አሰልጣኝ ዮሐንስ ስብስብ እነማንን ያጣምራል?<
ታህሳስ 30, 2008

ደጎል የካታንጋው   

ሶስት የአማካይ ተከላከዮችን እና በተጨማሪነት ደግሞ ከቀኝ ተከላካይ በተጓዳኝ የአማካይ ተከላካይነት ሚና ቢሰጠው በአግባቡ መወጣት የሚችል ተጫዋች ይዟል። ለቦታው የተፈጠረ፣ መዓበል አረጋጊው እና ፒያኖ ተሸካሚው እየተባለ የሚጠራው የቅዱስ ጊዮርጊሱ ተስፋዬ አለባቸው ከሶስት ዓመታት በኋላ በድጋሚ የብሔራዊ ቡድን ማሊያ የሚለብስበትን አጋጣሚ አግኝቷል። በ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የብሔራዊ ቡድኑን ማሊያ ለብሶ የተጫወተው አስራት መገርሳም በድጋሚ የብሔራዊ ቡድን ጥሪ የቀረበለት ሲሆን በክለቡ ከቀኝ ተከላካይነት እየተነሳ ወደ አማካይ ተከላካይነት ሚና ተዘዋውሮ እንዲጫወት የተደረገው አሉላ ግርማም እንዲሁ ከረጅም ጊዜ ቆይታ በኋላ የብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀርቦለት ወደ ሩዋንዳ ከሚጓዘው ቡድን ጋር ተቀላቅሏል። ከእነዚህ ሶስት ተጫዋቾች በተጨማሪ ደግሞ በተደጋጋሚ ጊዜ ትችት ያስተናገደው የኢትዮጵያ ቡናው ጋቶች ፓኖም በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ዘመን በቦታው ተረጋግቶ የተቀመጠ ይመስላል።

እነዚህን አራት አማካይ ተከላካዮች የያዘው የዮሐንስ ሳህሌ ስብስብ ኤሊያስ ማሞ፣ ቢኒያም በላይ፣ በሀይሉ አሰፋ፣ ታደለ መንገሻ፣ ሳምሶን ጥላሁን እና ታፈሰ ሰለሞን የመሳሰሉትን አማካይ አጥቂዎች ይዟል። የአጨዋወት ታክቲክ እና አሰላለፍ እንደ አሰልጣኙ የአሰለጣጠን ፍልስፍና የሚወሰን ቢሆንም ወቅታዊ ብቃትን እና የተጫዋቾቹን ጫና የመሸከም አቅምን ታሳቢ በማድረግ አሰልጣኙ ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት አራት አማካይ ተከላካዮች እና ስድስት አማካይ አጥቂዎች የትኞቹን ያጣምራል? አሰላለፉስ የትኛውን ፎርሜሽን ይከተላል? የሚሉ ጥያቄዎችን አንስቼ ለኢትዮፉትቦል ዶትኮም ጋዜጣ ልኬያለሁ። አንባቢያንም አሰልጣኙ በየትኛው ፎርሜሽን ወይም የትኛውን ተጫዋች ቢጠቀሙ መልካም ነው የምትሉትን ሃሳብ እንድታቀርቡ እጋብዛለሁ።

