ፈረሰኞቹ ከጎርማሂያ ዛሬ 11 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ
ጥር 05, 2008

በይርጋ አበበ

የተመሰረተበትን 80ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ያለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ዛሬ ከአመሻሹ 11 ሲሆን ከኬኒያው ጎርማሂያ ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታል። ቅዱስ ጊዮርጊስ ባለፈው እሁድ ምሽት የሱዳኑን ሀያል ክለብ ኤል ሜሪክን አስተናግዶ በናትናኤል ዘለቀ ብቸኛ ጎል አንድ ለባዶ ማሸነፉ የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ሌላ የወዳጅነት ጨዋታ አዘጋጅቷል።

ብሔራዊ ቡድናችን ለቻን ዋንጫ ወደ ሩዋንዳ ማቅቱን ተከትሎ እንደ ተስፋዬ አለባቸው በሀይሉ አሰፋ ራምኬል ሎክ አስቻለው ታመነ እና አሉላ ግርማ አይነት ወሳኝ ተጫዋቾቹን በዛሬው ጨዋታ ማሰለፍ የማይችለው ቅዱስ ጊዮርጊስ በኬኒያው ሻምፒዮን ይፈተናል ተብሎ ይጠበቃል።

የፈረሰኞቹ ተጋጣሚ ቦርማሂያ ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቶ በሸራተን አዲስ ሆቴል ማረፊያውን አድርጎ ነበር። ጎርማሂያ በኬኒያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሲሆን በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግም ኬኒያነ ወክሎ የሚወዳደር ክለብ ነው።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Dani Sanjawe [769 days ago.]
 Always St.george fc VVVVVVVVVVVV Ethiopian Foot Ball Ambassador !

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!