ኡጋንዳ የ38ኛው የምስራቅና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒኦን ሆነች
ህዳር 25, 2008

ኢትዮጵያ ባዘጋጀችውና ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተጠናቀቀው  የ38ኛው የምስራቅና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ  ፍጻሜ ጨዋታ ኡጋንዳ የዋንጫ ተጋጣሚዋን ሩዋንዳን በ13ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረችው ጎል 1ለ0 በማሸነፍ በሴካፋ የምንጊዜም የበላይነትዋን አስጠብቃ ሻምፒዮን ሆናለች። በቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን  አሰልጣኝ የሚሰለጥኑት ኡጋንዳዎች የሴካፋን ዋንጫ ሲያነሱ  ለ14ኛ ጊዜያቸው መሆኑ ነው።

UGANDA CECAFA Champion 2015 A.A Ethiopia


ሩዋንዳዎች በተለይ ከረፍት መልስ በማያቆርጥ በቀኝ ጥላ ፎቅ በተሰበሰቡ ደጋፊዎቻቸው የሞቀ ድጋፍ    በመታገዝ አቻ ለመሆን ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም የአሰልጣኝ ሚቾ ተከላካዮች በራቸውን  እስከመጨረሻው አላስደፈሩም።  ወደ መቶ የሚጠጉት የሩዋንዳ ደጋፊዎች ጨዋታው ከተጀመረ ጀምሮ የለማቋረጥ ድጋፍ ለቡድናቸው ሲሰጡ ላያቸው ያስቀናሉ። ውጤቱ ምንም ይሁን ምንም እንደዚህ አይነት የሀገር ፍቅር ስሜት የተላበሰ ድጋፍ የሀገራቸውን ማሊያ ለብሰው ለተጫወቱት ተጫዋቾች በመስጠታቸው ተመልካች የናፈቀውን ወና ስታዲየም  ትንሽም ቢሆን አድምቀወት አምሽተዋል። 

ከዋንጫው ጨዋታ ቀደም ብሎ ለሶስተኛ ደረጃ የተጫወቱት ኢትዮጵያና ሱዳን በመደበኛው ሰአት  በ56ኛው ደቂቃ በኤሊያስ ማሞ ጎል ኢትዮጵያ መምራት ብትችልም ሱዳኖች በ82ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠሩት ጎል አቻ ለመሆን ችለዋል። ጨዋታው በመደበኛው ሰአት 1ለ1 በመጠናቀቁ   አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የፍጹም ቅጣት ምት አዘጋጅዋ ሀገር ኢትዮጵያ  5ለ4 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሶስተኛነትን ደረጃ ለማግኘት ችላለች። 

በውድድሩ መጨረሻም አሸናፊው የኡጋንዳ ቡድን ከእለቱ የክብር እንግዳ የአሸናፊነቱን ዋንጫ ተረክቧል። ሁለተኛና ሶስተኛ ለወጡት የሩዋንዳና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድኖች የብርና የነሀስ ሜዳለያም ተበርክቶላቸዋል።
Elias Mamo Best Player Of CECAFA 2015 Championship


በውድድሩ የኮኮብ ተጫዋችነት ክብርን  የዋሊያዎቹ የመሃል ተጨዋች ኤልያስ ማሞ  ሲወስድ የኮኮብ ግብ አግቢነቱን በ5ት ጎል የሱዳኑ አጥቂ አልታየር ወስዷል። ኮኮብ በረኛ ከኡጋንዳ እንዲሁም ኮኮብ አሰልጣኝ ከረዋንዳው ተመርጠዋል። 

Empty Stadium

ኢትዮጵያ ባዘጋጀችው በዚህ በ38ኛው የምስራቅና መካከለኛው የአፍሪካ ሃገሮች እግር ኳስ ሻምፒዮና የታዘብነውና በሀገራችንን እግር ኳስ አፍቃሪ ታሪክ  አዲስ ክስተት የሆነብን  ነገር ቢኖር  በዛሬው የዋንጫ ጨዋታና የውድድሩ የፍጻሜ የታየው የተመልካች መራቆት ነው።  የኢትዮጵያ እግር ኳስ አፍቃሪ እውነት እግር ኳስ ያፈቅራል ወይ እስኪያስብል በሀገሩ የተዘጋጀን ዋንጫ ቡድኔ ለዋንጫ ካልደረሰ በማለት በማኩረፍ በእንግድነት ተጋብዘው የመጡትን ሀገራት የዋንጫ ጨዋታ ለማየት ፈቃደኛ አለመሆኑ እጅግ  ቅር የሚያሰኝ ጉዳይ ሆኖ አልፏል።  በኢትዮጵያ እግር ኳስ ተመልካች  ታሪክ የዛሬው  የዋንጫ ጨዋታ በዝግ ስታዲየም እንዲካሄድ የታዘዘ እስኪመስል  ድረስ በተመልካች የተራቆተ አለማቀፍ የዋንጫ ጨዋታ ሳይሆን አይቀርም። ሀገራችንንም ትዝብት ውስጥ የሚከት ነው። ምክንያቱም እግር ኳስ ሰላማዊ ስፖርት ነው ከአዝናኝነቱም በተጨማሪ  ተፎካካሪ ሀገራትን ህዝቦችን የሚያቀራርብ ወንድማማችነትን የሚያመጣ የሀገራትን ስብእና፣ ባህል፣ የአስተሳሰብና  የስልጣኔ ደረጃ   የሚታይበት መድረክ ነው። በዛሬው ጨዋታ ኢትዮጵያ የጋበዘቻቸውን እንግዶቿን  ጎረቤቶቿን ባዶ ስታዲየም ለዋንጫ ተጫወቱ ማለቷ በአፍሪካ የነበራትን የጨውነትና የአስተዋይነት የአስተሳሰብ የበላይነት መሪነት እየለቀቀች መሆኑን ያሳያል። ምንም ይሁን ምንም እንኳን የጋበዝነውን እንግዳ  ሳንጠራው የመጣን እንግዳ በአክብሮት የመቀበልና የመሸኘት ባህላችን የት እብስ ብሎ እንደጠፋ ፈልገን ልናገኘው የሚገባ ጉጋይ ነው። ሀገራትን  በተለይም የአህጉራችንን ኳስ ተመልካች ስናማበት የኖርነውን በማሸነፍ ላይ ብቻ የተመዘነ  ተራ ስሜታዊ ደጋፊነት በብዙሃኑ ደጋፊ ላይ ሲንፀባረቅ በሀገራችን በማየታችን ቅር ተሰኝተናል።  ባለፈው ሀሙስ በፍጹም ቅጣት ምት ባንሸነፍ ኖሮ አስተያየታችንም ሆነ ስታዲየማችን  ምን ሊመስሉ እንደሚችሉ ሁላችንም የምንገነዘበው ነገር ነው። 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
ታዬ ገብሩ [809 days ago.]
 እውነት ነው የምልህ ይህ ገንቢ እና አስተማሪ አስተያየት በመሆኑ አከበርኩህ

ይሁን [803 days ago.]
 ምንግዜም ቡና

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!