ናትናኤል ዘለቀ ታሪካዊ ጎል በማግባት ቡድኑን አሸናፊ አደረገ
ጥር 02, 2008

በይርጋ አበበ

አንጋፋው ኢትዮጵያዊ የእግር ኳስ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ መሆኑ ይታወሳል። ክለቡ ካዘጋጀው የበዓሉ ማድመቂያዎች መካከል አንዱ የሆነውና በደጋፊዎችም ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የወዳጅነት ጨዋታ ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሂዶ ነበር። የሱዳኑን ሀያል እና አንጋፋ ክለብ በወዳጅነት ጨዋታ የገጠሙት ፈረሰኞቹም በናትናኤል ዘለቀ ብቸኛ ጎል አንድ ለባዶ በማሸነፍ በዓላቸውን በድምቀት ማክበሩን ተያይዘውታል። የጎሏ ባለቤት ናትናኤል ዘለቀም ቢሆን ክለቡ 80ኛ ዓመት በዓሉን እያከበረ ባለበት ሰዓት ያስቆጠራት ጎል በመሆኑ ታሪካዊ ተጫዋች ያደርገዋል።

ፈረሰኞቹ ለብሔራዊ ቡድን የተመረጡት አምስት ተጫዋቾች ማለትም ተስፋዬ አለባቸው በሀይሉ አሰፋ አሉላ ግርማ አስቻለው ታመነ እና ራምኬል ሎክ በሌሉበት ሀያሉን የሱዳን ክለብ ገጥመው አንድ ለባዶ ማሸነፋቸው ያስወድሳቸዋል። ከጨዋታው በኋላ አስተያየታቸውን ለኢትዮፉትቦል ዶትኮም የሰጡ የክለቡ ደጋፊዎች በውጤቱ እና በጨዋታው መደሰታቸውን ገልጸው ነገር ግን ክለቡ ከዚህም በላይ ሊስተካከል የሚችልባቸው ክፍተቶች እንዳለ ገልጸዋል። ደጋፊዎቹ ለክለባቸው ቀጣይ ጉዞ ይበጃል ብለው የተናገሩት ደጋፊዎች የክለቡን ማሊያ በተፈለገው መጠን ማግኘት የሚችሉበት እድል አለመኖሩን ለክለቡ የማይመጥኑ ተጫዋቾች መኖራቸው እና የስታዲየም ግንባታውን የሚመለከቱ ናቸው።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለተኛ የነጥብ ጨዋታውን የፊታችን ሀሙስ ከአመሻሹ 11 ሰዓት ሲሆን በአዲስ አበባ ስታዲየም ከኬኒያው ሻምፒዮን                  ጋር ይጫወታል።

 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Ashenafi Kebede [736 days ago.]
 Nati man great player. i hope this young man soon will join europian club !

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!