ኢትዮጵያ ቡና በአምስተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው እና የጉባኤው ቅኝት
ህዳር 25, 2008

በይርጋ አበበ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ በአሁኑ ወቅት የክለቡን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ለጋዜጠኞች ክፍት በማድረግ ብቸኛ የሆነው ኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ትናንትናም አምስተኛውን ጠቅላላ ጉባኤ በኔክሰስ ኢንተርናሽናል ሆቴል አካሂዷል። 39 አባላት ያሉት የክለቡ ጠቅላላ ጉባኤ በትናንትናው ጉባኤው ያለፈውን ዓመት እቅድ አፈጻጸም ገምግሞ የሂሳብ ሪፖርቱንም በውጭ ኦዲተር አስጠንቶ የኦዲተሩን ውጤት ይፋ ያደረገ ሲሆን በዚህ ዓመት የክለቡን እቅድ ይፋ አድርጓል። ክለቡን ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት የሚመሩትን የስራ አመራር ቦርድ አባላትንም አስመርጦ አጸድቋል። የጉባኤውን ውሎ ጠቅላላ ይዘት በተመለከተ ከዚህ በታች እንዲህ ተሰናስኖ ቀርቧል።

ያለፈው ዓመት የክለቡ ጉዞ

የ2007 ዓ.ም የክለቡን ጉዞ በተመለከተ የስራ አመራሩ ቢርድ ሰብሳቢ መቶ ለቃ ፈቃደ ማሞ እና የክለቡ ዋና ስራ አስኪያጅ እና የቦርዱ ፀሀፊ አቶ ገዛኸኝ ወልዱ እንዲህ ገልጸውታል። መቶ ዓለቃ ፈቃደ ማሞ የጉባኤው ተሳታፊዎች እንኳን ደህና መጣችሁ ብለው በከፈቱት ንግግራቸው ያለፈውን ዓመት የክለባቸውን ጉዞ በሁለት ተጻራሪ ጎራዎች ከፍለው እንደሚያዩት ገልጸው “የመጀመሪያው ክለባችን ከፍተኛ ገቢ የጨያገኘበት እና የስፖርት ማዕከል ግንባታችንም የተጠናቀቀበት ዓመት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በተለይ ዋናው የወንዶች ቡድናችን ከተጠበቀው በታች ወርዶ መገኘቱ ነው” ሲሉ ገልጸውታል።

ከመቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ብዙም ያልተለየ ገለጻ ያቀረቡት አቶ ገዛኸኝ ወልዴ መቶ ዓለቃ ከገለጹት በተጨማሪ ደግሞ ክለቡ ባለፈው ዓመት በተለይ በወንዶች ቡድን በኩል የገጠመውን ድክመት ምክንያት እና የተወሰዱ እርምጃዎችን አቅርበዋል። አቶ ገዛኸኝ ክለባቸው በ2007 ዓ.ም አከናውነዋለሁ ብሎ ያቀደባቸው 15 ነጥቦች እንደነበሩ ገልጸው ከእነዚህ መካከልም “የወንዶች ዋናው ቡድን በፕሚየር ሊግ በጥሎ ማለፍ እና በአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ የድል ባለቤት እንዲሆን ማድረግ ከ17 ዓመት በታች እና ተስፋው ቡድን በተከታታይ ለዋናው ቡድን ተገቢ ተጫዋቾችን እንዲመግቡ ማስቻል የተጫዋቾች መኖሪያ ካምፕ ግንባታን በማጠናቀቅ ተጫዋቾችን ወደ ካምፑ ማዘዋወር የህዝብ ግንኙነት ስራውን በማጠናከር ደጋፊውን በልማት ተሳታፊ እንዲሆን ማድረግ እና ከስፖንሰሮች ጋር በነበጋገር በተለያዩ መንገዶች የክለቡን ደጋፊዎች ፍትሃዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ” የሚሉት እንደሚገኙበት አስታውቀዋል።

