አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ወደ ኪጋሊ እነማንን ይዘው ትጓዛሉ?
ታህሳስ 16, 2008


በይርጋ አበበ

የኢትዮጵያ ብራዊ ቡድን በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ በቻን ውድድር የሚያሳትፈውን ውጤት በማግኘቱ ከአንድ ወር በኋላ ውድድሩ ወደሚዘጋጅበት የሩዋንዳዋ ዋና ከተማ ኪጋሊ ያቀናል። ቡድኑ ወደ ኪጋሊ ከማቅናቱ በፊት የመጨረሻዎቹን 23 ተጫዋቾች አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል። ለጊዜው ግን 30 ተጫዋቾችን የጠሩ ሲሆን ሰባቱ ከጉዞው ይቀሩና 23ቱ ብቻ የኪጋሊን አውሮፕላን ቲኬት ይቆርጣሉ። እኛም ባለፈው ሀሙስ ይፋ የተደረጉትን የአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ የመጀመሪያ ጥሪ የተደረገላቸውን 30 ተጫዋቾች በተመለከተ ሙያዊ እይታችንን ከዚህ በታች አቅርበነዋል።

የተዘነጉትን ማስታወስ

ኢትዮፉትቦል ዶትኮምን ጨምሮ በርካታ መገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቀዳዳዎቹ ብዙ ናቸው ከእነዚህ ቀዳዳዎች መካከል የተወሰኑትን ለመድፈን አሰልጣኞች ትኩረት ማድረግ አለባቸው። ለዚህ ደግሞ በተለይ በአማካይ ተከላካይ እና በአጥቂ መስመሩ በኩል ችግሮቹን በመጠኑም ቢሆን መቅረፍ የሚችሉ ተጫዋቾች መኖራቸውን በስም እየጠራን ጠቁመን ነበር።

የአሁኑ የአሰልጣኙ ጥሪም ይህንን ጥቆማ ያደመጠ ወይም ችግሩን ለይቶ ያወቀ አስመስሎታል። ለዚህ ሀሳብ ማጠንከሪያ የሚሆነው ኢትዮፉትቦል ዶት ኮም ከሳምንት በፊት ባቀረበው ዘገባ “በአሁኑ ወቅት ተስፋዬ አለባቸው በአፍሪካ የትኛውም ብሔራዊ ቡድን ሊያጫውተው የሚያስችል ብቃት ላይ ነው” ብሎ ዘግቦ ነበር። አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ የቡድናቸውን የመጀመሪያ 30 ተጫዋቾች ጥሪ ሲያቀርቡ ይህን ተጫዋች መጥራታቸውም እውነትም ቦታው ላይ የነበረውን ክፍተት በብቃት ለመድፈን አስበዋል እንድንል አድርጎናል።

በአምስት የሴካፋ ጨዋታ አንድ ጎል ብቻ ያገባ አጥቂ ይዘው የነበሩት አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ለቻን ውድድር ግን የጎሉን መስመር ለይቶ ማየት የተሳናቸውን የቀደሙ አጥቂዎቻቸውን በሙሉ ከምርጫቸው ውጭ ማድረጋቸው እና በምትኩም ወጣቱን ቡልቻ ሆራን እና አንጋፋውን ታፈሰ ተስፋዬን እንዲሁም ታታሪውን ሙሉዓለም ጥላሁንን መጥራታቸውም የነበረባቸውን ክፍተት የመድፈን ፍላጎት እንዳላቸው ያሳዬ ሲሆን የአሉላ ግርማ እና የአስራት መገርሳ በድጋሚ መጠራታቸው ደግሞ ቡድናቸውን ልምድ ባላቸውና በወጣቶች በመገንባት ከኪጋሊ አንድ ነገር ይዘው ለመምጣት ያሰቡ አስመስሏቸዋል። የአሁኑ ስብስባቸውም የተዘነጉትን ማስታወስ ይመስላል ያልነው ለዚህ ነው።

