ዋልያዎቹ ወደ ኪጋሊ አቀኑ
ጥር 05, 2008

ይርጋ አበበ

በአገር ውስጥ ሊጎች ብቻ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ በሚሳተፉበት የቻን ዋንጫ ለመወዳደር ማጣሪያውን ያለፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ረፋዱ ላይ ወደ ሩዋንዳ ኪጋሊ አቅንተዋል። ብሔራዊ ቡድኑ 23 ተጫዋቾችን እና ሶስት አሰጣኞችን እንዲሁም የህክምና እና የተለያዩ የኪቺንግ ስታፉን ጨምሮ ሌሎች የጉዞው አባል የሆኑ በርካታ ሰዎችን ይዞ ነው ዛሬ የተጓዘው።

በምድብ ሁለት ከዴሞክራቲክ ኮንጎ፣ አንጎላ እና ካሜሩን ጋር የተደለደለ መሆኑ ይታወቃል። ከሳምንታት በፊት “ወደ ሩዋንዳ የምናቀናው ካለፈው የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ነው። ከምድባችን ማለፍ ትልቁ ግባችን ነው” ሲሉ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን በውድድሩም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ቡድናቸውን በሚገባ ማዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በውድድሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችው ከሁለት ዓመታት በፊት ደቡብ አፍሪካ አዘጋጅተው በነበረው ሶስተኛው የቻን ዋንጫ ሲሆን በወቅቱም አንድም ጎል ሳታስቆጥር በሁሉም ተሸንፋ ከምድቧ አራተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል። በዘንድሮው የቻን ዋንጫ ውድድር የደረሰው ብሔራዊ ቡድንም በማጣሪያው ኬኒያን በደርሶ መልስ ሁለት ለአንድ እና ብሩንዲን ደግሞ ሶስት ለሁለት አሸንፎ ነው።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Tesfaye G/weld [768 days ago.]
 ዋልያዎቹ በሩዋንዳም ተአምር መስራታቸዉን ይቀጥላሉ!

Dani man [766 days ago.]
 Loser and fake coach Yohanes “ወደ ሩዋንዳ የምናቀናው ካለፈው የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ነው። ከምድባችን ማለፍ ትልቁ ግባችን ነው” ሲሉ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን በውድድሩም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ቡድናቸውን በሚገባ ማዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። ha ha ha ha please leave us alone ! Long Live for Sir Coach Sewinet Bishawe !

samifelex [766 days ago.]
 እኔ የማዝነው የምናደደው በማይችል ኮች እየሰለጠነች ላለችው ሃገሬ ነው ሃገራችን ላይ ለተዘጋጀ ደካማ ውድድር CECAFA እንኳን ቡድን መስራት ያልቻለ አሰልጣኝ ምኑን አሰልጣኝ ሆነው .....ቻን ላይ ትላንትና በኮንጎ 3 ለ 0000000 ተሸንፎ አንገታችንን አስደፍቶናል የስራህን ይስጥህ ጁነዲን ስንት የሚችሉ አሰልጣኞች እያሉ .........

Gizegeta [766 days ago.]
 Message for Yohanes ምንም ነገር ብትናገር አያምርብህም:: ሴካፋ አንተ ምን አይነት ኮች እንደሆንክ ቁልጭ አድርጎ ለሕዝቡ አሳይቷል ይልቅ ዝም ብለህ ቦታውን ልቀቅ ለሌሎች ለሚችሉት.....you are loooooossssssser !

Ashenafi Kebede [766 days ago.]
 ተከብረሽ የኖርሺው በሠውነት ቢሻው ! ዮሃንስ መጣና አረገሽ እንዳሻው…ሁሁሁ

Abdu from Awassa [766 days ago.]
 የቻን የምድብ ዕጣ ድልድልን ባየሁኝ ጊዜ ዮሃንስ አሳዘነኝ ሃሃሃሃሃ በዚህ ስብስቡ በ ኮንጎ ( 3 ለ 0 ) አንጎላ ? ለ ? ካሜሮን ? ለ ? ሲቀለድበት ታየኝ :: ha ha ha

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!