ፈረሰኞቹ ወደ ሲሸልስ ሲያመሩ ጦሩ ወደ ግብጽ ያቀናል
ታህሳስ 02, 2008

በይርጋ አበበ

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የ2016 የውድድር ዓመት የአህጉሩን የክለቦች ውድድር የእጣ ድልድል ትናንት ይፋ አድርጓል። ከካፍ ድረ ገጽ እንዳገኘነው ኢትዮጵያን ወክለው በአህጉራዊ ውድድር የቅድም ማጣሪያ ቅድመ ማጣሪያ ውድድር ላይ የሚሳተፉት ዱስ ጊዮርጊስ እና መከላከያ እግር ኳስ ክለቦች ተጋጣሚዎቻቸውን አውቀዋል።

የሲሸልስ ሊግ ሊጠናቀቅ ሁለት ሳምንታት ስለሚቀሩትና የአገሪቱ ሊግ አሸናፊ የሚሆነው ክለብ ተለይቶ ስላልታወቀ ከፈረሰኞቹ ጋር የሚጫወተው ቡድን የትኛው እንደሆነ ሊታወቅ ባይቻልም ከሶስቱ የሲሸልስ ክለቦች አንዳቸው ምናልባትም ቅዱስ ሚካኤል የተባለው ክለባቸው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ሳይገናኝ እንደማይቀር ይጠበቃል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ከደደቢት እና ከዋልያወቹ ጋር በተደጋጋሚ ጊዜ የመጫወት እድል ያገኙት የሲሸልስ ብሔራዊ ቡድን እና ክለቦች በዚህ ዓመትም ከሌላኛው የኢትዮጵያ ለብ ጋር የመጫወት አጋጣሚ ተፈጥሮላቸዋል። ፈረሰኞቹ የሲሸልሱን ተጋጣሚያቸውን በደርሶ መልስ ማሸነፍ ከቻሉ ቀጣይ ተጋጣሚያቸው ያለፈው ዓመት የውድድሩ አሸናፊ የነበረው የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊኩ ግዙፍ ክለብ ቴፒ ማዜንቤ ይሆናል።
በአሰልጣኝ ገብረ መድህን ሀይሌ የሚመራው መከላከያ በበኩሉ ያለፈውን የውድድር ዓመት ከግብጽ ሊግ በአራተኛነት ካጠናቀቀው ምስር አል ማካሳ ጋር መደልደሉ ታውቋል። ከሆስኒ ሙባረክ ስልጣን መውረድ በኋላ ፖለቲካዋ መረጋጋት የተሳናት ግብጽ በእግር ኳሷም መረጋጋት እየተሳናት ሲሆን ክለቦቿም ሆነ ብሔራዊ ቡድኗ በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ውድድሮች የቀድሞ ወኔያቸው ክዷቸው ሲንሸራተቱ ታይተዋል። ያም ሆነ ይህ ግን መከላከያ ከግብጹ ምስር ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ በብቃት ለመወጣት ከፍተኛ ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅበት የማይካድ ነው። ምክንያቱም የግብጽ ክለቦችና ብሔራዊ ቡድኖች ለኢትዮጵያዊያን ተጋጣሚዎቻቸው በቀላሉ እጃቸውን ሲሰጡ የማይታዩ መሆናቸው አንዱ ምክንያት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ መከላከያ በቡድኑ የያዘው ስኳድ ጥልቀቱ አስተማማኝ እንዳልሆነ ይታያልና ነው።

የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ እና የኮንፌዴሬሽን ዋንጫዎች የመጀመሪያ ሳመንት ጨዋታዎች በየካቲት ወር መጀመሪያዎቹ ሳምንታት የሚካሄዱ ሲሆን ያ ወቅት ደግሞ በአገር ውስጥ ሊጎች ብቻ የሚጫወቱበት የአፍሪካ ዋንጫ ወይም ቻን የሚካሄድበት ሰሞን በመሆኑ ለኢትዮጵያዊያኑ ክለቦችና ብሔራዊ ቡድን ከባድ ፈተና እንዳይሆን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይገባል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Ashenafi Kebede [769 days ago.]
 Gooooooooooooood luck our great club St.George fc ! የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊኩን ግዙፍ ክለብ ቴፒ ማዜንቤን አሸንፈን ታሪክ እንሰራለን ለምን ሪያል ማድሪድ ወይም ባርሴሎና አይሆንም አንፈራም ...... አንበሳ ነን አንበሳ ነን እኛ የሜዳ ላይ ንጉስ ለማንም አንተኛም ! በ 80 ዓመት የክለባችን ልደት ታሪክ ይሰራል ! ምንጊዜም ጊዮርጊስ !!!

Dani Sanjawe [769 days ago.]
 ሳንጅዬ ካለፈው ዓመት የውድድሩ አሸናፊ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊኩ ግዙፍ ክለብ ቴፒ ማዜንቤ ጋር በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ሲጫወት ቡላ ገለባ ደግም በአቅሙ ጃል ሜዳ ላይ ከጃል ሜዳ ከነማ ጋር ለውሃ ቀን ይጫወታል ሃሃሃሃሃሃሃ አቤት ልዩነታችን the difference is visible ! Always St.George VVVVVVVVVVVVVVVVVVV !!!

Bereket (Beka) [769 days ago.]
 Good luck St.George fc VVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVV !

Jumbo [769 days ago.]
 St.George fc is our Pride Ethiopian Foot Ball Ambassadar Good luck !

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!