ከእነዚህ እቅዶች መካከልም በተለይ የወንዶች ዋናው ቡድን እንደተጠበቀው መሆኑ ቀርቶ ለማሰብ በሚከብድ መልኩ ውጤቱ አሽቆልቁሎ እና ደጋፊውንም ተስፋ አስቆርጦ መክረሙን ዋና ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል። የተስፋው እና ከ17 ዓመት በታች ያለው ቡድን ለዋናው ቡድን ተተኪ ተጫዋቾችን በማፍራት በኩል ደግሞ ስኬታማ መሆናቸውን ተናግረዋል። ክለቡ በሁለት የበጀት ዓመቶች አስር ተጫዋቾችን ወደ ዋናው ቡድኑ ማሳደጉን አውስተዋል።

አቶ ገዛኸኝ ባቀረቡት የ2007 ዓ.ም የክለቡ እቅድ ሪፖርት ከተገለጹት ጉዳዮች መካከል የወንዶች ቡድን በፕሪሚየር ሊጉ 26 ጨዋታዎችን አካሂዶ ዘጠኙን ብቻ አሸንፎ በዘጠኙ ተዘርሮ ሰባቱን ደግሞ ነጥብ ተጋርቶ በመውጣት ስድስተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀበትን ሪፖርት ያቀረቡት ይገኝበታል። ክለቡ እንደዚህ እጅግ የወረደ ውጤት ያስመዝግብ እንጂ የውድድር ዓመቱ ከመጀመሩ በፊት የአሰልጣኞችን ስታፍ በሙሉ በአዲስ ማዋቀሩንና አሰልጣኞቹም የሚፈልጓቸውን ተጫዋቾች ከአገር ውስጥ እንዲያስፈርሙ ነጻነት ተሰጥቷቸው ስለነበረ ማስፈረማቸውን እንዲሁም ከውጭ አገር ለሙከራ የተጠሩ ተጫዋቾችን ፈልገዋቸው አስፈርመዋል። ሆኖም ውጤቱ በመጥፋቱ ተጠያቂ ተደርገው እርምጃ ተወስዶባቸዋል ሲሉ የተናገሩ ሲሆን ለውጤቱ መጥፋት ከአሰልጣኞች በተጨማሪም በተጫዋቾች መካከል የቡድን አንድነት ስሜት ወይም ቲም ስፕሪት አለመኖር እና ለማሸነፍ ተነሳሽነት የሌላቸው መሆኑ አንዱ ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል።

አቶ ገዛኸኝ ከውጤቱ ቀውስ በተጓዳኝ የተወሰዱ እርምጃዎች መኖራቸውን ገልጸው ከእነዚህ እርምጃዎች መካከል “የማይደፈር የሚመስሉ ትልልቅ ውሳኔዎችነ የወሰነበት ዓመት ነው” ሲሉ የክለቡ አመራሮች ባለፈው የውድድር ዓመት ከባባድ ውሳኔዎችን ማሳለፍ የቻሉበት ዓመት እንደሆነ ጠቁመዋል። በርካቶች ይህን የአቶ ገዛኸኝን ንግግር አምበሉን ዳዊት እስጢፋኖስ ከክለቡ እንዲሰናበት የተወሰነውን ውሳኔ ለማለት ፈልገው እንደሆነ ገምተዋል። ዳዊት እስጢፋኖስ በቡና ቤት ውስጥ እጅግ የሚከበርና የማይነካ ተጫዋች ተደርጎ የሚታይ ቢሆንም ባለፈው የውድድር ዓመት መገባደጃ አካባቢ ግን ክለቡ ዳዊትን ማሰናበቱ ተነግሯል።

ቀጣይ የክለቡ ጉዞ

የክለቡን ቀጣይ ጉዞ በተመለከተ ከደጋፊዎች ማህበር ተወካዮች እና ከጠቅላላ ጉባኤ አባላት እንዲሁም ከክለቡ ኃላፊዎች የተነሱ ሀሳቦች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። በዋናነት የክለቡን አዲስ ስታዲየም ግንባታ ማስጀመር እና የዋናውን ቡድን ውጤት ጥሩ እንዲሆን ማድረግ ማለትም በሚወዳደርባቸው የውድድር ሜዳዎች ሁሉ በአሸናፊነት እየተወጣ የዋንጫ ባሌቤት እንዲሆን ማድረግ እንዲሁም የክለቡን ገቢ ማሳደግ በዋናነት በእቅድ ተይዘዋል።

