የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በቀድሞ ስያሜው ይቀጥላል
ታህሳስ 01, 2008

በይርጋ አበበ

ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በየሁለት ዓመቱ በሚታደስ የስፖንሰር ስምምነት መሰረት የሊጉን ስያሜ ሊቀይር ከስፖንሰር አድራጊው ድርጅት ጋር ስምምነት ላይ ደርሶ የነበረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሊጉን ስያሜ በቀድሞው አጠራሩ እንዲቀጥል መወሰኑን የፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መረጃ አስታወቀ።

ፌዴሬሽኑ በየዓመቱ ሰባት ሚሊዮን ብር እየከፈለ የሊጉን ስያሜ እንዲቀይርለት ከአንድ የቢራ አምራች ኩባንያ ጋር ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም የፌዴሬሽኑን ውሳኔ የተቃወሙት ክለቦች በተለይም የኢትዮጵያ ቡና እና የዳሽን ቢራ እግር ኳስ ክለቦች ጠንካራ ተቃውሞ ሀሳቡን ሳያስቀይረው እንዳልቀረ ተነግሯል። ከፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ክፍል የደረሰን መረጃ የሚያመለክተውም በተለይ ከሁለቱ ክለቦች የቀረበው ቅሬታ ለታይትል ስያሜው መቀየር ቀዳሚ ክምክንያት ሆኖ መቅረቡን ነው።

በዚህ የተነሳም በዚህ የውድድር ዓመት የሊጉ ስያሜ የቀደመውን ስሙን እንደያዘ ይቆይና ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ ደግሞ ሊጉ በፕሮፌሽናሊዝም አሰራር እንደሚቀጥል ተነግሯል። ፌዴሬሽኑ ከካስትል ቢራ ጋር የደረሰበትን ስምምነት ለማቋረጥም ተገድዷል። 

ኢትዮጵያ ቡና እና ዳሽን ቢራ እግር ኳስ ክለቦች የፌዴሬሽኑን የታይትል ስፖንሰርነት ስያሜ የተቃወሙት የክለቦቹ ቀዳሚ ስፖንሰሮች ተመሳሳይ ምርት የሚያመርቱት ሀበሻ ቢራ እና ዳሽን ቢራ በመሆናቸው ነው።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!