የተዘለሉት ተጫዋቾች

አሰልጣኝ ዮሃንስ ለቻን ውድድር ተጫዋቾችን ጥሪ ሲያደርጉ እነ ማን ሳይጠሩ ቀሩ የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል። አንድ አሰልጣኝ የብሔራዊ ቡድንን ከባድ ኃላፊነት ሲረከብ ተጫዋቾችን ከተለያዩ ክለቦች ጠርቶ ቡድኑን ሲያዋቅር በሚያካሂደው ምርጫ ላይ ቅሬታዎች አይፈጠሩም ማለት አይደለም። በአገራችንም ሆነ በየትኛውም ዓለም የሚያሰለጥኑ አሰልጣኞች ከዚህ አይነት መሰል ቅሬታ ነጻ ሆነው አያውቁም። አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌም በአሁኑ የብሔራዊ ቡድን ምርጫቸው ጥሪ ማድረግ ሲገባቸው የዘለሏቸው ተጫዋቾች አሉ ተብለው የተጠቀሱ ተጫዋቾች አሉ። አሰልጣኙ እንደ ሚካኤል ጆርጅ አይነት ተጫዋችን ሲጠሩ ጋዲሳ መብራቴ ምንይሉ ወንድሙ እና ታከለ ዓለማየሁን የመሳሰሉ አጥቂዎችን ዘንግተዋቸዋል ተብሏል። እነዚህ ሶስት አጥቂዎች በየትኛውም መመዘኛ ከሚካኤል ጆርጅ የተሻሉ እንጂ ያነሱ አለመሆናቸውን በማንሳትም ይከራከራሉ።

ከአጥቂ መስመሩ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ቡናዎቹ አብዱልከሪም መሃመድ፣ አህመድ ረሺድ፣ መስዑድ መሀመድ እና እያሱ ፈጠነ በምርጫው አለመካተታቸው የተነሳ ሲሆን የፈረሰኞቹ ምንያህል ተሾመ እና የመከላከያው በሀይሉ ግርማ የአሁኑ ምርጫ ሊያልፋቸው አይገባም ነበር ሲሉ የሚገልጹ አሉ።

የመጨረሻዎቹ እነማን ይሆናሉ?

ብሔራዊ ቡድኑ ወደ ሩዋንዳ ከማቅናቱ በፊት የመጨረሻዎቹን 23 ተጫዋቾች ለውድድሩ አዘጋጅ ክፍል የማሳወቅ ግዴታ ስላለበት አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌም የቡድናቸውን የመጨረሻዎቹን ተጫዋቾች ይፋ ማድረግ አለባቸው። በዚህም መሰረት አሁን ጥሪ ካደረጉላቸው 30 ተጫዋቾች መካከል ሰባቱ የሚቀነሱ እንደሚሆን ይጠበቃል። ጥያቄው ታዲያ እነማን ይቀነሳሉ የሚለው ሲሆን እሱን መልስ የሚሰጠን ጊዜ ቢሆንም የዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ ግን በተጫዋቾቹ ወቅታዊ ብቃት በመነሳት የአሰልጣኙ የመጨረሻ ተጫዋቾች እነማን ሊሆኑ እንደሚችሉ ከተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች በመነሳት ከዚህ በታች ይገልጻቸዋል።

ግብ ጠባዊዎች

አራት ተጫዋቾች የተጠሩበትን ይህንን ቦታ አቤል ማሞ እና ታሪክ ጌትነት ለመጀመሪያ ተሰላፊነት የሚፋለሙ በመሆኑ ሁለቱም ግብ ጠባቂዎች ወደ ኪጋሊ የማቅናታቸው ጉዳይ እርግጥ ሲሆን ከይድነቃቸው ኪዳኔ እና ለዓለም ብርሃኑ አንዳቸው የሚቀነሱ ይሆናል። አሰልጣኝ ዮሃንሰ ሳህሌ ከግብ ጠባቂዎች አሰልጣኙ ዓሊ ረዲ የሚሰጣቸውን ሪፖርት አድምጠው የሚወስኑ ቢሆንም ለዓለም ብርሃኑ ከእነ ታሪክ ጌትነት ጋር ወደ ኪጋሊ የሚጓዝ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ተከላካይ ክፍሉ

