ፈረሰኞቹ ደጋፊዎች ለምን ከካምቦሎጆ ራቁ?
ጥር 07, 2008


በይርጋ አበበ

በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ በአንጋፋነቱ ቀዳሚ የሆነውና በአገር ቤት ውድድሮች የበላይነቱን የያዘው ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ የበርካታ ደጋፊዎች ባለቤት መሆኑ ይታወቃል። የክለቡ የተመዘገቡ ደጋፊዎች ብዛትም ከአስር ሺዎች በላይ መሆኑን አንዳንድ መረጃዎች ያሳብቃሉ።

ክለቡ በአገር ውስጥ ውድድሮች የበርካታ ዋንጫዎች ባለቤት ከመሆኑም በላይ አገር ቤት ውስጥ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ተጫዋቾች መካከልም እጅግ ውጤታማዎቹን የያዘ ክለብ ነው። ነገር ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የዚህ ታላቅ ክለብ ደጋፊዎች ክለባቸው ጨዋታ በሚኖረው ሰዓት በስታዲየም የሚታዩበት ጊዜ ከቀደሙት ዓመታት በእጅጉ ያነሰ መሆኑን ሁሉም የስፖርት ቤተሰብ የሚስማማበት እውነታ ነው። ጥያቄው ታዲያ የፈረሰኞቹ ደጋፊዎች ለምን ከካምቦሎጆ ደጆች ሊርቁ ቻሉ? የሚለው ነው።

ለዚህ ጥያቄ በቅርቡ “ስፖርት ዞን” ለሚባል አንድ የሬዲዮ ፕሮግራም አስተያየታቸውን የሰጡት የክለቡ የቦርድ ፕሬዚዳንት ምክንያቱ አንድም ከክለቡ ተደጋጋሚ የውጤት የበላይነት የተነሳ ሲሆን ወዲህ ደግሞ ስታዲየም ውስጥ ከሚነገሩ መጥፎ ቃላት ጆሯቸውን ለማራቅ እንደሆነ ነበር የተናገሩት።

በዚህ ጉዳይ ላይ ለመጻፍ የተነሳሁት የፕሬዚዳንቱን አስተያየት ትክክል ወይም ስህተት ብሎ ለመፈረጅ ሳይሆን አንባቢያን እና በእግር ኳስ ፍቅር የወደቁ የክለቡም ሆነ የአገራችን እግር ኳስ ደጋፊዎች አስተያየታቸውን እንዲሰጡበት ነው።


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!