የፈረሰኞቹ 80ኛ ዓመ የምስረታ በዓል ከታህሳስ እስከ ሚያዝያ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል
ታህሳስ 12, 2008


አዲሱ የክለቡ መዝሙር ይፋ ሆኗል     

የሱዳኑ አንጋፋ እና ግዙፍ ከለብ ኤል ሜሪክ ለበዓሉ ድምቀት አዲስ አበባ ይገባል

በይርጋ አበበ

በኢትዮጵያም ሆነ በአዲስ አበባ የመጀመሪያው የእግር ኳስ ክለብ የሆነው የ80 ዓመቱ የእድሜ ባለጸጋው የእግር ኳስ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተመሰረተበትን 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ከያዝነው ወር ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 30 2008 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እንደሚያከብር የክለቡ ኃላፊዎች ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ።

ከጠላት ወረራ በፊት ጀምሮ የተቋቋመው ይሄው ክለብ ላለፉት 80 ዓመታት የተለያዩ ፈታኝ እና አስደሳች ጊዜያትን እንዳሳለፈ የገለጹት የክለቡ የስራ አመራር ቦርድ ዋና ጸሃፊ አቶ ንዋይ በየነ ናቸው። አቶ ንዋይ በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት የክለቡን ታሪክ በአጭሩ በገለጹበት ወቅት እንደተናገሩት “በጠላት ወረራ ጊዜ በአገሪቱ ይዘመሩ የነበሩ የአገር ፍቅር መዝሙሮች ከቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ቤተሰብ ነበር። በዚህም ምክንያት በርካታ የክለቡ ቤተሰቦች ለእስር ተዳርገዋል” ያሉ ሲሆን አያይዘውም ክለቡ በበርካታ ፈተናዎች አልፎ ለዚህ መብቃቱ የሚያሳየው ምን ያህል ህዝባዊ ክለብ መሆኑን ነው ሲሉ ተናግረዋል። ክለቡ እስካሁንም 26 ጊዜ የአገሪቱን ከፍተኛ ሊግ ዋንጫ እና ዘጠኝ ጊዜያት ደግሞ የጥሎ ማለፍ ዋንጫዎችን እንዳነሳ ተናግረዋል።

“የቅዱስ ጊዮርጊስ ቅርሱ ህዝቡ ነው” ሲሉ የተናገሩት የክለቡ ዋና ጸሀፉ አቶ ሰለሞን በቀለ በበኩላቸው ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው በርካታ ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል። ከጋዜጠኞች የተነሱትን ጥያቄዎችና የአቶ ሰለሞንን ምላሽ በቀጣዩ ክፍል ይዘን እንቀርባለን።

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የ80ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አስተባባሪ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ አቶ ቀጸላ ሙላት “የበዓሉ ዝግጅቶች በአስር አብይ ኮሚቴ እየተሰራ ነው” ሲሉ የተናገሩ ሲሆን በክብረ በዓሉ ከሚቀርቡ ዝግጅቶች መካከልም “የአባላት ይእግር ኳስ ውድድር፣ የባዛር እና የሲምፖዚየም ዝግጅት፣ ኢንተርናሽናል የእግር ኳስ ጨዋታ፣ ለክለቡ በርካታ ስራ ላበረከቱ ሰዎች የሽልማት አሰጣጥ ስነ ስርዓት እና የአርበኞች ቀን አከባበር ይገኙበታል” ብለዋል።

ከፈረሰኞቹ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ የሚያካሂዱ ክለቦች የሱዳኑ ኤልሜሪክ እና የኬኒያው ቦልማሂር መሆናቸውን የክለቡ ዋና ጸሀፊ አቶ ሰለሞን በቀለ ተናግረዋል። አቶ ሰለሞን “በመጀመሪያ ያቀድነው ካፍን ከመሰረቱት ሶስት አገሮች ማለትም ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ ውስጥ በየአገራቱ የመጀመሪያዎቹን ክለቦች ማገናኘት ነበር። ሆኖም የግብጽ ሊግ ባለመጠናቀቁ የፊታችን ጃንዋሪ 3፣ 7 እና 14 በተከታታይ ሶስት ጨዋታዎች ያሉበት አልአህሊ የእኛን ጥያቄ ሊቀበል አልቻለም። በመሆኑም የሱዳንን አንጋፋ ክለብ ኤል ሜሪክን እና ኬኒያን ወክሎ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የሚጫወተውን የኬኒያውን ቦልማሂር ልንጋብዝ ችለናል” ብለዋል። የወዳጅነት ጨዋታዎቹም ጥር 1 ቀን እና ጥር 5 ቀን 2008 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

በመጨረሻም በገጣሚ ይልማ ገብረ አብ ተገጥሞ በሙዚቃ አሰናሳኙ ቴዎድሮስ መኮንን ወይም ቴዲ ማክ የተሰናሰነው ወይም የተቀናበረው አዲሱ የክለቡ መዝሙር ይፋ ሆኗል። የጋዜጣዊ መግለጫውን ዝርዝር ጉዳዮች በቀጣዩ ክፍል ይዘን እንመለሳለን። 


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Habetom [727 days ago.]
 የዚህ ባለታሪክ ክለብ ደጋፊ መሆኔ እጅግ ያኮራኛል ደሜ ቢጫና ቀይ ነው ምንጊዜም ጊዮርጊስ !!! Happy Birthday to all St.George fc fans and Players !!!

Samuel Sanjawe [726 days ago.]
 ቡና ገለባ መቼም ተፎካካሪያችን አይደለም !!!!! በኘሪምየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ና ቡና 32 ጊዜ ተገናኙ ቅዱስ ጊዮርጊስ 17 ጊዜ ሲያሸንፍ ቡና 6 ጊዜ አሸንፎል በ9 ጨዋታ አቻ ወተዋል ፕሪምየር ሊጉን ጊዮርጊስ 12 ጊዜ ዋንጫ ሲያነሳ ቡና 1 ጊዜ ነው የበላው ha ha ha

jaimibarca [725 days ago.]
 Today my prediction ቅዱስ ጊዮርጊስ 5 - 0 ቡና 1 Goal Adane 2 Goal Briyan, 1 Goal Tussa and 1 Goal Tesfaye Kobbo

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!