ፌርሜሽን አንድ 4 1 3 2

ይህ አሰላለፍ በአምስት ተከላካዮች መከላከልን እና አምስት አጥቂዎችን መጠቀም ያስችላል። ለዚህ አሰላለፍ ደግሞ የአማካይ ተከላካዩን ቦታ ይበልጥ ወደ ተከላካዮች ተጠግቶ የሚጫወት አማካይ ተጫዋች ቢኖር ይመረጣል። ለዚህ ደግሞ በክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተከላካዮቹ ጋር ጠንካራ ቁርኝት መፍጠር የቻለው ተስፋዬ አለባቸው ይበልጥ ተመራጭ ተጫዋች ነው። አሰላለፉም ስዩም ተስፋዬ፣ አስቻለው ታመነ፣ ወንድይፍራው ጥላሁን እና ተካልኝ ደጀኔ በተከላካይ መስመር ሲሰለፉ ተስፋዬ አለባቸው ከእነሱ ፊት ያለውን ቦታ ይይዛል።
ከተስፋዬ አለባቸው ፊት ለፊት ያሉትን ሶስት የአማካይ ተከላካይ ቦታዎች ኤሊያስ ማሞ፣ ታደለ መንገሻ እና ቢኒያም በላይ እንዲይዙ ተደርጎ የአጥቂውን ክፍል ፈጣኑ ራምኬል ሎክ ከአንጋፋው ታፈሰ ተስፋዬ ጋር እንዲጣመሩበት ይደረጋል። በዚህ አሰላለፍ ወደ ፊት እየተጠጉ ማጥቃት የሚወዱት ስዩም ተስፋዬ እና ተካልኝ ደጀኔ ወደ ፊት ሲሄዱ ወይም ኳስን ተቆጣጥሮ መጫወት የሚወደው አስቻለው ታመነ የሚመርጡትን አጨዋወት ያለ ስጋት ለመጫወትም ሆነ ቦታቸውን ለቀው ወደ ፊት ሲሄዱ ያለ ስጋት እንዲያጠቁ ቦታቸውን በታማኝነት የሚጠብቅላቸው ተጫዋች ያሻቸዋል። በዛ ላይ ደግሞ በተለይ ሶስቱም አማካይ አጥቂዎች ከኳስ ጋር መጫወት የሚያዘወትሩ በመሆናቸው ሙሉ ትኩረታቸውን ተከላካይ ክፍሉን ከማገዝ ይልቅ አጥቂውን ክፍል ወደ ማገዙ እንዲያተኩሩ ያደርጋቸዋል። ለዚህ ነው ከተከላካዮቹ ፊት ለፊት ያለውን ቦታ ተስፋዬ አለባቸው ይሰለፍበት ያልኩት።

ሁለተኛው ፎርሜሽን 4 2 3 1

በዚህ አሰላለፍ ከአራቱ ተከላካዮች ፊት ለፊት ተስፋዬ አለባቸው እና ጋቶች ፓኖም ይጣመራሉ። ወደ ፊት ሂዶ መጫወት የሚወደው ጋቶች እና ከተከላካዮች መራቅ የማይወደው ተስፋዬ የአማካይ ተከላካዩን ቦታ ከያዙ ከእነሱ ፊት ያለውን ቦታ ደግሞ ኤሊያስ ማሞ፣ ሳምሶን ጥላሁን እና ራምኬል ሎክ እንዲይዙት ይደረግና ታፈሰ ታስፋዬ በፊት መስመር ብቻውን ይሰለፋል።

ሶስተኛው ፎርሜሽን 4 3 3

አራቱ አይነኬ ተከላካዮች እንደተጠበቁ ሆነው ከፊት ለፊታቸው ያሉትን ሶስት ቦታዎች አሁንም ተስፋዬ አለባቸው፣ ሳምሶን ጥላሁን እና ታደለ መንገሻ ይይዟቸዋል። የፊተኛውን ክፍል ደግሞ ኤሊያስ ማሞ፣ ራም ኬል ሎክ እና ታፈሰ ተስፋዬ እንዲይዙት ይደረጋል። በዚህ አሰላለፍ የነጻ ሚናውን ኤሊያስ ማሞ እንዲይዝ ከተደረገ በተደራቢ አጥቂነት ከታፈሰ ጀርባ ያለውን ቦታ በነጻነት መጠቀም እንዲችል ከሜዳው ሁለተኛው ክፍል ላይ የሚሰለፉት ታደለ መንገሻ እና ሳምሶን ጥላሁን ከፍተኛ ሀላፊነት ይኖራቸዋል።

እኔ ከዚህ በላይ ያለውን ተመልክቻለሁ የተለየም ሆነ የተሻለ ሀሳብ አለኝ የምትሉ ደግሞ የራሳችሁን ሀሳብ ይዛችሁ በመቅረብ በዚህ ገጽ ላይ ልንወያይ እንችላለን።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!