው በመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተነሳበተባቸው። የአንደ ተጫዋች ቁጥር ጉድለት የተፈጠረባቸው ሱዳኖችም የተጋጣሚያቸውን የጎል ክልል ደጋግመው ከመጎብኘት ይልቅ በራሳቸው የጎል ክልል ላይ ተሰባስበው በማህበር ተደራጅተው መከላከልን ቀዳሚ እቅዳቸው አድርገው ታይተዋል።

የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ወደ ተጋጣሚው የጎል ክልል ደጋግሞ ለመሄድ ሙከራ ካለማድረጉም በላይ መደበኛውን 90 ደቂቃ እና ተጨማሪውን 30 ደቂቃ በሙሉ በኒያስብል መልኩ ሰዓትለማባከን ሲሞክር አምሽቷል። በዚህ የተነሳም የተጋጣሚያቸውን የተከላካይ መስመር ጥንካሬ ሳይፈትኑ በማምሸታቸው እንጂ ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ማድረግ ቢችሉ ኖሮ የሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድን ሊሸነፍ የሚችል ቡድን እንደነበረ ሱዳኖች ባደረጓቸው ውስን ሙከራዎች ታይቷል።

ሁለቱ ቡድኖች በመደበኛው 90 ደቂቃ ጎል ማስቆጠር ተስኗቸው ቢያመሹም በጭማሪው 30 ደቂቃ ግን እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ጎል በማስቆጠር የሁለቱ አሸናፊ በመለያ ምት እንዲለይ ተደርጓል። ሩዋንዳዎች ግዳጃቸውን በሚገባ መወጣት ሲችሉ የሱዳኖች ሁለት ሙከራዎች ደግሞ ዓላማቸውን ሳይመቱ በመቅረታቸው ሊሸነፉ ችለዋል። የፍጻሜው ድግስም ተቋዳሽ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

ኢትዮጵያ ከዩጋንዳ የእለቱ ምርጥ ጨዋታ

ሁለቱ ቡድኖች የተገናኙት የጸሀዩ ግለት ገና መብረድ ሳይጀምር ቢሆንም ጸሀዩ እየቆየ መብረዱን ተከትሎ በሁለቱም ቡድኖች መካከል ማራኪ እና ፈጣን የኳስ ቅብብል የታየበት ጨዋታ አካሂደዋል። ለ10 ደቂቃዎች የረባ የጎል ሙከራ ያልተደረገበት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ እስከ አስረኛው ደቂቃ ድረስ እርስ በእርስ በመጠናናትና ወደ ጨዋታው ሪትም ለመግባት ጥረት ሲደረግበት የቆየ ጨዋታ ነበር። በ12ኛው ደቂቃ ግን የሩዋንዳው አምበል ፋሩክ ሚያ በዋልያዎቹ ተከላካዮች መካከል ገብቶ ወደ ጎል የሞከራት ጠንካራ የጎል ሙከራ በአቤል ማሞ ጥረት ከመረቡ ሳታርፍ ቀርታለች።

Waliya Fans


ከፋሩክ ሚያ ሙከራ በኋላ ዋልያዎቹ በራምኬል ሎክ እና አስቻለው ግርማ አማካኝነት ለጐል ያልቀረቡ ሙከራዎች ያደረጉ ቢሆንም በዋናነት ሊጠቀስ የሚችለው የእለቱ የመጀመሪያ ጠንካራ ሙከራቸው ግን በጋቶች ፓኖም አማካኝነት ከቅጣት ምት ተሞክራ በግብ ጠባቂው ጥንካሬ ወደ ውጭ እንድትሄድ የተደረገችዋ ሙከራ ነች። ይችህ ሙከራ የተደረገችው በ20ኛው ደቂቃ ላይ ነው። በአጠቃላይ እስከ 45ኛው ደቂቃ ድረስ ሁለቱም ቡድኖች በመሃል ሜዳ እና በመስመር የተወሰነ የጨዋታ እንቅስቃሴ ሲያካሂዱ ቀይተው እረፍት ሊወጡ ስድስት ደቂቃዎች ሲቀራቸው ግን መሀመድ ናስር ዋልያዎቹን መሪ ማድረግ የምትችል ምናልባትም ወደ ፍጻሜው ልታሸጋግር የምትችል የጎል እድል ቢያገኝም ሳይጠቀምባት ቀረ።

ከእረፍት መልስ ይበልጥ ተጠናክረው የገቡት የዮሃነስ ሳህሌ ልጆች በተለይ በቢኒያም በላይ እና በበረከት አዲሱ አማካኝነት ያደረገቸው የጎል ሙከራዎች በዩጋንዳው ግብ ጠባቂ ጥረት ጎል ከመሆን ዳኑባቸው እንጂ ለጎል የቀረቡ ነበሩ። ከእነዚህ በተጨማሪም የዩጋንዳው አምበል ሚያ በድጋሚ የማግባት እድል ማግኘት ቢችልም በዋልያዎቹ ተከላካዮች ንቃት ምክንያት ኳሷ መረቡን ሳትነካ ቀርታለች።