ከደጋፊ ማህበር ተወካዮች እና ከጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎች ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል “ባለፈው ዓመት ስድስትኛ የወጣን ቡድን እንዲሁም በዚህ ዓመት ገና እየተሰራ ያለን ቡድን ለዋንጫ መጠበቅ እንዲሁ ደጋፊዎችን ተስፋ ከመመገብ ተለይቶ አይታይም። ክለቡ 40ኛ ዓመቱን ለማክበር ጥቂት ወራት ብቻ ነው የቀረው። ለክለቡ በዓል አባበር የታሰበው ምንድን ነው?” የሚል ይገኝበታል። ለጥያቄዎቹ ሁሉ መልስ የሰጡት የክለቡ ዋና ስራ አስኪያጅ እና የቦርድ ሰብሳቢው ናቸው። ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ ገዛኸኝ እንደተባለው የዋናው ቡድን ውጤት የተለጠጠ እቅድ እንደሆነ አምነው ነገር ግን እንደቡና አይነት ግዙፍ ክለብ ውድድሩን መጀመር ያለበት ዋንጫን ታሳቢ አድርጎ እንጂ መሸነፍን አስቦ አይደለም ብለዋል። የክለቡን 40ኛ ዓመት በዓል አስመልክቶ በዚህ ዓመት በደማቅ ሁኔታ ማክበር እንደማይቻል ገልጸው ነገር ግን የበዓሉ አከባበር ቅድመ ዝግጅት በዚህ ዓመት እንደሚጀመርና ለዚህም እቅድ መያዙን የስራ አመራር ቦርዱ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ተናግረዋል።

የክለቡን ገቢ ለማሳደግ በተመለከተ ከቡና ላኪዎች ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ሁሴን አብራራው “ክለቡን ለማጠናከር ማህበራችን የሚያደርገውን ጥረት አሁም በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል። ከዚህ በዘለለም ከአንድ ወይም ከሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም የቡና ኢግዚቪሽን ታካሂዳለች። ያ ትልቅ መድረክ ሲሆን በዚያ መድረክ ክልባችንን የማስተዋወቅ እና ወደ ዓለም ህዝብ ለማቅረብ እንጠቀምበታለን” ሲሉ ተናግረዋል።

በመጨረሻም ክለቡን ለመጪዎቹ አራት ዓመታት በስራ አመራር ቦርድ አባልነት የሚመሩ የቦርድ አባላትን ምር አካሂዷል። በክለቡ መተዳደሪያ ደንብ መሰረትም ከየዘርፉ የተውጣጡ 11 የስራ አመራር ቦርድ አባላት ምርጫ ተካሂዶ የቦርድ ኃላፊዎችም ተመርጠዋል። በዚህም መሰረት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ በድጋሚ የቦርዱ ሰብሳቢ ተብለው ሲመረጡ አቶ መኩሪያ መርጊያ ምክትል ሰብሳቢ እና አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ደግሞ የቦርዱ ፀሀፊ ሆነው ተመርጠዋል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Babi [741 days ago.]
 በ 13 ዓመት አንድ ጊዜ ሻምፒዮን የሚሆንና ከተማ የሚረብሽ የመንደር ቲም

AbduilBunna [741 days ago.]
 መቼ ነው የስራ አመራሩ ቢርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ቦታውን ለተገቢው ሰው የሚለቀው በእሱ አመራር እየተመራን ብዙ አመታቶች ብናሳልፍም የክለባችን ጉዞ ግን እንደ ግመል ሽንት ወደ ሃላ ከሆነ ቆየ

Magnawe [740 days ago.]
 ቡላ ገለባ በየአመቱ ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ ዘንድሮስ ስንተኛ ሆናችሁ ትጨርሱ ይሆን ብቻ እንዳትወርዱ ብቻ ነው የምፈራላችሁ

sirak [736 days ago.]
 ALWAYS COFFEE

Montazhk3 [162 days ago.]
 Wolfpaw Consulting

Montazhk3 [161 days ago.]
 Karen cole paper LLC

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!