አስቻለው ታመነ፣ ስዩም ተስፋዬ፣ አንተነህ ተስፋዬ፣ ተካልኝ ደጀኔ እና ዘካሪያስ ቱጂ ከአሰልጣኝ ዮሃንስ ጋር አብረው በመስራት ልምድ ያገኙ በመሆኑ እና ባለፉት ጊዜያትም ጥሩ ብቃት ያሳዩ በመሆናቸው በቀጥታ 23ቱን የሚቀላቀሉ እንደሚሆን ሰፊ ግምት ተሰጥቷቸዋል። ይህንን ቦታ ለማጠናከር የተጠራው አሉላ ግርማ፣ ከወንድይፍራው ጌታሁን ጋር በመሆን የእነ ስዩምን ግሩፕ ይቀላቀላል የሚል ግምት ሲሰጠው የአዳማ ከነማው ሞገስ ታደሰ ምናልባት ወደ ሩዋንዳ የማቅናት እድል ሊኖረው ይችላል። ሱሌይማን መሃመድ እና ያሬድ ባዬህ የሚቀነሱ ሊሆኑ ይችላሉ።

አማካይ ቦታ

ይህ ቦታ ተመሳሳይ ብቃት እና የአጨዋወት ስልት በሚከተሉ ተጫዋቾች የተሞላ ቦታ ነው። የአማካይ ተከላካይነቱን ሚና ከተስፋዬ አለባቸው እና ጋቶች ፓኖም አንዳቸው ሊቆጣጠሩት እንደሚችል የሚጠበቅ ሲሆን ከእነዚህ ሁለት አማካይ ተከላካዮች ቀጥሎ ያለውን ቦታ ደግሞ ኤልያስ ማሞ፣ ራምኬል ሎክ፣ ታፈሰ ሰለሞን፣ ቢኒያም በላይ፣ ሳምሶን ጥላሁን፣ ታደለ መንገሻ እና አስራት መገርሳ ስለሚፋለሙበት ወደ ኪጋሊ ሊያቀኑ ይችላሉ።

ጎሉን የሚያስቆጥሩት

የጎል ድርቅ ለአሰልጣኝ ዮሃንሰ ሳህሌ ስብስብ ብቻ ሳይሆን ለአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ስብስብም ራስ ምታት የነበረ ችግር ነው። ይህ ያደረ ችግር ባለፈው የቻን ዋንጫ አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻውን ለስንብት የዳረገ ሲሆን ዮሃንስ ሳህሌም በውድድሩ ከሁለት ዓመት በፊት አገሪቱ የደረሰባትን አሳፋሪ ውጤት ለመካስ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያደርጉ ይሆናል። ለዚህም ከምርጫቸው ጀምረው ትኩረት እንደሚያደርጉ የሚጠበቅ ሲሆን ዳዊት ፈቃዱ፣ ታፈሰ ሰለሞን፣ ቡልቻ ሆራ እና ሙሉዓለም ጥላሁን እንደሚሆኑ ሲጠበቅ ሚካኤል ጆርጅ ከማጣሪያ የዘለለ ሚና ይኖረዋል ተብሎ አይጠበቅም።


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
emaraim [788 days ago.]
 If I am not mistaken the capital city of Rwanda is Kigali. Dear Reporter, please delete and substitute Kampla by kigali.

Babi [787 days ago.]
 Congrats Dedebit fc Bulla Gellebban lek asgebachuite !

Hagos [787 days ago.]
 Bravooooooooo Dedebit fc ! Dedebit 2 - 1 Dureyewe

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!