90 ደቂቃ ሙሉ 22 ሰዎች እንደ እብድ ውሻ ሲንከራትቷት ያመሸችው ኳስ አንድም ጊዜ መረብ ላይ ማረፍ ባለመቻሏ አሸናፊውን ቡድን ለመለየት ተጨማሪ 30 ደቂቃ ቢቆረጥላቸውም ኳሷ ግን መረቡን መንካት ሳትችል ቀርታለች። በመጨረሻም በመለያ ፍጹም ቅጣት ምት ዩጋንዳዎች አሸናፊ ሆኑ። ዋልያዎቹ ተሸናፊ የሆኑበትን ፍጹም ቅጣት ምት ያመከነው አምበሉ ጋቶች ፓኖም ነው።

የዋልያዎቹ የእለቱ አቋም

በትናንትናው ጨዋታ ዋልያዎቹ ያሳዩትን ብቃት የተመለከቱ ስፖርት ተከታታዮች ካለፉት ቀናት የተሻለ ሆነው እንደቀረቡ ተናግረዋል። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ አሰልጣኘ ዮሃንስ ሳህሌ ምርጡን ኳስ አቀጣጣይ ኤልያስ ማሞን ነጻ ሆኖ እንዲጫወት ስለፈቀዱለት ነው ማለት ይቻላል። የእለቱ የሱፐር ስፖርት ኮከብ ተጫዋች ኤልያስ ማሞ ከቡድን አጋሮቹ ጋር የነበረው ቅንጅት በተለይም ከቢኒያም በላይ ጋር ያሳዩት ጥምረት መልካም ነበር። ከዚህ በተጨማሪም በተደጋጋሚ ታክቲካል ዲስፕሊን የለውም እየተባለ የሚተቸውና ያለፉት የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች የቡድኑ ድክመት ተደርጎ ይቆጠር የነበረው ጋቶች ፓኖም በትናንቱ ጨዋታ ካለፉት ሳምንታት በመጠኑም ቢሆን የተሻለ ሆኖ ታይቷል።

በአስቻለው ታመነ እና አንተነህ ተስፋዬ የሚመራው የዋልያዎቹ የተከላካይ መስመር ጥምረቱ እጅግ መልካም ነበር ብሎ መናገር ይቻላል። ሁለቱ ወጣት የደቡብ ክልል ተወላጆች የፈጠሩት ጥምረት የመስመር ተከላካዮቹን ነጂብ ሳኒን እና ዘካሪያስ ቱጂም ሆነ የጎሉን ዘበኛ አቤል ማሞን በነጻነት እንዲጫወቱ መተማመኛ መሆን ችለዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ባደረገው አምስት ጨዋታ የተቆጠረበት የጎል ብዛት ሶስት ብቻ መሆኑም የተከላካይ መስመሩን ጥንካሬ የሚያሳይ ነው።

በእለቱ በዋልያዎቹ በኩል የተሻለ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ያመሸው ኤልያስ ማሞም ጨዋታው ኮከብ ተብሎ በዲኤስ ቲቪ መመረጡ ቡድኑ ካለፉት ጨዋታዎቹ እየተሻሻለ ለመቅረቡ ማሳያ ነው።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Hana [811 days ago.]
  sorry i dont like our coach Yohanes. his arogant person he must respect the fans and must call experiance players.Better Sewinet Bishawe is good.

ኳስ [811 days ago.]
 በትላንቱ ጨዋታ ኮኮብ ያልነበሩ ተጫዋቾች አጥቂ ቦታ የገቡት መሀመድ ናስር፣ ራምኬሎ እና በሇላ ተቀይሮ የገባው በረከት ብቻ ነበሩ። በትላንቱ ቡድን ባዬ ገዛህኝ፣ ምንይሉ ወንድሙ አይነት አጥቂ ቢያገኝ ኖሮ ዎው የሚያስብል ውጤት ከኳስ ጋር እናይ ነበር። ከሇላ ሁሉም ኮከብ የነበሩ ቢሆንም አስቻለው ታመነ እና ከመሃል ቢኒያ ለኔ የበለጠ ምርት ነበሩ። አሰልጠኝ ዮሃንስ ትላንት የሰራው ቡድን ምርጥ ነው። አትቂውን ክፍል ግል ሙሉ በሙሉ መቀር ይኖርበታል። በነበረከት ይሳቅ የትም መድረስ አይችልም።

Bereket (Beka) [811 days ago.]
 በጣም ያሳፍራል አዘጋጅ ሃገር ለነሃስ ሜዳሊያ ስትጫወት ማየት shame on you Yohanes

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!